Addis Insight -አዲስ እይታ
3.19K subscribers
9.28K photos
347 videos
33 files
3.06K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
#ParliamentQuotes

" ከደመወዙ 35% ግብር ፣ 7% ጡረታ በድምሩ 42% ይቆረጣል። ከ58% ደመወዙ ላይ በእያንዳንዱ በሚሸምተው ሸቀጥ 15% ቫት (VAT) ይቆረጣል። ትራንዛክሽን ላይ ንግድ ባንክ ለሰርቪስና ቫት እያለ ሌሎችም የማይታወቁ ተቆራጮችን ይቆርጣል።  ሰራተኛው ለውሃ፣ ለመብራት ለሌሎችም አገልግሎቶች ይቆረጥበታል። እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ኑሮን መቋቋም አቅቶታልና ለዚህ ታጋሽ ሲቪል ሰርቪስ እና አነስተኛ ኑሮ ላይ ላለው ዜጋ ምን ታስቦለታል ? ከሚመሰርቱት መንግሥት ምን እንጠብቅ ?  " - አቶ ባርጠማ ፍቃዱ
1
አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ

​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።

በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።

​ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።

በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።

​   ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ  በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
3
የቀድሞዉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ተቀበሩ።

አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን የፖለቲካና የኃይማኖት መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ ተቀበሩ።

እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት የካቲት 28 ቀን 2026 ከኻሜኒ ሌላ ሴት ልጃቸዉን፣ የልጅ ልጃቸውን ፣ አማቻቸውንና 11 ባለሥልጣኖቻቸውን ገድለዋል።

ባለቤታቸውም ክፉኛ ቆስለዉ ኋላ ሞተዋል።

የኻሜኒ ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የዚያን ቀን ቆስለዋል።

ሞጅታባሕ ጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ቢይዙም እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ እይታ አልቀረቡም።  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለአባታቸው በተደረገው የሽኝት ሥርዓትም ሆነ በዛሬው የቀብር ሥርዓት ላይ አልተገኙም።

ኢራንን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ የተቀበሩት በሐገሪቱ ሰሜን-ምሥራቅ ቅዱስ የቀብር ሥፍራ ማሻሐ,ድ ዉስጥ ነዉ። ማሽሐድ የኻሚኔይ የትዉልድ ሥፍራም ናት።

የኻምኔይ አስከሬን ወደ ቀብሩ ስፍራ ከመወሰዱ ከሰዓታት በፊት የአሜሪካ ጦር ርዕሠ-ከተማ ቴሕራንን ከማሻሐድ ከተማ ጋር የሚያገኛኘውን የባቡር መስመር ጨምሮ የተለያዩ የኢራን የመሠረተ-ልማት አውታሮችን አውድሟል።

ይሁንና በቀብር ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር የኢራን ሕዝብ የማሻሐድ ከተማን አጥለቅልቋት ነዉ የዋለዉ። ሕዝቡ የብቀላ ጥሪ ምልክት የሆነውን ቀይ አርማ እያዉለበለበ እስከ ቀብሩ ሥፍራ ድረስ ተጉዟል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም
3
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ሰራቆ ቀበሌ በግ ሰር'ቆ ሲያ'ርድ በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለው ሌባ መቀጣጫ ሆነ።
ሰ'ርቆ በመግፈፍ ላይ የነበረውን በግ ተሸክ'ሞ ከተማውን እንዲዞር ተደርጓል።
👍5
💔 የአንድ ዘመን እንባ...
አንድ ቀን የዓለምን ስታዲየሞች በጭብጨባ ያናወጡ ሰዎች፣ ዛሬ በዝምታ እንባቸውን እየጠረጉ ይታያሉ።
ሮናልዶ... ሜሲ... ኔይማር...
ሦስቱም በተለያየ ሀገር ተወለዱ፤ በተለያየ መንገድ አደጉ፤ ግን በአንድ ነገር ተመሳሳይ ነበሩ—ለሕዝባቸው የዓለም ዋንጫን ለማምጣት ልባቸውን ሰጥተው ተዋጉ።
ሰዎች ጎላቸውን ያስታውሳሉ፣ እነሱ ግን ያመለጣቸውን ዕድል ያስታውሳሉ።
እነዚህ እንባዎች የሽንፈት አይደሉም... የትልቅ ህልም ዋጋ ናቸው።
ስታዲየሙ ባዶ ይሆናል፤ የደጋፊዎች ጩኸት ይጠፋል፤ መብራቶቹም ይጠፋሉ። የሚቀረው ግን በሣሩ ላይ የወደቁት እንባዎች እና በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የተጻፈው ታሪክ ብቻ ነው።
ጊዜ አዳዲስ ኮከቦችን ያመጣል፤ ነገር ግን ዘመን የሚፈጥሩ ተጫዋቾች በየትውልዱ አንዴ ብቻ ናቸው።
ዛሬ የምናየው የሦስት ተጫዋቾች እንባ አይደለም... የአንድ ትውልድ ትዝታ ቀስ ብሎ ሲዘጋ የምንሰማው የልብ ስብራት ነው። 💔


