Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
197 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በዳግማዊ ምኒሊክ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፎረንሲክ ሕክምና እና ስነ-ምረዛ ዲፓርትመንት ሊገነባ በታሰበው ሕንፃ አርክቴክቸራል ዲዛይን መነሻ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

በወንጀል ምርመራው ረገድ የሆስፒታሉ የፎረንሲክ ሕክምናና ስነ-ምረዛ ዲፓርትመንት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመንና በቀጣይ ተቋሙ የዘረመልና የስነ-ምረዛ ምርመራ አገልግሎቶችን በላቀ ደረጃ መስጠት እንዲያስችለው ታስቦ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በሚገነባው በዚህ ሕንፃ ንድፍ ላይ መካተት የሚገባቸው ነጥቦች ዙሪያ የሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሞያዎች እንዲሁም የቢሮው የስራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች በተገኙበት በአማካሪ ድርጅቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ተያይዞም የሆስፒታሉን ነባር ሕንፃ ለማደስ በተያዘው ዕቅድ መሰረት በአማካሪ ድርጅቱ ኔማድ ኮንሰልቲንግ መሪነት በሆስፒታል ግንባታ እና ዕድሳት ሰፊ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው የዘርፉ ባለሞያዎች የተሳተፉበት መነሻ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 26/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
በአዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ማስገንባት ከጀመርናቸው 5000 የኪራይ ቤቶች ውስጥ 400 ያህሉ እየተጠናቀቁ ነው።

ቀሪዎቹ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ይጠናቀቃሉ። የቤት አቅርቦትን ለማሻሻል የጀመርነውን ዘርፈ ብዙ ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን።

ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 26/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍82🤯1
የህዝብ ተመራጮቹ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምና አገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

በዛሬው እለት በክፍለ ከተማው በህዝብ የተመረጡ የአዲስ አባባ ከተማ ምክር ቤት አባላት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባው የሚገኘውን የኮልፌ መንዲዳ አጠቃላይ ሆስፒታልን ጨምሮ ሌሎች የክፍለከተማውን አገልግሎት ለማዘመን እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ተዟዙረው ተመልክተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 26/2015

👍32