ትግራይ ቴሌቪዥን ላይ የድሮን ጥቃት‼️
የህወሓት ልሳን የሆነው የትግራይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ ዛሬ መስከረም 17/2019 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ጥቃት ተፈፅሞበታል።
መቀሌ ከተማ ዓዲ ሺንድሁን በተባለው ሰፈር የሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት በድሮን ጥቃት ጉዳት እንደደረሰበት በስፍራው ከሚገኙ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን የቴሌቪዥን ጣቢያው መሰረዙን እና የትግራይ ቴሌቪዥንን በመረጃ ምንጭነት በመጠቀም መረጃ ማሰራጨት እንደሚያስጠይቅ ማሳወቁ ይታወሳል።

#Update ‼️
የአቶ ጌታቸው አባት ማረፋቸው ተሰማ ‼
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ አባት አቶ ረዳ ካህሳይ ከዚህ አለም መለየታቸው ተሰምቷል።ለቤተሰቡ እና ወዳጅ ዘመድ መፅናናትን እንመኛለን።

❤2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💔 የጦርነት ጥቁር ጥላ፡
ጦርነት በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ መች አጭቆ አያውቅም፤ ነገር ግን የእሱ መዘዝ የሚያርፈው በሰዎች ላይ ብቻ አይደለም። አቅም በሌላቸው፣ ቋንቋ በሌላቸው እና ማንም በማይጠብቃቸው ንጹሃን እንስሳት ላይ የሚደርሰው መአት ከዚህ በላይ ልብ የሚሰብር የለም። ይህ ቪዲዮ የጦርነትን አረመኔነትና አስከፊነት ከቀዝቃዛው ፖለቲካ እና ስልጣን ርቆ በሚገኘው የተፈጥሮ ዓለም መነጽር ይመለከተዋል። የሰው ልጅ የስግብግብነት እሳት ድምፅ አልባ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ንጹሃን እንስሳትን ጭምር እንዴት እንደሚፈጅ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ፍቅርንና ታማኝነትን ብቻ ከሚሰጡን ፍጥረታት ጋር ስንጣላ፣ በጦር መሣሪያ ስንፈራርሳቸው የት ላይ ደርሰናል? እነዚህ እንስሳት በሰው ሰራሽ እሳት የደረሰባቸውን ጉዳት ሲያሳዩ፣ የዓለምን ግፍ በዝምታ የሚሸከሙት የተፈጥሮ ቁስሎች ናቸው። ጦርነት ማሸነፍ ወይም መሸነፍ ብቻ ሳይሆን፣ መላውን የምድር ሕይወትና ሰብአዊነት አብሮ የሚቀብር የሞራል ውድቀት መሆኑን ያስገነዝባል። የሰው ልጅ ጦርነት መች ቆመና? የሚገርመው ግን ጦርነቱ በሌሎች ፍጥረታት ላይ እያደረሰ ያለው ጥፋት ዝምታችን ነው።

አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ስለ ቡና የሰጠችው ድንቅ ምላሽ! ☕✨
ለጉብኝት ከመጣ ፈረንጅ ጋር በእንግሊዝኛ ቋንቋ በቀጥታ በመነጋገር፣ ስለ ቡና ታሪክ እና አሰራር የሚፈልገውን መረጃ ሁሉ በብቃት አስረክባዋለች። የኢትዮጵያ እናቶች እውቀት ወሰን የለውም፤ እንደ ሀገር ልንኮራባቸው ይገባል! 👏👏
እናንተስ በዚህች እናት ድንቅ ብቃት ምን ተሰማችሁ?
An Ethiopian Mother’s Remarkable Response About Coffee ☕💚💛❤
An Ethiopian mother has captured hearts with her impressive knowledge and confidence while speaking fluent English to a foreign visitor. She beautifully explained the history, culture, and traditional preparation of Ethiopian coffee, answering every question with clarity and pride.
This is a wonderful reminder that the wisdom of Ethiopian mothers runs deep. Their knowledge, hospitality, and cultural heritage deserve to be celebrated and appreciated around the world. ❤️
What do you think about this inspiring mother’s incredible knowledge and confidence? Share your thoughts below! 👇
#EthiopianCoffee #Ethiopia #CoffeeCulture #ViralReels #ReelsVideo #FYP #ProudlyEthiopian

