የሲጋራ ቁራጭ የጣለ 2000 ብር‼️
በአዲስ አበባ ከተማ የሲጋራ ቁራጭ መንገድ ላይ መጣል 2 ሺህ ብር ያስቀጣል ተባለ።
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሲጋራ ቁራጭ በመንገድ፣ በአደባባይ ወይም በማንኛውም የህዝብ መገልገያ ቦታ ላይ የሚጥል ግለሰብ በ2 ሺህ ብር እንደሚቀጣ ገልጿል።ይህ እርምጃ የከተማዋን ንፅህና፣ የህዝብን ጤና ለመጠበቅ እና የትምባሆ ተጠቃሚነትን ለመቀነስ የሚደረገው የቁጥጥር አካል መሆኑ ተገልጿል።
የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ እንደገለጹት ቅጣቱ የሚተገበረው በከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር 167/2016 መሠረት ነው።ደንቡ የትምባሆ ምርቶችን አጠቃቀም ለመቆጣጠርና ከጭስ ነፃ የሆነ የከተማ አካባቢን ለመፍጠር የወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዳጉ ጆርናል

👍3❤1
የተራራው ላይ ገዢዎች የቢግሆርን በጎች አስደናቂ የተፈጥሮ ሚስጥር
በሰሜን አሜሪካ በሚገኙት እጅግ አስገራሚና አስፈሪ ተራራማ ገደላማ ቦታዎች ላይ ተፈጥሮን ተቋቁመው የሚኖሩት ቢግሆርን በጎች የጽናትና የጥንካሬ ትልቅ ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ እንስሳት ስማቸውን ያገኙት በጭንቅላታቸው ላይ ካለውና እስከ አስራ አራት ኪሎ ግራም ሊመዝን ከሚችለው ግዙፍና የተጠማዘዘ ቀንዳቸው ሲሆን ይህ ቀንድ በየዓመቱ የማይረግፍና ዕድሜ ልካቸውን አብሮአቸው የሚያድግ ልዩ አካላቸው ነው። በዓለታማና ቁልቁል በሆኑ ገደሎች ላይ ሳይንሸራተቱ ፍጥነት ጨምረው እንዲሮጡና እንዲዘልሉ የረዳቸው ደግሞ ውጫዊው ክፍል ጠንካራ ውስጠኛው ደግሞ እንደ ስፖንጅ የሚለጠጥ ተፈጥሮአዊ ሰኮናቸው ነው። በተለይም በመኸር ወቅት አውራዎቹ የበላይነታቸውን ለማሳየትና ጥንካሬአቸውን ለማስመስከር እርስ በርስ የሚያደርጉት የራስ በራስ ግጭት እጅግ አስገራሚ ሲሆን በሰዓት እስከ አርባ ስምንት ኪሎ ሜትር በሚደርስ ፍጥነት ሲጋጩ የሚፈጠረው ድምፅ በተራራው ላይ እስከ አንድ ነጥብ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ድረስ ያስተጋባል። ይህንን ኃይለኛ ግጭት ያለ ምንም የመደንገጥ ወይም የአንጎል ጉዳት የሚቋቋሙት የራስ ቅላቸው ድርብርብ አጥንትና ልዩ የሆነ አስደንጋጭ መከላከያ ፈሳሽ በውስጡ ስላለው ነው። ሴቶቹና ግልገሎቹ በትላልቅ መንጋዎች ተከታትለው በሚኖሩበት የተራራማው ዓለም ውስጥ እነዚህ እንስሳት ከአንድ ነጥብ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለን ማንኛውንም እንቅስቃሴ መለየት የሚያስችል ጥራት ያለው እይታ ያላቸው ሲሆን ይህም ካሉባቸው እንደ ተኩላና ተራራ አንበሳ ካሉ አዳኞች በቀላሉ እንዲያመልጡ ትልቅ እገዛ ያደርግላቸዋል። በአንድ ወቅት በከፍተኛ አደን እና በበሽታዎች ምክንያት ቁጥራቸው ተመናምኖ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በተደረጉ ጥብቅ የጥበቃ ስራዎች በተራራው ላይ በነፃነት መኖራቸውን ቀጥለዋል።

❤1
