Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
196 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በ54 የመኖሪያ ቤት የሕብረት ስራ ማሕብራት የተደራጁ ከ4 ሺህ በላይ የጋራ የመኖሪያ ቤት ቆጣቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የቤት ግንባታ ዛሬ አስጀምረናል።

የነዋሪው ቀዳሚ ጥያቄ የሆነውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ አዳዲስ አማራጭ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ የምንገኝ ሲሆን፣ የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቆጣቢ ነዋሪዎቻችን የከተማ አስተዳደሩ ያዘጋጀውን ይህን አማራጭ ተጠቅመው በማህበር በመደራጀት እና በመቆጠብ የቤት ባለቤት መሆን የምትችሉ መሆኑን አሳውቃለሁ።

ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ -የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍3
የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ለመንገድ ደህንነት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተገለጸ።

መንገዶች ላይ ጉዳት በሚያስከትል ሁኔታ ጭነት በሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎችና የኮንስትራክሽን ግንባታ ማሽነሪ ኦፕሬተሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳሰበ።

በከተማችን በተለያዩ ስፍራዎች ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑ ይታወቃል። ከግንባታዎቹ ጋር ተያይዞ ሲሚንቶ የሚያቦኩ ተሽከርካሪዎች የተቦካ ሲሚንቶ መንገድ ላይ በማፍሰስ እንዲሁም ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ከጭነት አቅም በላይ አፈርና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን መንገዶች ላይ በማፍሰስ እና ጭቃ በጎማቸው ይዘው ወደ ጎዳና የሚወጡ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ለመንገዶች ደህንነት ማድረግ የሚገባቸውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በከፍተኛ ወጪ በተገነቡ መንገዶች ላይ ጉዳት ከማድረሳቸው ባሸገር ለትራፊክ መጨናነቅ መንስኤ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ፖሊስ አጥፊዎቹ ከጥፋታቸው እንዲታረሙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ መቆየቱን አስተውሷል።
በጥፋቱ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከለካል የአዲስ አበባ ፖሊስ እርምጃ እንደሚወስድ አሰጠንቅቋል።

የግንባታ ስራ የሚያከናውኑ ማሽነሪ ኦፕሬተሮችና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች ጭነት በሚጭኑበት ወቅት የመንገድ ደህንነት ህጉ በሚያዘው መሰረት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበቸው እንዲሁም መንገዶቹን በጭቃ የሚያበላሹ፤ የተሽከርካሪዎችንም የጎማ ፅዳት የመጠበቅ ግዴታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ያለው ፖሊስ ይህንን መልእክት በመተላለፍ ጥፋት ላይ በሚገኙ አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስ አስታውቋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ ነው፡፡

ፎቶ-ከማህበራዊ ሚዲያ
👍52
......የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ26/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍6
በዳግማዊ ምኒሊክ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፎረንሲክ ሕክምና እና ስነ-ምረዛ ዲፓርትመንት ሊገነባ በታሰበው ሕንፃ አርክቴክቸራል ዲዛይን መነሻ ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡

በወንጀል ምርመራው ረገድ የሆስፒታሉ የፎረንሲክ ሕክምናና ስነ-ምረዛ ዲፓርትመንት የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማዘመንና በቀጣይ ተቋሙ የዘረመልና የስነ-ምረዛ ምርመራ አገልግሎቶችን በላቀ ደረጃ መስጠት እንዲያስችለው ታስቦ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በሚገነባው በዚህ ሕንፃ ንድፍ ላይ መካተት የሚገባቸው ነጥቦች ዙሪያ የሚመለከታቸው የዘርፉ ባለሞያዎች እንዲሁም የቢሮው የስራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች በተገኙበት በአማካሪ ድርጅቱ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ተያይዞም የሆስፒታሉን ነባር ሕንፃ ለማደስ በተያዘው ዕቅድ መሰረት በአማካሪ ድርጅቱ ኔማድ ኮንሰልቲንግ መሪነት በሆስፒታል ግንባታ እና ዕድሳት ሰፊ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው የዘርፉ ባለሞያዎች የተሳተፉበት መነሻ ጥናት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 26/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
በአዲስ አበባ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ማስገንባት ከጀመርናቸው 5000 የኪራይ ቤቶች ውስጥ 400 ያህሉ እየተጠናቀቁ ነው።

ቀሪዎቹ በሚቀጥለው በጀት ዓመት ይጠናቀቃሉ። የቤት አቅርቦትን ለማሻሻል የጀመርነውን ዘርፈ ብዙ ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን።

👍82🤯1