Addis Insight -አዲስ እይታ
3.19K subscribers
9.28K photos
347 videos
33 files
3.06K links
እርሶ ቻናላችንን Subscribe ሲያደርጉ ወቅታዊና ሁሉን አቀፍ መረጃዎችን ያገኛሉ።
Link👇
https://t.me/AddisInsight23
Download Telegram
"ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም

ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ኩዋኩ ቦንሳም ከጥቂት ቀናት በፊት ካቦ ቨርዴ አርጀንቲናን ረትታ ታልፋለች ፤የአርጀንቲናም የአለምዋንጫ ጉዞ ይጠናቀቃል "ታይቶኛል" ሲል ተናግሮ ነበር።

ትናንት ምሽት ታድያ አርጀንቲና ድል ካደረገች በኋላ ትንቢቱ ፉርሽ የሆነበት ይህ ጠንቋይ "ጥቆላዬን ስሰራ የቴክኒክ ችግር ገጥሞኝ ነበር" ሲል ተናግሯል።

ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም አይደል...
1
ካናዳ ከራሷ ድግስ ላይ በሞሮኮ ተባረረች 🤔

ካናዳ 0-3 ሞሮኮ
የ16ቱ የጥሎ ማለፍ  ጨዋታዎች ወደ ቀጣዩ ዙር በpoly market መሰረት ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድል።

ብራዚል 66%
እንግሊዝ 53%
አርጀንቲና 83%
ኮሎምቢያ 59%
" የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

ደሳለኝ (ዶ/ር) "ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለው ዋጋ እጅግ የበዛ እና ከባድ ነው እርሶ ስልጣን ላይ ሲቀመጡ የገቡት የሰላም እና የብልጽግና ቃልኪዳን ነበር በተግባር ያየነው ተገላቢጦሹን ነው" በማለት ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል።

"የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያስከተለው አስከፊ ሰብአዊ ውድመት እና ጠባሳ ሳይሽር ዛሬም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚታዩት ቀጣይነት ያላቸው ግጭቶች እና ጦርነቶች፣ ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር ጥቃቶች፣ እገታዎች እና አለመረጋጋቶች የዜጎችን የመኖር መብት ነፍገዋል" ሲሉም አክለዋል።

በቅርቡም "ከትግራይ እና ከኤርትራ ሀይሎች ጋር የሌላ ጦርነት ስጋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉም ጉዳዩ የደረሰበትን አሳሳቢነት ጠቁመዋል።

በዝርዝር ባቀረቡት ጥያቄ ምን አሉ ?

" በፖለቲካው መስክ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ፣ የሀገራዊ ተቃርኖዎች መስፋት ወይም Political Polarization፣ የሲቪክ ማህበራት መኮስመን፣ በጋዜጠኞች እና በሚዲያዎች ላይ እገዳዎች እና ክልከላዎች ዜጎች አማራጭ ድምፅ እንዳያሰሙ አፍነዋቸዋል።

በርካታ የፖለቲካ እስረኞችም ህገ-መንግስታዊ የፍትህ ዋስትና ተነፍገው ይገኛሉ። ይህ አጠቃላይ የሰላም፣ የፀጥታ እና የፖለቲካ ውድቀት የፓርቲዎ የተሳሳተ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ውጤት፣ አንድነትን በተግባር ማምጣት ያቃተው የመደመር ትረካ መዋቅራዊ ስብራት ውጤት ነው።

መንግስት የችግሮቹን ስር መሰረት ትቶ ምልክቶቹን ብቻ የመቀጥቀጥና እና በቁጥር ጨዋታ ህዝብን የማደናገር አካሄድ እየተከተለ ነው።

በተላከልን የመንግስት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ2018 በጀት አመት 10.2% እንደሚያድግ፣ የግብር ገቢ 1.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ 11 ቢሊዮን ዶላር ማስገኘቱ እና የውጭ ቀጥታ ሃዋላ ፍሰት ኢንቨስትመንት 7.7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።

