Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.3K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙንኬሽን ቢሮ አስተባባሪነት #ነገን_ዛሬ_እንትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተተገበረ ።



በመርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግርና የእንኳ ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ኮሙንኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ እናት ዐለም መለስ " ዛሬ ቢሮው በላቀ አስተባባሪነት 10ሺህ ችግኞች እንደሚተከል ጠቁመው በከተማ ደረጃ ያቀድነውን እናሳካለን ብለዋል ።

በፊታችን ሰኞም አሻራችንን ለማኖር በሀገር አቀፍ ጥሪው በየደረጃችን ሚናችንን እንድንወጣ የአደራ መልዕክቴን አስተላልፋለው ሲሉ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ እናት ዐለም መለስ ተናግረዋል

በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አረንጓዴ ልማትና ውበት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጀማሉ ጀንበር በበኩላቸው "ከተማችንን ብሎም ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ልማት የማልበስ ተግባራችን ተጠናክሮ ቀጥሏል በመሆኑም በዛሬው ዕለት " ነገን ዛሬ እንትከል " መርሀ ግብር ላይ የምትሳተፉ ታዋቂ ሰዎች ፣ አርቲስቶች ፣ የኮሙንኬሽን መዋቅሩ ሰራተኞች ፣ የሚዲያ ተቋማት ሀላፊዎችና ጥሪ የደረገላችው ሁሉ እንኳን ደህና መጣችው ብለዋል ።

የፊታችን ሰኞ መጋቢት 10 በመላው ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ ለዚህም ስኬት አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን በነቂስ ታሳትፋለች ።
👍63
እንዴት አደርሽ አዲስ አበባ!
ነገን ዛሬ እንትከል ተጀመረ!

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን ሪከርድ የሚሰብርበት ዕለት!!

ዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500ሚሊዮን ችግኞች የሚተከሉበት እለት ነው!!
ይህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ነው!!

ዛሬ በጋራ ታሪክ እንሰራለን!!!
500ሚሊዮን  የ#አረንጓዴዐሻራ ችግኞችን እንተክላለን!
👍4👎42
የቢሮው አመራርና ሰራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን እያሳረፉ ነው፡፡

በአንዲት ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ታላቁን ሀገራዊ ትልም ለማሳካት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሰራተኞች ከንጋት ጀምሮ በችግኝ ተከላው ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ሰኔ 30/2015 ዓ/ም 5,000 ችግኞችን በመትከል የተጀመረው የዘንድሮው የቢሮው የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብር በዛሬው ሀገራዊ ዘመቻ 15,000 ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ውጥን ቀጥሎ ውሏል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 05 በተካሄደው በዚህ ታላቅ መርኃ-ግብር ላይከአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በተጨማሪ የወረዳው አመራርና ሰራተኞች ፣የወረዳው ነዋሪዎች የሀይማኖት አባቶች፣ህፃናትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 10/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7
በአንዲት ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ ውጥን በኢትዮጵያ ልጆች ግቡን በመምታት ዕለቱ ዓለም የሚነጋገርበትና ቀጣዩ ትውልድ በክብር የሚያወሳው ታላቅ ቀን ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል።በዚህ ታሪካዊ ተግባር ለተሳተፋችሁ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ /እንኳን ደስ ያለን።


ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም

(የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ኃላፊ )


#አረንጓዴ_አሻራ
#በአንዲት_ጀምበር_500_ሚሊዮን_ችግኞች
#ነገን_ዛሬ_እንትከል
🙏5👍3👎1
በአንዲት ጀምበር 500 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርኃ-ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 06 እንዲሁም ወረዳ 04 ተገኝተው አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።



#አረንጓዴ_አሻራ
#በአንዲት_ጀምበር_500_ሚሊዮን_ችግኞች
#ነገን_ዛሬ_እንትከል
👌4👍3👎1