በ #ሱዳን በተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ከፍተኛ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣የ #ኢትዮጵያ እና የቀጠናው ባለሥልጣናት ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲደረግ ተጠየቀ‼️
ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች እና የሕግ ድርጅቶች ጥምረት፤ በሱዳን ዳርፉር ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ለተፈጸሙ አስከፊ ወንጀሎች ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ረገድ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ፣ የኢትዮጵያን ጨምሮ የቻድ፣የሶማሊያ፣ የሊቢያ እና የኬኒያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያደርግ ጠየቀ።
ሚድል ኢስት አይ ባወጣው ዘገባ መሠረት፤ ይህ ጥሪ ሰኞ ዕለት የቀረበው፤ ራውል ዋለንበርግ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል (RWCHR) ከተለያዩ የሕግ፣ የምርመራ እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጥምረት ጋር በመሆን የቀረበ ነው። አቤቱታው የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዓቃቢያነ ሕግ የውጭ አገር ባለሥልጣናትና አሸማጋዮች በሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተፈጸሙ ወንጀሎችን ሆን ብለው በማገዝ ወይም በማበረታታት ረገድ የተሳተፉ መሆኑን እንዲመረምሩ ይጠይቃል።

" የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
የፓርላማ አባሉ ደሳለኝ ጫኔ(ዶ/ር) ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።
ደሳለኝ (ዶ/ር) "ላለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ የከፈለው ዋጋ እጅግ የበዛ እና ከባድ ነው እርሶ ስልጣን ላይ ሲቀመጡ የገቡት የሰላም እና የብልጽግና ቃልኪዳን ነበር በተግባር ያየነው ተገላቢጦሹን ነው" በማለት ጠንከር ያለ ትችት ሰንዝረዋል።
"የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ያስከተለው አስከፊ ሰብአዊ ውድመት እና ጠባሳ ሳይሽር ዛሬም በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በሌሎችም አካባቢዎች የሚታዩት ቀጣይነት ያላቸው ግጭቶች እና ጦርነቶች፣ ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር ጥቃቶች፣ እገታዎች እና አለመረጋጋቶች የዜጎችን የመኖር መብት ነፍገዋል" ሲሉም አክለዋል።
በቅርቡም "ከትግራይ እና ከኤርትራ ሀይሎች ጋር የሌላ ጦርነት ስጋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል" ሲሉም ጉዳዩ የደረሰበትን አሳሳቢነት ጠቁመዋል።
በዝርዝር ባቀረቡት ጥያቄ ምን አሉ ?
