Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
18.6K subscribers
7.14K photos
104 videos
73 files
682 links
Government Organization
Download Telegram
በግንባታ ሳይቶች ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው የማህበራቱ አስደናቂ የመፈፀም አቅም፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ስራዎችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት ሰጥቶ ልዩ ክትትል እያደረገና ማሕበራቱም የተሰጣቸውን ድርብ ኃላፊነት በመወጣት ሀገራቸውንም እራሳቸውንም እየጠቀሙ ይገኛል፡፡

በዚህ ረገድ የማሕበራትን ቀደምት ስም የሚሽሩና አዲስ እይታን የሚፈጥሩ ውጤቶች በየግንባታ ሳይቱ እጠየተስተዋሉ ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያ በ3ር ከ15 ቀናት ጊዜያት ብቻ 96 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ የደረሰው የየካ ወረዳ 10 ሳላይሽ የመጀመሪያ ደረጃ G+4 ት/ቤት ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ፕሮግራም ተጠቃሚ በሆኑት አቻ ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እና ሲጫሌ ብሩክ እና ጓደኞቻቸው አማካሪ ማህበር አማካሪነት እንዲገነባ ከቢሮው ውል የታሰረለት ፕሮጀክቱ ከውለታ ጊዜው ቀድሞ ለመጠናቀቅ የሚያስችለው ቁመና ላይ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

በግንባታ ሳይቱ የሚቀሩትን የውስጥ ቀለም ስራ፣ የኤሌክትሪክ ፊቲንግ ገጠማ እና የደረጃ ማርብል ስራዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዕድሜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ በሁለት ፈረቃ እየተሰራ እንደሚገኝ የሚጠቅሱት የማሕበሩ ስራ አስኪያጅ ድርጅታቸው ይህንን ለማድረግ የሚያስችል በቂ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

120 ቀናት የማጠናቀቂያ ዕድሜ ተሰጥቶት ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የመስታወት ገጠማ፣የኮርኒስ ጂፕሰም ስራ እንዲሁም የሴራሚክ ስራዎች እየተጠናቀቁለት ይገኛል፡፡……..
……….የአዲስ አበበ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 11/2015


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
#ዜና_እረፍት


የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባልደረባ ሆነው ለበርካታ ዓመታት ተቋሙን ሲያገለግሉ የቆዩትና ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ደግሞ በመሰረተልማት ቅንጅት፣ግንባታ ፍቃድባ ቁጥጥር ባለስልጣን ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ቲመርጋ አግዛ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በቀድሞ የስራ ባልደረባቸው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው መፅናናትን ይመኛሉ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የተመራ ከፍተኛ አመራር ቡድን በክፍለከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት እያስገነባቸው የሚገኙ ዘጠኝ ማሕበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተካሂዷል፡፡

የክፍለከተማው የካቢኔ አባላትን፣የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን፣ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን፣የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የፓርቲ ኃላፊዎችን ባካተተውና በክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የተመራው የዚህ የመስክ ምልከታ ዓላማ አመራሩ በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አውቆና በፕሮጀክቶቹ ላይ ያሉ ችግሮችን ተረድቶ መፍትሄ በመስጠት ሂደቱ ላይ የራሱን አበርክቶ እንዲያሳርፍ ዕድል ከመፍጠሩም ሌላ በበጀት ድልድል ወቅት የእነዚህን ፕሮጀክቶች አንገብጋቢነት ተረድቶ የአመራሩን በቂ ትኩረት እንዲያገኝ አስቻይ አጋጣሚን ይፈጥራል ሲሉ የክፍለከተማው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ኃላፊው ኢ/ር ስንታየሁ ማሞ አስረድተዋል፡፡

የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የመስክ ምልከታውን ሲያጠቃልሉ እንዳሉት ምልከታ ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የወረዳ 12 ወጣት ማዕከል ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀሞችን አድንቀው በዛሬው ዕለት ምልከታ የተደረገባቸው አጠቃላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የታለመላቸውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁሉም አመራር በባለቤትነት ይዞ ማስፈፀም እንደሚገባው አደራ ሰጥተው ይህም በጋራ የመምራታችን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡…….
……..በመስክ ምልከታው የወረዳ 05 ስፖርት ሜዳ፣ቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ፣ የወረዳ 08 ፖሊስ ጣቢያ፣የህዳሴ ሲኒማ አዳራሽ ጥገና፣የወረዳ 01 ማኑፋክቸሪንግ ሼዶች፣የወረዳ 01 ደረቅ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ፣ኤላ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት፣አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የወረዳ 12 ወጣት ማዕከል ፕሮጀክቶች ተካተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 13/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg