🌍 “AMARA” — ከኢትዮጵያ ውጭም የሚገኝ ስያሜ!
“አማራ” ስንል ብዙዎቻችን ወዲያውኑ የኢትዮጵያውን አማራ ሕዝብ እናስታውሳለን። ነገር ግን “Amara” የሚለው ተመሳሳይ ስያሜ በተለያዩ የዓለም አገሮች እንደ ከተማ፣ መንደር፣ ሰፈር ወይም ታሪካዊ ቦታ ይገኛል።
እነሆ ከተረጋገጡት ምሳሌዎች፦
🇷🇴 1. AMARA — ሮማኒያ
በሮማኒያ Ialomița County ውስጥ Amara የምትባል ከተማ አለች። ከተማዋ በLake Amara ትታወቃለች፤ ሐይቁም በማዕድናት የበለፀገ ውሃና የሕክምና ጭቃ በመኖሩ ከጤና ቱሪዝም ጋር የተያያዘ መዳረሻ ነው።
🇮🇷 2. AMĀRA / AMEREH — ኢራን
በኢራን Markazi Province ውስጥ Amereh (Āmereh) የሚባል መንደር ይገኛል። በአንዳንድ የስም አጻጻፎች Amāra ተብሎም ይጠቀሳል።
🇹🇷 3. AMARA — ቱርክ
በŞanlıurfa ክልል፣ Halfeti አካባቢ የሚገኘው ዛሬ Ömerli ተብሎ የሚጠራው መንደር በታሪክ Amara በሚል ስም ይታወቅ ነበር።
🇮🇳 4. AMARA — ህንድ
በህንድ Odisha ግዛት ውስጥ Amara የሚባሉ መንደሮች ተመዝግበዋል። ይህም “Amara” የሚለው ስም በደቡብ እስያም እንደ የቦታ ስም መኖሩን ያሳያል።
🇪🇸 5. AMARA — ስፔን
በSan Sebastián ከተማ ውስጥ Amara የሚባል ታዋቂ ሰፈር አለ። ሰፈሩ Amara Viejo (Old Amara) እና Amara Nuevo (New Amara) በሚባሉ ክፍሎች ይጠቀሳል።
🇳🇬 6. AMARA — ናይጄሪያ
በናይጄሪያ Kogi State ውስጥ Amara የሚባል መንደር ተመዝግቧል።
🇸🇩 7. AMARA — ሱዳን
በሰሜናዊ ሱዳን፣ በጥንታዊ ኑቢያ አካባቢ Amara West እና Amara East የሚባሉ ታሪካዊ የአርኪዮሎጂ ቦታዎች አሉ።
በተለይ Amara West በጥንታዊ ግብፅ ዘመን የኩሽ/ኑቢያ ክልል የነበረውን ታሪክ ለመረዳት ጠቃሚ የአርኪዮሎጂ ቦታ ነው።
---
🤔 አንድ ስያሜ በአውሮፓ፣ እስያ እና አፍሪካ በተለያዩ ቦታዎች መገኘቱ በራሱ የሚያስገርም የቋንቋና የታሪክ ጉዳይ ነው። 🌍
“AMARA” — አንድ ስም፣ ብዙ ቦታዎች፣ የተለያዩ ታሪኮች! ✨

❤1
በጥቃቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ!
በማኅበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው አሳዛኝ የጥቃት ቪዲዮ ውስጥ ተሳትፋለች የተባለችው “ፈርደውስ” እና አባሪዎቿ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ በተደረገ ፈጣንና የተቀናጀ ክትትል ተጠርጣሪዎች ሆነው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።
ይህ እርምጃ ማንም ሰው በሕግ ላይ እንደማይሆን የሚያሳይ ነው። የተፈጸመው ጥቃት እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም፣ የተጠርጣሪዎች መያዝ ግን ፍትሕ እንዲረጋገጥ የሚያስችል ወሳኝ እርምጃ ነው።
ሕብረተሰቡም እንደዚህ ያሉ ክስተቶችን በራሱ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ፣ ያለውን መረጃ ለሕግ አካላት በማቅረብ ለፍትሕ ሂደቱ አስተዋፅዖ ማድረግ ይገባዋል።
ለሰላምና ለሕግ የበላይነት የሚደረገው ትግል በሕጋዊ መንገድ ሲመራ ብቻ ዘላቂ ፍትሕ ይሰፍናል። ለፈጣን ምላሹ የአዲስ አበባ ፖሊስን እና ለሰላማችን የሚሠሩ የሕግ አስከባሪዎችን እናመሰግናለን።