‟የተገኘውን ድል አጽንተን የበለጸገች ኦሮሚያን ለመገንባት እንሠራለን” - ሽመልስ አብዲሳ‼️
👉ከፊታችን ውስብስብ ተግዳሮቶች ይጠብቁናል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፣ “እኛ አሸናፊ ትውልድ ነን” በማለት የተገኘውን ድል ማጽናትና የበለጸገች እና በራሷ የምትተማመን ኦሮሚያን ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ለሕዝቡ ያሳየውን እምነት አመስግነው፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በአግባቡ ለመወጣት እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ሕዝብ ለማንነቱ፣ ለነፃነቱ፣ ለባህሉና ለማኅበራዊ እሴቶቹ ያደረገውን መስዋዕትነት ያነሱት ሽመልስ አብዲሳ፣ የተገኙ ውጤቶችን በመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ የልማት እና የብልጽግና ሥራዎችን ማፋጠን እንደሚገባ ገልጸዋል።
በቀጣይ ጊዜያት የሚገጥሙ ተግዳሮቶች ውስብስብ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ለዚህም ቁርጠኝነት፣ ዕውቀት፣ ክህሎትና አቅም እንዲሁም አንድነትና በጋራ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

🦡 ሀኒ ባጀር፦ ከእባብ መርዝ ጋር የሚጋፈጥ እንስሳ
ሀኒ ባጀር (Honey Badger) በሳይንሳዊ ስሙ Mellivora capensis የሚታወቅ ሲሆን፣ በአፍሪካና በእስያ ክፍሎች ይገኛል። መጠኑ ትንሽ ቢሆንም ጠንካራ አካል፣ ወፍራም ቆዳና ራሱን ለመከላከል የሚያግዙ ልዩ ባህሪያት አሉት።
🐍 ከእባብ መርዝ ጋር ያለው ግንኙነት
ሀኒ ባጀር ከመርዛማ እባቦች ጋር ሲጋጭ የእባብ መርዝ ሊነክሰው ይችላል። በተለይ ነርቭን የሚጎዱ መርዞች በላዩ ላይ ከባድ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ቢችሉም፣ ሀኒ ባጀር ለአንዳንድ የእባብ መርዞች የተለየ የመቋቋም ችሎታ አለው።
ከከባድ ንክሻ በኋላ ለጊዜው ሊደክም ወይም ሊወድቅ ይችላል፤ ከዚያም ከመርዙ ተጽእኖ ሲያገግም እንደገና መንቀሳቀስ ይችላል። ይህ ግን ሀኒ ባጀር ለሁሉም አይነት መርዝ የማይጎዳ ማለት አይደለም።
🛡️ የሚያስደንቀው ቆዳው
ወፍራምና ተንቀሳቃሽ ቆዳው ከንክሻና ከጥፍር ጥቃት የተወሰነ ጥበቃ ይሰጠዋል። እንስሳው በሌላ እንስሳ ከተያዘም ሰውነቱን በማንቀሳቀስ ጥቃት የሚያደርስበትን አካል ለመንከስ ሊሞክር ይችላል።
🍯 ስሙ ለምን “ሀኒ ባጀር” ተባለ?
ማርና የንብ ቀፎ ውስጥ ያሉ እጮች ከሚመገባቸው ምግቦች መካከል ናቸው። ሆኖም ምግቡ በዚህ ብቻ አይወሰንም፤ ትንንሽ አጥቢ እንስሳትን፣ ወፎችን፣ እንቁላሎችንና ተሳቢዎችንም ይመገባል።
🌍 በአጭሩ
ሀኒ ባጀር መርዝን “ሙሉ በሙሉ የማይፈራ” እንስሳ ሲሆን፣ ከአንዳንድ ኃይለኛ የእባብ መርዞች ተጽእኖ ለመቋቋም ያዳበረው ልዩ የሰውነት ችሎታ የሚያስደንቅ እንስሳ ነው።
አዲስ ኢንሳይት — ዓለምን በአዲስ እይታ።

ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ሰዎች በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።
ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ሰዎች ወንድና ወንድ ወይም ሴትና ሴት ሆነው በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እና አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ለብስራት ሬድዮ አስታውቋል።
የተቋሙ የገበያ ጥናት አገልግሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ ኢትዮጵያ አብረሃም ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በአንድ ወር ውስጥ 150 ሺህ ሰዎች የፍል ውሀ አገልግሎትን የሚጠቀሙ ሲሆን በዓመት 1.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞችን ተቋሙ እንደሚያስተናግድም ነው የገለፁት።
ወይዘሮ ኢትዮጵያ አክለው እንደገለፁት አቅመ ደካማ አባትን ወይም እናትን ለመርዳት አብሮ መግባት ሲያስፈልግ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ በመጠየቅ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወጣቶች እህትማማቾችም ቢሆኑ እንኳን በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ገብተው እንዲታጠቡ እንደሚያደርግ አገልግሎቱ ገልጿል።
አያይዞም ደንበኞች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት የቅሬታ መስጫ ሳጥን እና መዝገብያ መዘጋጀቱን የገለጹ ሲሆን፣ ቅሬታዎቹ በየጊዜው እየተነበቡ ማስተካከያዎች ይደረግባቸዋልምብሏል።

