Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.3K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በአራዳ ክፍለከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች በይፋ ተመረቁ፡፡


በዛሬው ዕለት በይፋ ከተመረቁት የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች ውስጥ በክፍለከተማው ወረዳ 2 የሚገኘው ሲመንስ ሜዳና የወጣት ስብዕና መገንቢያ ማዕከል እንዲሁም የአፍሪካ ቁጥር 2 ት/ቤት 3በ1 ሜዳ ይገኙበታል፡፡


የስፖርት ፕሮጀክቶቹን በበጤና ጥበቃ ሚ/ር የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ፣ የአዲስ አበባ ብልፅግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሞላ ንጉስ እንዲሁም ሌሎች የከተማው አመራሮች በይፋ መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡


ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የሲመንስ ሜዳ ግንባታ ሙሉ ወጪ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ‹‹የመደመር ትውልድ›› መፅሀፍ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ የተሸፈነ ነው፡፡


በዛሬው ዕለት በከተማ ደረጃ 410,217,800.37 ብር ወጪ የተደረገባቸው 24 የስፖርት ማዘውተሪያና የልጆች መጫወቻ ስፍራዎችን ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 110 ሚሊዮን ብር የወጣባቸው ሰባቱ ፕሮጀክቶች ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ‹‹የመደመር ትውልድ›› መፅሀፍ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ የተከናወኑ ሲሆን ከ300 ሚ.ብር በላይ የወጣባቸው 17 ፕሮጀክቶች ደግሞ ወጪያቸው በከተማ አስተዳደሩ ተሸፍኗል፡፡…..
👍31
……..የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍3
የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በወጣቶችና ህፃናት እንዲሁም በትውልድ ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን።
--------
በ"የመደመር ትውልድ" መፅሀፍ ሽያጭ ከተገነቡ 7 የወጣቶችና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት አንዱ የሆነውና በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 የተገነባው ፈረንሳይ ለጋሲዮን ስፓርት ሜዳ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደርጓል።

በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ማዕከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት፣ የብልፅግና መንግስት የዛሬና የነገው ትውልድ አካል እንደመሆኑ ወጣቶችና ህፃናት የአዕምሮ፣ የአካልና የስብእና መገንቢያ ስፍራዎችን የሚገነባው ለሀገር ተረካቢ ህፃናትና ወጣቶች ልዩ ትኩረት ከመስጠቱ የመነጨ ነው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡



https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
3
በቦሌ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ተመረቁ።

በክፍለ ከተማው ወ/ 2 በ16 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው "የመደመር ትውልድ" የሕፃናትና ወጣቶች መጫወቻና የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ እንዲሁም በወረዳ 13 ገርጂ ቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በ34 ሚ. ብር ወጪ የተገነባውን የስፖርት ሜዳ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መርቀው ከፍተዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር አስተዳደሩ ለስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች መስፋፋት በሰጠው ትኩረት በርካታ መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ እንደሆነ ገልፀዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ "የመደመር ትውልድ" የተሰኘው መጽሐፋቸው ገቢ ለሕፃናትና ወጣቶች የመጫወቻና የስፖርት ማዕከላት ግንባታ እንዲውል ባደረጉት መሠረት በተለያዩ ክ/ ከተሞች ማዕከላቱ መገንባታቸውን ያመለከቱት ከንቲባዋ፣ "ማዕከላቱ በአጭር ጊዜ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁ የገባነውን ቃል አሳክተናል፣ ይህ ተግባራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል" ብለዋል።


በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይና የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሠ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሐምሌ 08/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡


https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2👎1