ነገር ግን እነዚህ የቁጥር ስኬቶች የዜጎችን የመኖር እውነታ ፍፁም አይወክሉም፤ እንዲያውም መሬት ካለው እውነታ ጋር በፅኑ ይጋጫሉ። ምክንያቱም የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከገቢያችን ጋር አልተመጣጠነም።

ሪፖርቱ እስከ ግንቦት 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.4፣ የምግብ የዋጋ ግሽበት ደግሞ 15% ደርሷል ይላል።

ይህን ግሽበት ለመደጎም መንግስት 379 ቢሊዮን ብር ማውጣቱ ቢገለፅም በተግባር ግን ባለፉት አመታት የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍል ለከፋ ድህነት በዳረገበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን።

ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ሰማይ የነካ የዋጋ ግሽበት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ሙሉ በሙሉ አሳጥቷል።

ይህንንም ተከትሎ ቋሚ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች፣ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ወገኖቻችን በስውር ረሀብ ውስጥ ወድቀዋል።

የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል።

በሪፖርቱ መረጃ መንግስት በበጀት አመቱ 1.13 ትሪሊዮን ብር ብድር መልቀቁን እና 91% የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው ይላል።

ክቡር የብሄራዊ ባንክ ገዢ እና የፋይናንስ ሚኒስትርም በተደጋጋሚ ላለፉት አመታት መንግስት አንድም ሳንቲም የንግድ ብድር (Commercial Loan) አልተበደረም እያሉ ይናገራሉ።

ይህ የውጭ ንግድ ብድርን ብቻ ነጥሎ በማየት እውነታውን የማደብዘዝ አካሄድ ነው። መንግስትዎ በግምጃ ቤት ሰነድ እና በሀገር ውስጥ እዳ ዋስትናዎች አማካኝነት ከሀገር ውስጥ ባንኮች እና ተቋማት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር እየተበደረ መሆኑን እና ይህም የሀገር ውስጥ እዳ ሸክምን በከፍተኛ ደረጃ እንዳንናረው እና የግሉ ዘርፍ ብድር እንዳጠበበው ለምን ተደበቀ?

በየጊዜው በዚህ ፓርላማ የምናፀድቃቸው በቢሊዮኖች ዶላሮች የሚቆጠሩ የእርዳታ ብድሮች (Concessional Loans) ለምን በሪፖርቱ አይካተቱም? የእዳ ምንጭ እና አይነት መለወጡ እዳ መኖሩን ያስቀራል ወይ?

ሪፖርቱ አሁንም ድረስ ከዩሮ ቦንድ ባለቤቶች ጋር ያለው ድርድር ስላልተጠናቀቀ ሀገሪቱ በከፍተኛ የእዳ ቀውስ ውስጥ ያለች ወይም Debt Distress መሆኗን ይሸሽጋል።

ሌላው የትምህርት እና የማህበራዊ ዘርፍ መውደቅ አለ በሪፖርቱ ላይ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች በመመዝገባቸው በስፋት ቢወራም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 50% እና ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት 8.7% ወይም 50 ሺህ ተማሪዎች ብቻ ናቸው።

ይህም የመንግስትዎ የትምህርት ጥራት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳየን ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከ8.7% የማለፍ ምጣኔ በየትኛውም አለም ታይቶ የማይታወቅ ወይም 92% የመውደቅ ምጣኔ ከፍተኛ የትውልድ ብክነት ወይም Generational Catastrophe ነው።

እኔ የህይወቴን ግማሽ ጊዜ በማስተማር ያሳለፍኩበት በተለያዩ ደረጃዎች እና ኮመን የሚባል አባባል አለ፤ 'መምህሩ ፈተና አውጥቶ ተማሪዎችን ማሳለፍ ካልቻለ እና ከወደቁ የወደቀው መምህሩ ነው' የሚል ኮመን አባባል አለ በእኛ በአስተማሪዎች ዘንድ። እና ይህን ያህል 92% የመውደቅ ምጣኔ ካለ እኔ ወደቋል ብዬ የማስበው ትምህርት ሚኒስቴር ነው።

በዚህ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ውስጥ አልፈው ለምረቃ የበቁ ወጣቶችም የስራ እድል የላቸውም ይባስ ብሎም ወደ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ተማሪዎች አሁንም ድረስ ከትምህርት ገበታቸው ተገልለው ይገኛሉ። ይህ 7 ሚሊዮን አሃዝ ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራት እያንዳንዳቸው ካላቸው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር በላይ መሆኑንም ልብ ይሏል።

ሌላው የሰብአዊ ቀውሶች ትኩረት አለመስጠቱ ነው መንግስትዎ የመረጃ ማጥራት ስራ ሰርቻለሁ በሚል ሰበብ የሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 2.3 ሚሊዮን ወርዷል ይላል።

ነገር ግን መሬት ላይ በጦርነት እና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ፣ የለጋሾች እርዳታ ያጡ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፍጆታ በቂ ምርት የማይያመርቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች እያሉ ይህንን ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎ ማቅረብ ፖለቲካዊ የቁጥር ማሳመር እንጂ የዜጎችን ነባራዊ ህይወት በተጨባጭ የሚያሳይ አይመስለኝም።

እነ WFP፣ FAO፣ Famine Early Warning Network የሚያስቀምጡት ዝቅተኛ ግምት ከ15.8 እስከ 21.4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ ነው " ብለዋል።
#ParliamentQuotes

" ከደመወዙ 35% ግብር ፣ 7% ጡረታ በድምሩ 42% ይቆረጣል። ከ58% ደመወዙ ላይ በእያንዳንዱ በሚሸምተው ሸቀጥ 15% ቫት (VAT) ይቆረጣል። ትራንዛክሽን ላይ ንግድ ባንክ ለሰርቪስና ቫት እያለ ሌሎችም የማይታወቁ ተቆራጮችን ይቆርጣል።  ሰራተኛው ለውሃ፣ ለመብራት ለሌሎችም አገልግሎቶች ይቆረጥበታል። እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ኑሮን መቋቋም አቅቶታልና ለዚህ ታጋሽ ሲቪል ሰርቪስ እና አነስተኛ ኑሮ ላይ ላለው ዜጋ ምን ታስቦለታል ? ከሚመሰርቱት መንግሥት ምን እንጠብቅ ?  " - አቶ ባርጠማ ፍቃዱ
1
አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ

​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።

በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።

​ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።

በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።

​   ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ  በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
3
የቀድሞዉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ተቀበሩ።

አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን የፖለቲካና የኃይማኖት መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ ተቀበሩ።

እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት የካቲት 28 ቀን 2026 ከኻሜኒ ሌላ ሴት ልጃቸዉን፣ የልጅ ልጃቸውን ፣ አማቻቸውንና 11 ባለሥልጣኖቻቸውን ገድለዋል።

ባለቤታቸውም ክፉኛ ቆስለዉ ኋላ ሞተዋል።

የኻሜኒ ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የዚያን ቀን ቆስለዋል።

ሞጅታባሕ ጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ቢይዙም እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ እይታ አልቀረቡም።  ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለአባታቸው በተደረገው የሽኝት ሥርዓትም ሆነ በዛሬው የቀብር ሥርዓት ላይ አልተገኙም።

ኢራንን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ የተቀበሩት በሐገሪቱ ሰሜን-ምሥራቅ ቅዱስ የቀብር ሥፍራ ማሻሐ,ድ ዉስጥ ነዉ። ማሽሐድ የኻሚኔይ የትዉልድ ሥፍራም ናት።

የኻምኔይ አስከሬን ወደ ቀብሩ ስፍራ ከመወሰዱ ከሰዓታት በፊት የአሜሪካ ጦር ርዕሠ-ከተማ ቴሕራንን ከማሻሐድ ከተማ ጋር የሚያገኛኘውን የባቡር መስመር ጨምሮ የተለያዩ የኢራን የመሠረተ-ልማት አውታሮችን አውድሟል።

ይሁንና በቀብር ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር የኢራን ሕዝብ የማሻሐድ ከተማን አጥለቅልቋት ነዉ የዋለዉ። ሕዝቡ የብቀላ ጥሪ ምልክት የሆነውን ቀይ አርማ እያዉለበለበ እስከ ቀብሩ ሥፍራ ድረስ ተጉዟል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም
3
በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ሰራቆ ቀበሌ በግ ሰር'ቆ ሲያ'ርድ በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለው ሌባ መቀጣጫ ሆነ።
ሰ'ርቆ በመግፈፍ ላይ የነበረውን በግ ተሸክ'ሞ ከተማውን እንዲዞር ተደርጓል።
👍5
💔 የአንድ ዘመን እንባ...
አንድ ቀን የዓለምን ስታዲየሞች በጭብጨባ ያናወጡ ሰዎች፣ ዛሬ በዝምታ እንባቸውን እየጠረጉ ይታያሉ።
ሮናልዶ... ሜሲ... ኔይማር...
ሦስቱም በተለያየ ሀገር ተወለዱ፤ በተለያየ መንገድ አደጉ፤ ግን በአንድ ነገር ተመሳሳይ ነበሩ—ለሕዝባቸው የዓለም ዋንጫን ለማምጣት ልባቸውን ሰጥተው ተዋጉ።
ሰዎች ጎላቸውን ያስታውሳሉ፣ እነሱ ግን ያመለጣቸውን ዕድል ያስታውሳሉ።
እነዚህ እንባዎች የሽንፈት አይደሉም... የትልቅ ህልም ዋጋ ናቸው።
ስታዲየሙ ባዶ ይሆናል፤ የደጋፊዎች ጩኸት ይጠፋል፤ መብራቶቹም ይጠፋሉ። የሚቀረው ግን በሣሩ ላይ የወደቁት እንባዎች እና በሚሊዮኖች ልብ ውስጥ የተጻፈው ታሪክ ብቻ ነው።
ጊዜ አዳዲስ ኮከቦችን ያመጣል፤ ነገር ግን ዘመን የሚፈጥሩ ተጫዋቾች በየትውልዱ አንዴ ብቻ ናቸው።
ዛሬ የምናየው የሦስት ተጫዋቾች እንባ አይደለም... የአንድ ትውልድ ትዝታ ቀስ ብሎ ሲዘጋ የምንሰማው የልብ ስብራት ነው። 💔


ለአንድ ትውልድ የማይረሳ ደስታን ሰጣችሁ።
በአስደናቂ ጎሎቻችሁ ዓለምን አስደመማችሁ።
በታሪካዊ ፉክክሮቻችሁ ሚሊዮኖችን አዝናናችሁ።
ለድል ስትታገሉ ላባችሁን አፈሰሳችሁ፤ አንዳንድ ጊዜም እንባችሁን አስመለከታችሁን።
ከሁሉም በላይ ግን፣ ለእግር ኳስ ታሪክ በወርቅ ፊደል የማይጠፋ ምዕራፍ ጻፋችሁ።
እናመሰግናለን...! ❤️
5
የድሮን ጥቃት‼️
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ “በመካነ ሰላም ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በድሮን ጥቃት የመነኮሳት ህይወት አለፈ”‼️

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም በምዕራብ ወሎ በመካነ ሰላም በዓባይ ወንዝ ዳርቻ በሚገኘው ዓባይ ገዳመ አስቀጤስ የሰማእቷ ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ 4:30 አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ምክንያት በገዳሙ ውስጥ የሚኖሩ 2 ሴቶች ወዲያው ህይወታቸው ማለፉን እና ሌሎች መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል።
ምግብ እየሰሩ በነበረበት ወቅት ነው ጥቃት የተፈፀመው ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው በአካባቢው የፋኖ ሀይሎች ከትመዋል በሚል ነው ተብሏል።
ሰላም ለሀገራችን🕊🕊
(አዩዘሀበሻ)
2