👍3🤬1
አሁናዊ መረጃ❗❗
ነሐሴ 12/2018❗
በደቡብ ወሎ በምዕራብ ቀጠና ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለጸ።
በምዕራብ ወሎ ቀጠና በሚገኙ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ከዛሬ ማለዳ 11 ሰዓት ጀምሮ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ገለፁ።
ውጊያው እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ በሚባሉት በዋናነት በመቅደላ ወረዳ፣ በተንታ እንዲሁም በደላንታ ቀጠናዎች በሚገኙ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሰባት የተለያዩ ንኡስ ግንባሮች ተከፍሎ እየተካሄደ ይገኛል።
በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
#አዩዘሀበሻ

❤3
መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲል ሕወሃት ከሰሰ።
የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ ዛሬ የድሮን ጥቃት ፈጽሞብናል ሲሉ ሕወሃት መራሹ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከሰዋል።
የባለስልጣናቱ ክስ የተሰማው በሁለቱ ኃይላት መካከል ከዛሬ ነገ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚለው ውጥረት እያየለ በመጣበት ወቅት ነው።
የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉን ከላሊ ሃጋዚን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው የፌደራል ኃይሎች ከክልሉ መዲና መቀሌ በግምት 15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዳንደራ በተባለች መንደር ውስጥ ባለ የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማእከል ላይ ጠዋት 4:00 ገደማ "የድሮን ጥቃት ፈፅመዋል" ብለዋል።
ደረሰ በተባለው የድሮን ጥቃት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጹት ባለስልጣኑ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዳልሰጡ ዘገባው አመልክቷል።
አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ካህን ግን በጥቃቱ ቢያንስ አንድ ሰው መገደሉን ተናግረዋል።
በድሮን ጥቃቱ የተወነጨፈው ሚሳኤል በአንድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ መውደቁን መመልከታቸውን የተናገሩት ካህኑ ለዜና ወኪሉ "በጥቃቱ የተገደለ አንድ ታጣቂ በቁስለኛ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ሲወሰድ አይቻለሁ" ብለዋል።
በህወሃት እና በፌዴራል መንግስቱ መካከል ዳግም ጦርነት ቀስቃሽ ውጥረት ከተከሰተ ወዲህ የድሮን ጥቃት ሲፈጸም በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህ ሁለተኛው ነው።

❤1👍1
በአሜሪካ የሚኖሩ ከ5 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ሃገሪቷን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ
በአሜሪካ የፌዴራል ፍርድ ቤት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ የህጋዊ መኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ጥበቃ (TPS - Temporary Protected Status) እንዲያበቃ ውሳኔ አስተላለፈ።
የፌዴራል ዳኛ ብሪያን ሙርፊ ማክሰኞ ዕለት ባስተላለፉት ውሳኔ፣ የሃገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት (DHS) በኢትዮጵያውያን ላይ የነበረውን የTPS ጥበቃ ለማቋረጥ ያቀደውን እርምጃ እንዳይፈጽም ታግዶ የቆየውን የህግ እገዳ በማንሳት የትራምፕ አስተዳደር እርምጃውን እንዲቀጥል ፈቅደዋል።
📌 ከውሳኔው ጀርባ የተካሄዱ ዋና ዋና ነጥቦች
ጊዜያዊ የህጋዊ መኖሪያ ጥበቃ (TPS) በኢትዮጵያ በነበረው የፖለቲካና የፀጥታ ችግር ምክንያት በጆ ባይደን አስተዳደር ወቅት በ2022 ተሰጥቶ የነበረ ነው።
የፌዴራል ዳኛው ይህንን እገዳ ያነሱት፣ የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት (Supreme Court) ባለፈው ሰኔ ወር የትራምፕ አስተዳደር የTPS ጥበቃዎችን የማቋረጥ ስልጣን እንዳለው የሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ ነው።
ምንም እንኳን ህጋዊ የመኖሪያ እና የሰራ ፈቃዱ የመሰረዝ ሂደት የሚቀጥል ቢሆንም፣ የውሳኔውን ህገ-መንግስታዊነት አስመልከቶ የተመሰረተው ክስ በፍርድ ቤት ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል።
ውሳኔውን ተከትሎ በአሜሪካ የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ቤተሰቦቻቸው አዲስ የህግና የመኖሪያ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል።

ወለጋ‼️
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ከትላንት በስተያ ረቡዕ ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ኦዲተርን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል። በጥቃቱ የአዋሽ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ኦዲተር ለሚ መንግሥቱ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ማሙሽ ማሩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው፣ በወረዳው ቱሉ ሌንጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ "መቀ ለሊ" በተባለ ሥፍራ ጸጥታ ኃይሎች ከባንኮቹ የተሠበሠበ ጥሬ ብር በተሽከርካሪ አጅበው በመጓዝ ላይ ሳሉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ክፉ ዘመን😭😭
አንድ ህፃን የሚፈልገው የጦር መሳሪያ ድምፅ ሳይሆን የእናትና የአባት ድምፅ ነው። የሚፈልገው የጥይት ድምፅ ሳይሆን የሳቅና የፍቅር ድምፅ ነው።
ለልጆቻችን የምንተወው የጦርነት ቁስል ሳይሆን የሰላም ውርስ ይሁን። 🕊️😭
እናም መመካከር ያለብህ እንዲህ ያሉ ህፃናትን ህልም እና ተስፋ የሚበላውን የብሄር ጭቆናና ዘረኝነት ለማስወገድ መሆን አለበት!!
💙 ቤተሰባችን ይሁኑ!
የተመረጡና ጠቃሚ መረጃዎችን፣ ልዩ ይዘቶችን እና ወቅታዊ ዜናዎችን በቀጥታ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ! 📲💙
https://t.me/AddisInsight23/14102

ዮሚፍ ቀጀልቻ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረ
ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በአርጀንቲና የተካሄደውን የቦነስ አይረስ ግማሽ ማራቶን ውድድር 56 ደቂቃ ከ51 ሰኮንድ በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ የግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዳግም አሻሽሏል።
ዮሚፍ ኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ በሊዝበን ያስመዘገበውን የ57 ደቂቃ ከ20 ሴኮንድ የቀድሞ ክብረ ወሰን በ29 ሰከንዶች አሻሽሏል።j
ዮሚፍ እ.አ.አ. በ2024 ቫሌንሲያ ላይ 57 ደቂቃ ከ30 ሰኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ይዞ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቱ በዓለም የግማሽ ማራቶን ንግስናውን በድጋሚ አረጋግጧል።
በተመሳሳይ በሴቶች የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፎይተን ተስፋይ ርቀቱን በ1 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ57 ሰኮንድ በማጠናቀቅ አሸናፊ ሆናለች።
የዮሚፍ አዲሱ የዓለም ክብረ ወሰን የዓለም አትሌቲክስን ይፋዊ ማረጋገጫ የሚጠብቅ ይሆናል።

