4ኛው ከተማ-ዓቀፍ የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብር በአዲስ አበባ በይፋ ተጀመረ፡፡
ከተማችንን አረንጓዴ የማልበስ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በደማቅ ሁኔታ በይፋ የተጀመረ ሲሆን በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አገኘው ተሻገር፣ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙን ጨምሮ የፌደራልና የከተማ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
እንደከተማ ይተከላሉ ተብሎ በዕቅድ ከተያዙ 7.4 ሚሊዮን ችግኞች መካከል የጥላና የውበት ዛፎች እያንዳንዳቸው 40 በመቶውን የሚይዙ ሲሆን ቀሪውን 20 በመቶ ፍራፍሬ እንደሚይዝ በስነስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
በመርኃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳሉት የሁላችንም መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግና የአረንጓዴ አሻራውን ዕቅድ ለማሳካት ይችል ዘንድ መትከል ብቻ በቂ ስላልሆነ ሁሉም የከተማው ህብረተሰብ የተተከሉትን ችግኞች በባለቤትነትና በኃላፊነት ተንከባክቦ ማቆየት እንደሚገባው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
#አሻራችንን_ለትውልዳችን !!!!!! #ኑ_አዲስ_አበባን_እናልብሳት !!!!!
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 21/2014 ዓ/ም

የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በእንጦጦ ፓርክ ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አሳረፉ፡፡
አራተኛው ሀገር-ዓቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብርን ተከትሎ የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በተዘጋጀላቸው ስፍራ 5,000 ሀገር በቀል የዛፍ እና የጥላ ችግኞች ተክለዋል፡፡
የችግኝ ተከላውን ያስጀመሩት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊዋ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት ቢሮው በአዋጅ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት በተጨማሪ ይሄንና መሰል ሀገራዊና ማህበራዊ ጥሪዎችን ተቀብሎ በፍጥነት ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው እንደዜጋ ዛሬ የምንተክለው ችግኝ ነገ ላይ በስነምህዳሩ ላይ የሚኖረውን አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደመሀንዲስ ተረድተንና ችግኝ መትከልን ባህላችን በማድረግ አዲስ አበባችንን ውብ እና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የበኩላችንን እንወጣ ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰኔ 23/2014 ዓ/ም

የሀገር ፍቅር ቴአትርን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ዕድሳቱን አጠናቆ በማስረከብ መልካም ስም ያተረፈው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የራስ ቴአትርን መልሶ ግንባታ ፕሮጀክት ለማስፈፀም ከከተማ አስተዳደሩ በሀላፊነት ተረክቧል።
የራስ ቴአትር መልሶ ግንባታ ፕሮጀክትን ለማስጀመር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
ጥበብ ሀገርን የመገንባትና ትውልድን የማነፅ ትልቅ ፋይዳ እንዳላት የገለፁት ከንቲባዋ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ብቻም ሳይሆን ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።
ቤተ-ተውኔቱ ታሪካዊ ይዘቱን ሳይቀይር በዘመናዊ መልኩ አጠናቆ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊነቱን ተረክቧል።
ቢሮው በቅርቡ የሀገር ፍቅር ቴአትር ዕድሳትን ከማጠናቀቁም ባለፈ በተለያዩ ምክንያቶች ግንባታው ተጓቶ የነበረውን የህፃናትና ወጣቶች ቴአትርን በቅርቡ ለማጠናቀቅ በትጋት እየሰራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰኔ 25/2014 ዓ/ም

የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ፣ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በስሩ የሚገኙ ኮሌጆችን በማስተባበር በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ 42 አቅመ ደካሞች ቤት ለማደስ በዛሬው ዕለት አቧሬ አካባቢ የእድሳት መርሃ ግብሩን አስጀምሯል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ኃብተማሪያምን ጨምሮ ሌሎች የካቢኔ አባላት ተገኝተው የቤት እድሳቱን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም