Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.3K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በቦሌ ክፍለከተማ የተገነቡ ፕሮጀክቶች በይፋ ተመረቁ፡፡

የቦሌ ክፍለከተማ በበጀት ዓመቱ ሲያከናውናቸው የቆዩ 65 የልማት ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት በከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በይፋ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከተማ አስተዳደሩ በጀት መድቦላቸው በክፍለከተማው ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ክትትል የተከናወኑ 41 ካፒታል ፕሮጀክቶችን ጨምሮ 24 በሕብረተሰቡ ተሳትፎ የተከናወኑ ግንባታዎች የሚገኙበት ሲሆን በአጠቃላይ ወጪያቸውም ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሆነ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ ከተመረቁ ፕሮጀክቶች ውስጥ ትምህርት ቤቶች፣ጤና ጣቢያዎች፣የፖሊስ ማዕከላት የአስተዳደር ህንፃዎችና የወጣት ስብዕና ግንባታ ማዕከላት ይገኙበታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 13/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍42
የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያከናወናቸው ከሚገኙ የጤና መሰረተ-ልማት ግንባታዎች መካከል የሚጠቀሰውና በቂርቆስ ክፍለከተማ ወረዳ 11 እየተገነባ የሚገኘው የቂርቆስ 2B+G+4 ጤና ጣቢያ 43 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ግንባታ ማማከር ድርጅት በአማካሪነት እንዲሁም ፍቃዱ ሙላቱ ህ/ስ/ተቋራጭ በስራ ተቋራጭነት የሚያከናውኑት ይህ የጤና ጣቢያ ግንባታ ከ247 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለት ሲሆን በተቀመጠለት የውለታ ጊዜ ማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ ሶስቱም አካላት በቅርበት እየሰሩ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ በግንባታ ሳይቱ የአራተኛ ወለል ፎርም ወርክ ስራ ተጠናቆ ለአርማታ ሙሌት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የብረት ስራ እንዲሁም የቤዝመንት ዎል እና ብሎክ ልስን ስራዎች ጎንለጎን እየተሰሩ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 13/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍31
የአለም ብርሀን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ባደረጋቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋራጭና አማካሪ ኢንተርፕራይዞች እየተገነቡ የሚገኙት የትምህርት ቤት ግንባታዎች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ፡፡

ከነዚህ ግንባታዎች ውስጥ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 01 ዓለም ብርሀን የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የተገነባው ባለ 5 ወለል የማስፋፊያ ህንፃ ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ ተደርጓል፡፡

ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ ገንዘብ የተያዘለትና በኤፍ.ቲ.ኤፍ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በሳሙኤል አብረሀም እና ጓደኞቻቸው ሕ/ሽ/ማ አማካሪነት ግንባታው የተከናወነው ይህ የት/ቤት ማስፋፊያ ፕሮጀክት 100 % የተጠናቀቀ ሲሆን ለሚቀጥለው የት/ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገድ የክፍለከተማውን የት/ት ሽፋን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 13/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍123
በቢሮው እየተገነቡ ከሚገኙና በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ከደረሱ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግንባታ።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 15/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍62👎1
#የጨረታ_ማስታወቂያ

ተቋማችን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ #የህትመት እንዲሁም #የሆቴል_መስተንግዶ አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
👍7👏1