#ድል በሌለው ጦርነት የልጆችን የነገ ተስፋ አታጨልሙ!
ፖለቲካ ስልጣንን ሊጠብቅ ይችላል፤ ትውልድን ግን አይጠብቅም። ጦርነት የሚያሸንፈው ማንም ቢሆን፣ የሚሸነፈው ግን ሁሌም ልጆች ናቸው።
14 እና 16 ዓመት ያሉ ወጣቶች የመጽሐፍ ገጽ ሊገልጡ፣ በክፍል ውስጥ ሕልማቸውን ሊጽፉ፣ ለነገ ሕይወታቸውን ሊገነቡ የሚገባቸው ዕድሜ ላይ ናቸው። ነገር ግን ዛሬ በትከሻቸው የሚጫነው መጽሐፍ ሳይሆን መሣሪያ ሲሆን ልብ ይሰብራል።
ትከሻቸው የትምህርት ቤት ቦርሳን እንኳን በትክክል ለመሸከም ያልጠነከረ ሆኖ ሳለ የጦርነትን ክብደት እንዲሸከም ማስገደድ ከስህተት በላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ጭካኔ ነው።
የቱንም ያህል ብንከፋ፣ የቱንም ያህል ብንለያይ፣ የልጆችን ልጅነት ከእጃቸው መንጠቅ ይቅር የማይባል ስህተት ነው። ሕፃናት የጦርነት ነዳጅ ሳይሆኑ የሰላም ተስፋ መሆን አለባቸው።
ልጆችን ከጦርነት ጠብቁ፤ የሀገር ነገ በእነሱ እጅ ነው። 😭🕊️
ምስል :- ምዕራብ ጎጃም

ግዙፉ ስኩዊድ (Giant Squid)።
🦑 ግዙፉ ስኩዊድ — ከጥልቅ ውቅያኖስ የመጣ እጅግ አስገራሚ ፍጥረት
ግዙፉ ስኩዊድ (Architeuthis dux) በዓለም ላይ ከሚኖሩ ትልቁ የስኩዊድ ዝርያዎች አንዱ ነው። በጥልቅ ውቅያኖስ ውስጥ ስለሚኖር ለረጅም ጊዜ ሰዎች እንደ ተረት የባሕር ጭራቅ ይቆጥሩት ነበር። ዛሬ ግን እውነተኛ እንስሳ መሆኑ በሳይንስ ተረጋግጧል።
ሰውነቱ ከዓይነቱ ጋር በሚለያይ መልኩ ከ10 ሜትር በላይ ሊረዝም ይችላል፤ እጅግ ረጅሙ መጠን ግን በሳይንሳዊ መለኪያ ላይ ክርክር አለበት። አብዛኛው ርዝመቱ የሚመጣው ከሁለቱ ረጅም መያዣዎቹ ነው። እነዚህ መያዣዎች ምርኮውን ለመያዝ የሚረዱ ጠንካራ የመምጠጫ ክብ አካላት አሏቸው።
ዓይኑ ደግሞ እጅግ ያስደንቃል። የግዙፉ ስኩዊድ ዓይኖች እስከ 27 ሴ.ሜ. ያህል ዲያሜትር ሊደርሱ ይችላሉ፤ ይህም በእንስሳት ዓለም ከሚታወቁት ትልልቅ ዓይኖች መካከል ያስገባዋል። በጥልቅ ባሕር ጨለማ ውስጥ እንዲታይ ይህ ትልቅ ዓይን ትልቅ ጥቅም አለው።
ግዙፉ ስኩዊድ ዓሣንና ሌሎች የባሕር ፍጥረታትን ይመገባል። በጥልቅ ውቅያኖስ ውስጥ ስለሚኖር በተፈጥሮ አካባቢው ማየት እጅግ ከባድ ነው፤ ስለዚህ ሳይንቲስቶች ስለ አኗኗሩ የሚያውቁት አሁንም በጣም ውስን ነው።
ከሁሉ የሚያስገርመው፣ ይህ እንስሳ በእውነት አለ ብለን ከማረጋገጣችን በፊት ለዘመናት እንደ “የባሕር ጭራቅ” ተቆጥሮ ነበር። ዛሬም ቢሆን የጥልቅ ውቅያኖስ ብዙ ምስጢሮች እንዳሉት የሚያሳይ አስደናቂ ምሳሌ ነው።

❤2