ቢሮው የክፍለከተማ ፅ/ቤቶችን የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስሩ የሚገኙትን የክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ፅ/ቤቶችን የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡
የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አስራ አንዱም የክፍለከተማ ፅ/ቤት ሀላፊዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ ፅ/ቤቶቹ በጊዜ ማዕቀፉ የነበራቸው የዕቅድ አፈፃፀም ስኬቶችና ተግዳሮቶች ቀርበው ግምገማ ተደርጎባቸዋል፡፡
የግምገማ መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም የግምገማውን አስፈላጊነት አብራርተው በቀጣይም ሊከናወኑ የሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ የስራ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን በተለይ በማዕከል እንዲሁም በክፍለከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የተለየና ሊያሰራ የማያስችል ሁኔታ እስካልተፈጠረ ድረስ በማንኛውም መልኩ ወደሚቀጥለው በጀት ዓመት መሻገር እንደሌለባቸውና በተያዘላቸው የጊዜ መርኃ-ግብር መሰረት መጠናቀቅ እንደሚገባቸው አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የካቲት 19/2014 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity

✍️በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ የተገነባውን በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድጂታል ቤተመጻሕፍት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ በተገኙበት ለአገልግሎት ክፍት አደረገ ።
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ አስተዳደር ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ያስገነባውን ደጂታል ቤተመጻሕፍት የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻል በዛሬው ዕለት በአካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች ለንባብ ክፍት እንዲሆን አደረገ
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይና ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አያልነሽ ሐብተማርያም በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ላይብረሪው ተዘዋውረው በመመልከት ብቁ መሆኑን በማረጋገጥ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ በመረሐ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ላይብረሪው ከዚህ ቀደም በከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መመረቁን አስታውሰው በፍጥነት አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረግልን የሚል ጥያቄ ከአካባቢው ሕዝብ መነሳቱን እንዲሁ ጨምረው ገልጸው በጥያቄው መሠረት እሳቸውም አስፈላጊ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተሟልተው ላይብረሪውን ለማስጀመር ቃል ገብተው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር በዚሕ መልኩ አገልግሎት እንድናስጀምር ስለደገፉን በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስም ልናመሰግናቸው እንወዳለን ብለዋል።
በዚሕም መሠረት ሲነን የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ የተቀናጀ የማሕበረሰብ አገልግሎት መስጪያ ግብረ ሰናይ ድርጅቶትና መሠል ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ቤተመጽሐፍቱ አገልግሎት እንዲሰጥ የበኩላቸውን በጎ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል።
ዘገባው የላፍቶ ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት ነው

በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ሲሰጥ የቆየው የዓቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ.ከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ይህ የአሰልጣኞች ስልጠና ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ መስተዳደሮች ለተውጣጡ 129 የኮንስትራክሽን ባለሞያዎች እንዲሁም የቴክኒክና ሞያ መምህራን ላለፉት 5 ቀናት masonry,electrical and sanitary installation ዙሪያ እየተሰጠ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለትም እንደሚጠናቀቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ስልጠናው በሀገራዊ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አነስተኛና መለስተኛ ባለሞያዎች ላይ ሊስተዋሉ የሚችሉ የክህሎት እና የፅንሰ-ኃሳብ ክፍተቶችን መሙላት የሚችሉ አሰልጣኞችን ለማፍራት ታስቦ የተዘጋጀ የዓቅም ግንባታ ስልጠና ሲሆን ኢንዱስትሪውን በሳይንሳዊና ዘመኑ በሚጠይቀው የፅንሰ-ሀሳብ እንዲሁም የክህሎት ደረጃ ለመምራት የሚያስችል አቅም ከማዳበርም ባለፈ በዘርፉ ተወዳዳሪ የሰው ኃይል መፍጠር ያስችላል ተብሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱና ኢንስቲትዩቱ በጋራ ባዘጋጁት በዚህ ስልጠና ላይ ከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የተለያዩ የስራ ክፍሎች እና በስሩ ከሚገኙ የክፍለከተማ ፅ/ቤቶች የተውጣጡ 20 የዘርፉ ባለሞያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የካቲት 25/2014 ዓ/ም