" በፖለቲካው መስክ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበብ፣ የሀገራዊ ተቃርኖዎች መስፋት ወይም Political Polarization፣ የሲቪክ ማህበራት መኮስመን፣ በጋዜጠኞች እና በሚዲያዎች ላይ እገዳዎች እና ክልከላዎች ዜጎች አማራጭ ድምፅ እንዳያሰሙ አፍነዋቸዋል።
በርካታ የፖለቲካ እስረኞችም ህገ-መንግስታዊ የፍትህ ዋስትና ተነፍገው ይገኛሉ። ይህ አጠቃላይ የሰላም፣ የፀጥታ እና የፖለቲካ ውድቀት የፓርቲዎ የተሳሳተ ፖለቲካዊ ፍልስፍና ውጤት፣ አንድነትን በተግባር ማምጣት ያቃተው የመደመር ትረካ መዋቅራዊ ስብራት ውጤት ነው።
መንግስት የችግሮቹን ስር መሰረት ትቶ ምልክቶቹን ብቻ የመቀጥቀጥና እና በቁጥር ጨዋታ ህዝብን የማደናገር አካሄድ እየተከተለ ነው።
በተላከልን የመንግስት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ2018 በጀት አመት 10.2% እንደሚያድግ፣ የግብር ገቢ 1.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱ፣ የሸቀጦች ወጪ ንግድ 11 ቢሊዮን ዶላር ማስገኘቱ እና የውጭ ቀጥታ ሃዋላ ፍሰት ኢንቨስትመንት 7.7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ተገልጿል።
ነገር ግን እነዚህ የቁጥር ስኬቶች የዜጎችን የመኖር እውነታ ፍፁም አይወክሉም፤ እንዲያውም መሬት ካለው እውነታ ጋር በፅኑ ይጋጫሉ። ምክንያቱም የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ከገቢያችን ጋር አልተመጣጠነም።
ሪፖርቱ እስከ ግንቦት 2018 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 13.4፣ የምግብ የዋጋ ግሽበት ደግሞ 15% ደርሷል ይላል።
ይህን ግሽበት ለመደጎም መንግስት 379 ቢሊዮን ብር ማውጣቱ ቢገለፅም በተግባር ግን ባለፉት አመታት የተተገበረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ዝቅተኛውን የማህበረሰብ ክፍል ለከፋ ድህነት በዳረገበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን።
ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ሰማይ የነካ የዋጋ ግሽበት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ሙሉ በሙሉ አሳጥቷል።
ይህንንም ተከትሎ ቋሚ ደሞዝ የሚከፈላቸው የመንግስት እና የግል ድርጅቶች ሰራተኞች፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የከተማ ነዋሪዎች፣ አነስተኛ ነጋዴዎች፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ወገኖቻችን በስውር ረሀብ ውስጥ ወድቀዋል።
የቤት ኪራይ ከአብዛኛው ዜጎቻችን ወርሃዊ ገቢ በላይ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን መካከለኛ የሚባል የህብረተሰብ መደብ ጠፍቶ ጥቂት እጅግ የበለፀጉ እና አብዛኛው በድህነት የሚማቅቅ ሁለት መደቦች ሆነዋል።
በሪፖርቱ መረጃ መንግስት በበጀት አመቱ 1.13 ትሪሊዮን ብር ብድር መልቀቁን እና 91% የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ ነው ይላል።
ክቡር የብሄራዊ ባንክ ገዢ እና የፋይናንስ ሚኒስትርም በተደጋጋሚ ላለፉት አመታት መንግስት አንድም ሳንቲም የንግድ ብድር (Commercial Loan) አልተበደረም እያሉ ይናገራሉ።
ይህ የውጭ ንግድ ብድርን ብቻ ነጥሎ በማየት እውነታውን የማደብዘዝ አካሄድ ነው። መንግስትዎ በግምጃ ቤት ሰነድ እና በሀገር ውስጥ እዳ ዋስትናዎች አማካኝነት ከሀገር ውስጥ ባንኮች እና ተቋማት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር እየተበደረ መሆኑን እና ይህም የሀገር ውስጥ እዳ ሸክምን በከፍተኛ ደረጃ እንዳንናረው እና የግሉ ዘርፍ ብድር እንዳጠበበው ለምን ተደበቀ?
በየጊዜው በዚህ ፓርላማ የምናፀድቃቸው በቢሊዮኖች ዶላሮች የሚቆጠሩ የእርዳታ ብድሮች (Concessional Loans) ለምን በሪፖርቱ አይካተቱም? የእዳ ምንጭ እና አይነት መለወጡ እዳ መኖሩን ያስቀራል ወይ?
ሪፖርቱ አሁንም ድረስ ከዩሮ ቦንድ ባለቤቶች ጋር ያለው ድርድር ስላልተጠናቀቀ ሀገሪቱ በከፍተኛ የእዳ ቀውስ ውስጥ ያለች ወይም Debt Distress መሆኗን ይሸሽጋል።
ሌላው የትምህርት እና የማህበራዊ ዘርፍ መውደቅ አለ በሪፖርቱ ላይ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች በመመዝገባቸው በስፋት ቢወራም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 50% እና ከዚያ በላይ ማምጣት የቻሉት 8.7% ወይም 50 ሺህ ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
ይህም የመንግስትዎ የትምህርት ጥራት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳየን ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ከ8.7% የማለፍ ምጣኔ በየትኛውም አለም ታይቶ የማይታወቅ ወይም 92% የመውደቅ ምጣኔ ከፍተኛ የትውልድ ብክነት ወይም Generational Catastrophe ነው።
እኔ የህይወቴን ግማሽ ጊዜ በማስተማር ያሳለፍኩበት በተለያዩ ደረጃዎች እና ኮመን የሚባል አባባል አለ፤ 'መምህሩ ፈተና አውጥቶ ተማሪዎችን ማሳለፍ ካልቻለ እና ከወደቁ የወደቀው መምህሩ ነው' የሚል ኮመን አባባል አለ በእኛ በአስተማሪዎች ዘንድ። እና ይህን ያህል 92% የመውደቅ ምጣኔ ካለ እኔ ወደቋል ብዬ የማስበው ትምህርት ሚኒስቴር ነው።
በዚህ ሁሉ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ውስጥ አልፈው ለምረቃ የበቁ ወጣቶችም የስራ እድል የላቸውም ይባስ ብሎም ወደ 7 ሚሊዮን የሚደርሱ ተማሪዎች አሁንም ድረስ ከትምህርት ገበታቸው ተገልለው ይገኛሉ። ይህ 7 ሚሊዮን አሃዝ ከ20 በላይ የአፍሪካ ሀገራት እያንዳንዳቸው ካላቸው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር በላይ መሆኑንም ልብ ይሏል።
ሌላው የሰብአዊ ቀውሶች ትኩረት አለመስጠቱ ነው መንግስትዎ የመረጃ ማጥራት ስራ ሰርቻለሁ በሚል ሰበብ የሰብአዊ ድጋፍ ፈላጊዎች ቁጥር ከ27 ሚሊዮን ወደ 2.3 ሚሊዮን ወርዷል ይላል።
ነገር ግን መሬት ላይ በጦርነት እና በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ፣ የለጋሾች እርዳታ ያጡ፣ ለቤተሰቦቻቸው ፍጆታ በቂ ምርት የማይያመርቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች እያሉ ይህንን ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ አድርጎ ማቅረብ ፖለቲካዊ የቁጥር ማሳመር እንጂ የዜጎችን ነባራዊ ህይወት በተጨባጭ የሚያሳይ አይመስለኝም።
እነ WFP፣ FAO፣ Famine Early Warning Network የሚያስቀምጡት ዝቅተኛ ግምት ከ15.8 እስከ 21.4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የምግብ እጥረት ውስጥ እንደሚገኙ ነው " ብለዋል።

#ParliamentQuotes
" ከደመወዙ 35% ግብር ፣ 7% ጡረታ በድምሩ 42% ይቆረጣል። ከ58% ደመወዙ ላይ በእያንዳንዱ በሚሸምተው ሸቀጥ 15% ቫት (VAT) ይቆረጣል። ትራንዛክሽን ላይ ንግድ ባንክ ለሰርቪስና ቫት እያለ ሌሎችም የማይታወቁ ተቆራጮችን ይቆርጣል። ሰራተኛው ለውሃ፣ ለመብራት ለሌሎችም አገልግሎቶች ይቆረጥበታል። እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ኑሮን መቋቋም አቅቶታልና ለዚህ ታጋሽ ሲቪል ሰርቪስ እና አነስተኛ ኑሮ ላይ ላለው ዜጋ ምን ታስቦለታል ? ከሚመሰርቱት መንግሥት ምን እንጠብቅ ? " - አቶ ባርጠማ ፍቃዱ

አቶ ደሳለኝ ጫኔ ከቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ
ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ታዋቂው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ አቶ ደሳለኝ ጫኔ፣ የፓርላማ ቆይታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ከማንኛውም ቀጥተኛ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መውጣታቸውን በይፋ ገለጹ።
በትናንትናው ዕለት የምክር ቤቱ ዘመን ማክተሙን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አቶ ደሳለኝ፣ ለጊዜው በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ በአባልነትም ሆነ በደጋፊነት እንደማይሳተፉ አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲ መምህርነት እና በሲቪክ ማኅበራት መሪነት ያገለገሉት ምሁር ፣ ባለፉት ስምንት ዓመታት በፖለቲካ አመራርነት እንዲሁም የባሕር ዳር ከተማ መራጮችን በመወከል በፓርላማ በንቁ ተቃዋሚነት አገልግለዋል።
በዚህ ጉዟቸው ወቅትም ለ45 ቀናት መታሰራቸውን ጠቅሰዋል።
ከ10 ዓመታት የፖለቲካ ድካም መልስ ወደ ግሉ ዘርፍ በመግባት በሙያቸው ሀገርን ለማገልገልና ለቤተሰባቸው ጊዜ ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
ከተቃውሞ ፖለቲካው ቢወጡም፣ በሀገራዊ የሰላም እና የብሔራዊ ውይይት ጉዳዮች ላይ በሙያቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

❤3
የቀድሞዉ የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ተቀበሩ።
አሜሪካ እና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን የፖለቲካና የኃይማኖት መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ ተቀበሩ።
እስራኤልና አሜሪካ በኢራን ላይ ጦርነት በከፈቱበት ዕለት የካቲት 28 ቀን 2026 ከኻሜኒ ሌላ ሴት ልጃቸዉን፣ የልጅ ልጃቸውን ፣ አማቻቸውንና 11 ባለሥልጣኖቻቸውን ገድለዋል።
ባለቤታቸውም ክፉኛ ቆስለዉ ኋላ ሞተዋል።
የኻሜኒ ሥልጣን የያዙት ያሁኑ የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ የዚያን ቀን ቆስለዋል።
ሞጅታባሕ ጠቅላይ መሪነቱን ሥልጣን ቢይዙም እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ እይታ አልቀረቡም። ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለአባታቸው በተደረገው የሽኝት ሥርዓትም ሆነ በዛሬው የቀብር ሥርዓት ላይ አልተገኙም።
ኢራንን ከ30 ዓመታት በላይ የመሩት ዓሊ ኻሜኒ ዛሬ የተቀበሩት በሐገሪቱ ሰሜን-ምሥራቅ ቅዱስ የቀብር ሥፍራ ማሻሐ,ድ ዉስጥ ነዉ። ማሽሐድ የኻሚኔይ የትዉልድ ሥፍራም ናት።
የኻምኔይ አስከሬን ወደ ቀብሩ ስፍራ ከመወሰዱ ከሰዓታት በፊት የአሜሪካ ጦር ርዕሠ-ከተማ ቴሕራንን ከማሻሐድ ከተማ ጋር የሚያገኛኘውን የባቡር መስመር ጨምሮ የተለያዩ የኢራን የመሠረተ-ልማት አውታሮችን አውድሟል።
ይሁንና በቀብር ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት በመቶ ሺሕ የሚቆጠር የኢራን ሕዝብ የማሻሐድ ከተማን አጥለቅልቋት ነዉ የዋለዉ። ሕዝቡ የብቀላ ጥሪ ምልክት የሆነውን ቀይ አርማ እያዉለበለበ እስከ ቀብሩ ሥፍራ ድረስ ተጉዟል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
ሃምሌ 2 ቀን 2018 ዓ/ም

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ሰራቆ ቀበሌ በግ ሰር'ቆ ሲያ'ርድ በህብረተሰቡና በፀጥታ ሀይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለው ሌባ መቀጣጫ ሆነ።
ሰ'ርቆ በመግፈፍ ላይ የነበረውን በግ ተሸክ'ሞ ከተማውን እንዲዞር ተደርጓል።

👍5