Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.3K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በወጣቶችና ህፃናት እንዲሁም በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።
--------
በ"የመደመር ትውልድ" መፅሀፍ ሽያጭ ከተገነቡ 7 የወጣቶችና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት አንዱ የሆነውና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የተገነባው ፈረንሳይ ለጋሲዮን ስፓርት ሜዳ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ማዕከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት፣ የብልፅግና መንግስት የዛሬና የነገው ትውልድ አካል እንደመሆኑ ወጣቶችና ህፃናት የአዕምሮ፣ የአካልና የስብእና መገንቢያ ስፍራዎችን የሚገነባው ለሀገር ተረካቢ ህፃናትና ወጣቶች ልዩ ትኩረት ከመስጠቱ የመነጨ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
3
በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተመረቁ።

በክፍለ ከተማው ወ/ 2 በ16 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው "የመደመር ትውልድ" የሕፃናትና ወጣቶች መጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ እንዲሁም በወረዳ 13 ገርጂ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በ34 ሚ. ብር ወጪ የተገነባውን የስፖርት ሜዳ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መርቀው ከፍተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር አስተዳደሩ ለስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች መስፋፋት በሰጠው ትኩረት በርካታ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ እንደሆነ ገልፀዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ "የመደመር ትውልድ" የተሰኘው መጽሐፋቸው ገቢ ለሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻና የስፖርት ማዕከላት ግንባታ እንዲውል ባደረጉት መሠረት በተለያዩ ክ/ ከተሞች ማዕከላቱ መገንባታቸውን ያመለከቱት ከንቲባዋ፣ "ማዕከላቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ የገባነውን ቃል አሳክተናል፣ ይህ ተግባራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2👎1
ቢሮው ለፕሮጀክቶች ስኬት ለሰጠው የተሳካ አመራር ምስጋና ተቸረው።

በርካታ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎችን በማከናወን ለአገልግሎት እያበቃ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በማዕከልና ክፍለከተማ መዋቅሩ ግንባታቸው የተከናወነ የስፖርት ማዘውተሪያ ፕሮጀክቶች በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል።

ከነዚህም ውስጥ በአራዳ ክፍለከተማ የተገነቡት የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች ይገኙበታል።

በዚህ ምርቃት ስነስርዓት ላይ በክፍለከተማው ለተገነቡ ፕሮጀክቶች መሳካት ቢሮው ለሰጠው ቁርጠኛ አመራር ከክፍለከተማው አስተዳደር ምስጋና ተችሮታል።

ለፕሮጀክቶቹ ስኬት የተሰጠውን የላቀ አመራር ዕውቅና የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ከክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞላ ንጉስ እጅ ተቀብለዋል።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
1👍1
ቅድመ ዝግጅቱ እየተጠናቀቀ ይገኛል።

በሀገራችን አዲስ ታሪክ ለሚፃፍበት ታላቁ ቀን ሐምሌ 10 ቢሮው ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ነው።

በአንዲት ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞችን በመትከል ታላቅ የአካባቢ ጥበቃ ገድል ለሚፈፀምበት ዕለት የችግኝ ዝግጅትና የጉድጓድ ቁፋሮዎች ከወዲሁ በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።

በዕለቱ ቢሮው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ በሚያከናውነው የችግኝ ተከላ መርኃ-ግብር በግንባታው ረገድ እያስመዘገበው የሚገኘውን ውጤት በአረንጓዴ አሻራውም ለመድገም ከፍ ያለ ሞራል ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

#ነገን_ዛሬ_እንትከል
#አረንጓዴ_አሻራ
#500_ሚሊዮን_ችግኞች_በአንድ_ቀን

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍6
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙንኬሽን ቢሮ አስተባባሪነት #ነገን_ዛሬ_እንትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተተገበረ ።

በመርሐ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግርና የእንኳ ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ኮሙንኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ እናት ዐለም መለስ " ዛሬ ቢሮው በላቀ አስተባባሪነት 10ሺህ ችግኞች እንደሚተከል ጠቁመው በከተማ ደረጃ ያቀድነውን እናሳካለን ብለዋል ።

በፊታችን ሰኞም አሻራችንን ለማኖር በሀገር አቀፍ ጥሪው በየደረጃችን ሚናችንን እንድንወጣ የአደራ መልዕክቴን አስተላልፋለው ሲሉ የቢሮው ሀላፊ ወይዘሮ እናት ዐለም መለስ ተናግረዋል

በክብር እንግድነት የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አረንጓዴ ልማትና ውበት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጀማሉ ጀንበር በበኩላቸው "ከተማችንን ብሎም ኢትዮጵያን በአረንጓዴ ልማት የማልበስ ተግባራችን ተጠናክሮ ቀጥሏል በመሆኑም በዛሬው ዕለት " ነገን ዛሬ እንትከል " መርሀ ግብር ላይ የምትሳተፉ ታዋቂ ሰዎች ፣ አርቲስቶች ፣ የኮሙንኬሽን መዋቅሩ ሰራተኞች ፣ የሚዲያ ተቋማት ሀላፊዎችና ጥሪ የደረገላችው ሁሉ እንኳን ደህና መጣችው ብለዋል ።

የፊታችን ሰኞ መጋቢት 10 በመላው ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 500 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ ለዚህም ስኬት አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን በነቂስ ታሳትፋለች ።
👍63