Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
197 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የአዲስ አበባ ም/ቤት አባላት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

============================


በምልከታው በክ/ከተማ አስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች ተካተዋል።


የም/ቤቱ አባላት በክ/ከተማ አስተዳደሩ የተከናወኑት እና በመከናወን ላይ ያሉት ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተለይ በሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ት/ቤት በመገንባት ላይ የሚገኘው ባለ አምስት ወለል ሕንፃ በአራት ወራት ጊዜያት ውስጥ በጥራት ማገባደድ መቻሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜያት ውስጥ በጥራት በማጠናቀቅ ለማኅበረሰቡ ጥቅም ማዋል እንደሚቻል ማሳያ ናቸው ብለዋል።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 26/2015



ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍52👏1
በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች እየተከናወኑ የሚገኙት የትምህርት መሰረተ ልማት ግንባታዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎችን እያከናወነ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ተግባራዊ አድርጎ ውጤቶችን ባስመዘገበበት የስራ ዕድል ፈጠራ መርኃ-ግብሩ የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታዎችና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪያል ሼድ ግንባታዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

በማሕበራቱ እየተከናወኑ ከሚገኙትና የተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ከደረሱት 22 ትምህርትቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የለሚኩራ ወረዳ 06 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት G+4 ህንፃ ተጠናቆ ለርክክብ ለማዘጋጀት የፅዳት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ በሆኑት በሊትሆፕስ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በበላቸው ተሰጋ እና ጓደኞቻችው አማካሪነት በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 06 በ 405 ካ.ሜ. ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ትምህርት ቤት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ የተያዘለት ሲሆን በሚቀጥሉት 2 ቀናት ሙሉ ስራውን ለማጠናቀቅ የሚያስችል የፅዳት ስራዎች ላይ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 29/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍10
ቢሮው አምስተኛውን ዙር አረንጓዴ አሻራውን አኖረ፡፡

የአዲስ አበባ ደዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ 20 ሺህ ችግኞችን ለመትከል ግብ የያዘበትን የዘንድሮውን አረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት የቢሮውን ሰራተኞች እንዲሁም የተቋሙን ባለድርሻ አካለት በማሳተፍ አካሂዷል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ኤፍ. ኤም. ራዲዮ ጣቢያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በተካሄደው የዘንድሮው ችግኝ ተከላ የመጀመሪያ ዙር መርኃ-ግብር 5 ሺህ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን ለመርኃ-ግብሩ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላትም ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

የቢሮውን የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር በይፋ መጀመሩን ያበሰሩትና መርኃ-ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት ቢሮው ከዚህ ቀደም የነበሩትን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብሮችን በስኬት ማከናወኑን አንስተው በዘንድሮው ዓመት ከወትሮው በቁጥር ላቅ ያለ ችግኝ በቀጣይነት እንደሚተከል በመጥቀስ ይህንንም ቢሮው በግንባታው ዘርፍ እያስመዘገበ በሚገኘው ውጤት ልክ በማሳካት ለታላቁ ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ትልም የድርሻውን ያበረክታል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ለዚህ ለትውልድ ተሻጋሪ ለሆነ ታላቅ ተግባር ስኬት ከቢሮው ጎን በመቆም የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ ስራ ተቋራጮችና አማካሪ ድርጅቶች በቢሮው ስም ምስጋናቸውን አስተላልፈዋል፡፡......
👍51