ለአንድ ትውልድ የማይረሳ ደስታን ሰጣችሁ።
በአስደናቂ ጎሎቻችሁ ዓለምን አስደመማችሁ።
በታሪካዊ ፉክክሮቻችሁ ሚሊዮኖችን አዝናናችሁ።
ለድል ስትታገሉ ላባችሁን አፈሰሳችሁ፤ አንዳንድ ጊዜም እንባችሁን አስመለከታችሁን።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ለእግር ኳስ ታሪክ በወርቅ ፊደል የማይጠፋ ምዕራፍ ጻፋችሁ።
እናመሰግናለን...! ❤️
5
የድሮን ጥቃት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ “በመካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በድሮን ጥቃት የመነኮሳት ህይወት አለፈ”‼️

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ በመካነ ሰላም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው ዓባይ ገዳመ አስቀጤስ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ 4:30 አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩ 2 ሴቶች ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን እና ሌሎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ምግብ እየሰሩ በነበረበት ወቅት ነው ጥቃት የተፈፀመው ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የፋኖ ሀይሎች ከትመዋል በሚል ነው ተብሏል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊
(አዩዘሀበሻ)
2
ሰበር መረጃ‼️
የኢትዮጵያን መንግስት ለመጣል ያለመ ስብሰባ በኤርትራ ድንበር ተደረገ፣ስብሰባውን የመሩት አቶ አማኑኤል አሰፋ ናቸው።
ሕወሓት የብልጽግናን መንግስት አስወግዳለሁ እያለ ነው፡፡ ቡድኑ ካለፈው እሁድ አንስቶ 'ህልውናችን የሚረጋገጠው በብልጽግና መቃብር ላይ ነው' በሚል መሪቃል ስብሰባዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ከወትሮው በተለየ መልኩ የሕወሓት አመራሮች ‹‹ብልጽግናን ከስልጣን ማስወገድ አለብን›› በማለት በግላጭ እየተናገሩ ነው፡፡
በሚዲያዎቻቸውም የፌደራል መንግስቱን 'ጄንኖሳይዳዊ አገዛዝ' የሚል ስያሜ ሰጥተው በትግራይ ቴሌቪዥን ጭምር ዜና መስራት ጀምረዋል። የፌደራል መንግሥቱ ለህወሓት የጦርነት ጉሰማ በቀጥታ የሰጠው ምላሽ የለም።
(አዩዘሀበሻ)
=====================
3👎1
ማስተዋል ከጠፋ፣ ዛሬም ነገም ተጎጂ ሁላችንም ነን ⚠️

ጦርነት የማንንም ድንበር አያከብርም፤ እንደ ሰደድ እሳት ተስፋፍቶ ቤትን፣ ንብረትን፣ ሕይወትንና ሰብአዊነትን ያወድማል። ይህ አውዳሚ መቅሰፍት በነደደ ቁጥር የሚጠፋው የአንድ ወገን ህልውና ሳይሆን፣ የሁላችንንም የጋራ ህልውና ነው።

በአንድ በኩል በሰሜን አቅጣጫ የሚኖረው ሕዝብ በጦርነት እሳትና በከባድ ሰቆቃ ውስጥ እየተቃጠለ ሳለ፣ የቀረው የሀገራችን ሕዝብ ግን የእሳቱን ነበልባል ለማጥፋት ከመተባበር ይልቅ፣ የማገዶ እንጨት እየጨመረ ማቀጣጠሉ ልብን የሚያቆስልና ከባድ ታሪካዊ ስህተት ነው።

ጦርነት ሲባባስ የሚቃጠለው የአንድ ወገን ቤት ብቻ አይደለም፤ መላው ሀገር ነው። ዛሬ በዝምታ፣ በግዴለሽነት ወይም በተሳሳተ እልህ ለጦርነት ነዳጅ የሚሆኑ ሰዎች፣ ነገ የዛሬው እሳት ወደ ራሳቸው ማኅበረሰብ እንደሚዛመት ሊገነዘቡ ይገባል።

«"እሳት ለባሹን ገድሎ አይተኛም።" ይባላል።»

ጦርነትን በእልህ፣ በጥላቻ ወይም በድፍን ብሔርተኝነት ማበረታታት መጨረሻው የሁሉም ሽንፈት እንጂ የማንም ድል አይደለም። ሀገርን አመድ ከማድረጉ በፊት፣ ሕዝባችን ከእንቅልፉ ነቅቶ ሰላምን፣ ይቅርታንና የጋራ አብሮነትን ከማንኛውም ልዩነት በላይ ማስቀደም አለበት።

ይህ ምስልና መልእክት የሚያስተምረን አንድ ግልጽ እውነት አለ፤ የጥፋትን መንገድ ትተን ለሰላም፣ ለይቅርታ፣ ለፍትሕና ለጋራ ህልውናችን መቆም ያለብን ዛሬ ነው፤ ምክንያቱም የጦርነት እሳት አንዴ ከተለኮሰ ማንን እንደሚያቃጥል አይመርጥም።

ምስል ኤ አይ (ለማስተማሪያነት ብቻ )
3