Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
197 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
.......ቢሮው ከዚህ ቀደም በእንጦጦ ፓርክ፣በለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ፣አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ እና በየካ ሚሊኒየም ፓርኮች የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብሮቹን ማካሄዱ የሚታወስ ነው ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 30/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
ቢሮው ለአረንጓዴ አሻራው ስኬት አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በዛሬው ዕለት ተግባራዊ ያደረገውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር እንዲሳካ አስተዋፅዖ ላበረከቱ የስራ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች ቢሮው የዕውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል፡፡

በዕውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይም የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት ቢሮው በጠራችሁ ማንኛውም ጊዜ ያለ አንዳች ማቅማማት ማሕበራዊ ኃላፊነታችሁን በመወጣት ሀገራዊ ዕቅዶች እንዲሳኩ ሁሌም ፍቃዳችሁን በመስጠት የልማት አጋርነታችሁን በተግባር ስላረጋገጣችሁልን በቢሮው ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ያሉ ሲሆን ለዕለቱ የተዘጋጀውን የምስክር ወረቀትም በቢሮው ስም አበርክተውላቸዋል፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ ቢ.ጂ.ኤም. ኮንስትራክሽን፣ታቡ ኮንስትራክሽን፣ፍቃዱ ሙላቱ ሕንፃ ስራ ተቋራጭ፣አዞይ ኮንስትራክሽን እንዲሁም ኔማድ ኮንሰልቲንግ በቢሮው ዕውቅና ያገኙ አጋሮች ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 30/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለም/ቤት ካቀረቡት ሪፖርት /በበጀት አመቱ የኘሮጀክቶች አፈፃፀምን በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑ ተግባራት/

👉 የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች መመለስ ላይ ጉልህ ሚና ያላቸው አዳዲስና ከባለፈው በጀት አመት የተሻገሩ ኘሮጀክቶችን ከ6ዐ ቢሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ በጊዜ የለንም መንፈስ፣ ወጪ ቆጣቢና ቶሎ ለአገልግሎት ለማብቃት በሚያስችል ፍጥነትና ጥራት እየገነቡ ይገኛሉ፤
👉በዝርዝር ለመመልከት፡-
=> 538 የመንገድና ተያያዥ ኘሮጀክቶች፣
=> 264 የውሃና ፍሳሽ ኘሮጀክቶች፣
=> 39 የጤና ፕሮጀክቶች፣
=> 1ዐ7 የትምህርት ፕሮጀክቶች፣
=> 99 የሼዶች፣
=> 9 የአረንጓዴና የፓርክ ኘሮጀክቶች፣
=> 28 የእስፖርት ማዘወተሪያ እና የወጣቶች ስብዕና መገንቢያዎች፣
=> 258 ልዩ ልዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ኘሮጀክቶች፣
=> ከ1ዐ,ዐዐዐ በላይ መኖሪያ ቤቶች፣
=> በጥቅሉ በከተማው በጀት 11,3ዐ7 ኘሮጀክቶች እየተገነቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 5,256 ኘሮጀክቶችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፣ ይህ ቁጥር በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩትን አይጨምርም፡፡
--------
👉 የነባር ሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ:-
=> አድዋ ሙዚየም ዜሮ ኪ.ሜ ፕሮጀክት ግንባታ ከነበረበት 74.78% ወደ (86%)፣ ማድረስጠተችሏል፤
=> የትራንስፖርት ቢሮ ተቋማት ህንፃ ግንባታን ከነበረበት 45.79% ወደ (61.5%) ማድረስ ተችሏል፤
=> የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ግንባታ ከነበረበት 43% ወደ (71.2%) ማድረስ ተችሏል.........
👍3👏2
=> እንዲሁም የየካ 2 መኪና ማቆሚያ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታ ከነበረበት 24.27% ወደ (48.2%) ማድረስ ተችሏል፤
=> አዲስ አፍሪካ ኢግዚቪሽን ማዕከል ከነበረበት 6ዐ% ወደ (80%) ማድረስጠተችሏል፤
=> የአቃቂ አለምአቀፍ እስቴዲየም ከነበረበት 65% ወደ 8ዐ% ማድረስ ተችሏል፤
---------
👉 የአዳዲስ የፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ:-
=> አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ ክላስተር ግንባታ ሎት አንድ (16%) እና ሎት ሁለት (46%) ማድረስ ተችሏል
=> የግብርና ምርቶች የገበያ ማዕከላት ማለትም ለሚኩራ ሳይት አንድ (74%)፣ለሚኩራ ሰሚት ሳይት (32%) ኮልፌ ቤቴል ሳይት (88%) እና የላፍቶ ምዕራፍ 86% ላይ ለማድረስ ተችልሏ፤
=> አቃቂና የግብርና ምርት እና የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የገበያ ማዕከል ፕሮጀክት ተጠናቋል፡፡
=> የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ግንባታ (20%) ማድረስ ተችሏል
=> ቤተል መንዲዳ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ 52% ማድረስ ተችሏል፤
=> ላፍቶ ሆስፒታል ፕሮጀክት ግንባታ 36% ማድረስ ተችሏል
=> የጥሩነሽ ቤጂንግ ማስፋፍያ ፕሮጀክት ግንባታ 37% ማድረስ ተችሏል፡፡
👍5
የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ የከተማ አስተዳደሩን ለ2016 ዓ.ም በጀት አመት የ140.29 ቢለየን ብር በጀት አፀደቀ፤
---------
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩን የ2016 ዓ/ም በጀት እቅድ መርምሮ ያፀደቀ ሲሆን
በበጀት አመቱ:-
=> ለመደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 23,498,446,197.00
=> ለካፒታል ወጪዎች 69,336,835,072.00
=> ለመጠባበቂያ በጀት 5,300,000,000.00
---
ለክፍለ ከተሞች:-
=> መደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 33,498,495,001.00
=> ለፒታል ወጪዎች 8,657,773,794.00 የመደበ ሲሆን፣
በጥቅሉ ለከተማ አስተዳደሩ የ140,291,550,064.00 ብር በጀት ለመደበኛ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት አፅድቋል፡፡

የበጀት እቅዱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድር ቃድር ሬድዋን እንደገለፁት አጠቃላይ አሁናዊ በጀቱ ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የ40% እድገት እንዳለው ገልፀው የተያዘውን በጀት ለማሳካት ከታክስ ነክና ታክስ ነክ ካልሆኑ ገቢዎች፣ ማዘጋጃቤታዊ፣ መንገድ ፈንድ፣ የውጭ እርዳታ የውጭ ብድር ገቢን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለው እንደገለፁት የገቢና ወጭ አፈፃፀምን ለማሳካት የኢኮኖሚውን እድገት ማስቀጠል፣ ምርታማነትንና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ በትኩረት የሚሰራበት ይሆናል ብለዋል።
👍4