❤3
🚨 ሰበር ዜና
🇪🇹🇪🇷 የኤርትራ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ግዛት መግባቱን የአፋር ክልል መሪ ገለጹ
የአፋር ክልል መሪ አወል አርባ ለአልጀዚራ እንደገለጹት፣ የኤርትራ ጦር በአፋር ክልል ውስጥ በቀጥታ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ ጀምሯል። በዘመቻውም ከፍተኛ የጦር አዛዦችና ከባድ መሳሪያዎች መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
አወል አርባ እንደገለጹት፣ የኤርትራ ጦር የአፋርን ግዛት በማስገባት የኢትዮጵያን ወደ ጅቡቲ የሚወስደውን ዋና የንግድ መስመር ለመቆጣጠር እና በክልሉ ያለውን የድንበር ሁኔታ ለመቀየር ያለመ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው።
በኤርትራ ጦርና በአፋር ክልል ኃይሎች መካከል ያለው ውጊያ የኃይል ልዩነት ያለበት መሆኑንም የክልሉ መሪ ገልጸዋል።
⚠️ ማስታወሻ፦ እነዚህ የአፋር ክልል መሪ አወል አርባ የሰጡት መግለጫዎች ናቸው። የኤርትራ ጦር በአፋር ውስጥ መግባቱ እና በተጠቀሱት ስፍራዎች ላይ የተደረገው የግዛት ቁጥጥር በተናጠል በበቂ ገለልተኛ ምንጮች እስካሁን አልተረጋገጠም።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ የአልጀዚራ የቅርብ ዘገባዎች በአፋር ክልል ውስጥ ከባድ ውጊያዎች መኖራቸውን እና የትግራይ ኃይሎች ሶስት ከተሞችን መቆጣጠራቸውን ዘግበዋል።

❤1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ባሕርዳር❤️
በባሕር ዳር ያለው አሁናዊ ድባብ ምን ይመስላል ?
የኢትዮጵያ እና ሴኔጋል ጨዋታ ዛሬ ከሰዓታት በኋላ ከቀኑ 10:00 በባህርዳር ስታዲየም ይካሄዳል።
በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ የባህር ዳር ስፖርት ወዳድ ህብረተሰብ በነቂስ ወጥቶ በስታዲየም አቅራቢያ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።
ደጋፊዎች በተዘጋጁ የትኬት መቁረጫ ቦታዎች ላይ ትኬቶችን ሲገዙ ተመልክተናል።
የከተማው ነዋሪዎች በሀገራዊ ቀለሞች አሸብርቀው ጨዋታው የሚጀምርበትን ሰዓት በጉጉት እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ስፖርት
መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም

❤4
24 የመማሪያ ክፍል መስኮቶችን የሰረቁ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ የቡሬ አቦ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማሪያ ክፍሎች 24 መስኮቶችን በመስረቅ የተከሰሱ ሦስት ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በእስራት መቀጣታቸው ተገልጿል።
የቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ያየህ አድገህ እንደገለፁት የትምህርት ቤቱ አመራሮችና የአካባቢው ሕብረተሰብ ለፖሊስ ባቀረቡት ጥቆማ መሠረት ፖሊስ ክትትል በማድረግ ተጠርጣሪዎቹን ለመያዝ ችሏል።
ተከሳሾቹ የሰረቁትን መስኮቶች በባጃጅ ጭነው ወደ አዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ በመውሰድ ለቁራሌ ለመሸጥ ሲሞክሩ መሆኑን ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታኅሣሥ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ ማድረጉን ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል።
ፖሊስ በምርመራው ያገኘውን ማስረጃና የተያዙትን ንብረቶች በማስረጃነት በማቅረብ መዝገቡን ለቡሬ ወረዳ ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ልኳል።በዚህም ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት ተከሳሾች በቡሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ጥፋተኛ መሆናቸው በማስረጃ ከተረጋገጠ በኋላ በመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል።
በውሳኔውም ስንታየሁ ባንቴ፣ ስማቸው ፈንታሁን እና ምስጋናው አስማረ የተባሉት ሦስት ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል። ሌላኛው ተከሳሽ ደግሞ የተሰረቀውን እቃ በመደበቅ ጥፋተኛ በመሆኑ የ1 ዓመት ከ3 ወር እስራት መፈረዱን ብስራት ሬዲዮ ከቡሬ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅ/ቤት የደረሰው መረጃ ያመላክታል።
Dagu