ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ሰዎች በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ሰዎች ወንድና ወንድ ወይም ሴትና ሴት ሆነው በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እና አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ለብስራት ሬድዮ አስታውቋል።
የተቋሙ የገበያ ጥናት አገልግሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢትዮጵያ አብረሃም ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በአንድ ወር ውስጥ 150 ሺህ ሰዎች የፍል ውሀ አገልግሎትን የሚጠቀሙ ሲሆን በዓመት 1.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞችን ተቋሙ እንደሚያስተናግድም ነው የገለፁት።
ወይዘሮ ኢትዮጵያ አክለው እንደገለፁት አቅመ ደካማ አባትን ወይም እናትን ለመርዳት አብሮ መግባት ሲያስፈልግ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ በመጠየቅ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወጣቶች እህትማማቾችም ቢሆኑ እንኳን በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ገብተው እንዲታጠቡ እንደሚያደርግ አገልግሎቱ ገልጿል።
አያይዞም ደንበኞች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት የቅሬታ መስጫ ሳጥን እና መዝገብያ መዘጋጀቱን የገለጹ ሲሆን፣ ቅሬታዎቹ በየጊዜው እየተነበቡ ማስተካከያዎች ይደረግባቸዋልምብሏል።

❤3
🚨 ሰበር ዜና
🇪🇹🇪🇷 የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን የአፋር ክልል መሪ ገለጹ
የአፋር ክልል መሪ አወል አርባ ለአልጀዚራ እንደገለጹት፣ የኤርትራ ጦር በአፋር ክልል ውስጥ በቀጥታ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል። በዘመቻውም ከፍተኛ የጦር አዛዦችና ከባድ መሳሪያዎች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
አወል አርባ እንደገለጹት፣ የኤርትራ ጦር የአፋርን ግዛት በማስገባት የኢትዮጵያን ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን ዋና የንግድ መስመር ለመቆጣጠር እና በክልሉ ያለውን የድንበር ሁኔታ ለመቀየር ያለመ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
በኤርትራ ጦርና በአፋር ክልል ኃይሎች መካከል ያለው ውጊያ የኃይል ልዩነት ያለበት መሆኑንም የክልሉ መሪ ገልጸዋል።
⚠️ ማስታወሻ፦ እነዚህ የአፋር ክልል መሪ አወል አርባ የሰጡት መግለጫዎች ናቸው። የኤርትራ ጦር በአፋር ውስጥ መግባቱ እና በተጠቀሱት ስፍራዎች ላይ የተደረገው የግዛት ቁጥጥር በተናጠል በበቂ ገለልተኛ ምንጮች እስካሁን አልተረጋገጠም።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ የአልጀዚራ የቅርብ ዘገባዎች በአፋር ክልል ውስጥ ከባድ ውጊያዎች መኖራቸውን እና የትግራይ ኃይሎች ሶስት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ዘግበዋል።
አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ።

❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ባሕርዳር❤️
በባሕር ዳር ያለው አሁናዊ ድባብ ምን ይመስላል ?
የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከቀኑ 10:00 በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል።
በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ዳር ስፖርት ወዳድ ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በስታዲየም አቅራቢያ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።
ደጋፊዎች በተዘጋጁ የትኬት መቁረጫ ቦታዎች ላይ ትኬቶችን ሲገዙ ተመልክተናል።
የከተማው ነዋሪዎች በሀገራዊ ቀለሞች አሸብርቀው ጨዋታው የሚጀምርበትን ሰዓት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ስፖርት
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም

❤4
24 የመማሪያ ክፍል መስኮቶችን የሰረቁ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የቡሬ አቦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች 24 መስኮቶችን በመስረቅ የተከሰሱ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።
የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ያየህ አድገህ እንደገለፁት የትምህርት ቤቱ አመራሮችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ለፖሊስ ባቀረቡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ችሏል።
ተከሳሾቹ የሰረቁትን መስኮቶች በባጃጅ ጭነው ወደ አዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ በመውሰድ ለቁራሌ ለመሸጥ ሲሞክሩ መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማድረጉን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ፖሊስ በምርመራው ያገኘውን ማስረጃና የተያዙትን ንብረቶች በማስረጃነት በማቅረብ መዝገቡን ለቡሬ ወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ልኳል።በዚህም ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች በቡሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ መሆናቸው በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ በመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል።
በውሳኔውም ስንታየሁ ባንቴ፣ ስማቸው ፈንታሁን እና ምስጋናው አስማረ የተባሉት ሦስት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል። ሌላኛው ተከሳሽ ደግሞ የተሰረቀውን እቃ በመደበቅ ጥፋተኛ በመሆኑ የ1 ዓመት ከ3 ወር እስራት መፈረዱን ብስራት ሬዲዮ ከቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የደረሰው መረጃ ያመላክታል።
Dagu

🌊 ባህር ላይ የሚኖሩ አስደናቂ ሕዝቦች!
🌊 እስቲ አስቡት… ቤትዎ መሬት ላይ ሳይሆን በባህር ላይ ቢሆንስ?
ለአብዛኛዎቻችን ባህር የምንጎበኘው ቦታ ነው። ለአንዳንድ ሕዝቦች ግን ባህር የሚጎበኙት ቦታ ሳይሆን ቤታቸው ነው።
በደቡብ ምሥራቅ እስያ፣ በተለይም በፊሊፒንስ፣ ማሌዥያ እና ኢንዶኔዥያ መካከል ባሉ የባህር አካባቢዎች ባጃው (Bajau/Sama-Bajau) ተብለው የሚጠሩ ማህበረሰቦች ከባህር ጋር የተቆራኘ ልዩ አኗኗር አላቸው።
🏠 በአንዳንድ ቦታዎች ቤቶቻቸውን በባህር ውስጥ በተተከሉ የእንጨት እግሮች ላይ ይገነባሉ። በጀልባ ይጓዛሉ፣ በባህር ውስጥ ዓሣ ያጠምዳሉ፣ እና የባህር ሀብት የኑሯቸው ዋነኛ ክፍል ነው።
🤿 ከሁሉም የሚያስደንቀው ግን የውሃ ውስጥ አደን ችሎታቸው ነው።
አንዳንድ የባጃው የባህር አዳኞች ያለ ዘመናዊ የመተንፈሻ መሳሪያ በተደጋጋሚ ወደ ጥልቅ ውሃ ይገባሉ። በዚህ የተነሳም የባህር ሕይወትን ከትውልድ ወደ ትውልድ የተማሩበት እጅግ ልዩ ዕውቀት አዳብረዋል።
ለእነሱ የባህር ድምፅ የተለመደ ነው፤ የሞገድ እንቅስቃሴ የሕይወታቸው አካል ነው፤ ባህርም ከቤታቸው የሚለይ ነገር አይደለም።
✨ ይህ ታሪክ የሚያስታውሰን አንድ ውብ ነገር አለው፦ ሰው የሚኖርበት ቦታ ሕይወቱን ይቀይረዋል፤ ሕይወቱም በተራው አካባቢውን የመረዳት ልዩ ችሎታ ይሰጠዋል።
ለእኛ ባህር የሚያልቅ አድማስ ሊሆን ይችላል፤ ለእነሱ ግን እዚያው አድማስ ላይ ቤት፣ ሥራ፣ ባህል እና ሕይወት አለ። 🌊
አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ
#አዲስኢንሳይት #Bajau #ባጃው #SuluSea #CelebesSea #የዓለምአስደናቂነገሮች #አስደናቂሕይወት

❤2
ሰመራ ኤርፖርት‼️
በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ዋና ከተማ ሰመራ አየር ማረፊያ (ኤርፖርት) ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ የሚገልፁ መረጃዎች በስፋት ሲሰራጩ ቆይተዋል።
ሚድያችን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ እንዳረጋገጠው በሰመራ አየር ማረፊያ ላይ የደረሰ ምንም አይነት ጥቃት የለም።
ይሁንና የድሮን ምት እንደሆነ በተገመተ ከባድ ጥቃት ምክንያት ከኤርፖርቱ በቅርብ ርቀት በሚገኘው የክልሉ መንግስት መቀመጫ ቤተ መንግስት ግቢ ወስጥ ዛሬ ምሽት 1:45 ገደማ ጥቃት መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።
ይህ ለክብር እንግዶች (VIP) እንዲሆን ታስቦ እየተሰራ ያለ ህንፃ ተመትቶ በእሳት መያያዙ የታወቀ ሲሆን ስለደረሰው ጉዳት እስካሁን አለመታወቁን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።
"በቦታው ከፍተኛ የፀጥታ ሀይል ተሰማርቶ የክልል ፕሬዚዳንቱን የመጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው፣ ወደ ቦታ ሰው እንዳይደርስ እየተከለከለ መሆኑንም አይተናል" በማለት አንድ ምንጫችን ማምሻውን ለመሰረተ ሚዲያ ተናግረዋል።
ኤርፖርቱ በመደበኛ ስራው ላይ ነው፣ በረራም አልተቋረጠም።
በዚህ መረጃ ዙርያ እስካሁን ከአፋር ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መረጃ የለም።

ሹመት‼️
የደሴ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ፤ ጃንጥራር አባይን በመተካት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ካቢኔ አባላት
👉 አቶ ግርማ ሰይፉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፦
1. አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ
2. አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
3. አቶ ጥላሁን ከበደ - በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
4. አቶ ሃፍታይ ገ/እግዚአብሔር - በም/ ከንቲባ ማዕረግ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
5. ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
6. ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ
7. ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ
8. ወ/ሪት ፂዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል) - የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ
9. ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ
10. ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ
11. ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. አቶ ግርማ ሰይፉ - የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
13. አቶ ቢኒያም ምክሩ - ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
14. አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
15. ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ
16. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ
17. ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
18. አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
19. ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ
20 ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
21. ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ
22. ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ
23. አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
24. አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
25. አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