Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
196 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር B+G+11 ሕንፃ ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ አዲስ በታሰረው የ6 ወራት ውል መሰረት እየተሰራ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባው የሚገኘውና የግንባታ ስራው ከዓመት በላይ በመቆሙ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምንጭ ሆኖ የቆየው የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ በተሰጠው ህጋዊ ውሳኔ መሰረት ለቀሪ ስራዎቹ አዲስ ውለታ ታስሮ ስራውን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ የምሽት ፈረቃ ጭምር ተግባራዊ ተደርጎ እየተሰራ ነው፡፡

ቀድሞ በህንፃው ላይ የነበሩና የበሰበሱ ስካፎልዲንጎችን በማፍረስና እንደገና በማዋቀር እንዳዲስ የተጀመረው የቀሪ ስራዎች ግንባታ በውሀ ተሞልቶ የነበረውን የብሎክ A ሁለተኛ ቤዝመንት ከውሀው ነፃ የማድረግ እንዲሁም ውል በተቋረጠ ጊዜ በቁፋሮ ሂደት ላይ በነበረው ብሎክ C ላይ ያቆረውን ውሀ ቀናትን የወሰደ የማውጣት ስራና ቦታውን በድጋሚ የመቆፈር ብሎም እንደአዲስ የሰሌክትድ ማቴሪያል ሙሌት ከተከናወነ በኋላ ወደዋናው ስራ ተገብቷል፡፡

ዋናው ስራ ከተጀመረ በኋላ የብሎኬትና የውጪ ልስን ስራዎች፣የኮለንና የስላብ ኮንክሪት ሙሌቶች በብሎክ A እና B የተከናወኑ ሲሆን በብሎክ C ደግሞ የግሬድ ቢም ፎርምዎርክና የብረት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

ከ 883 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለት በባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በኔማድ ኮንሰልቲንግ አማካሪነት በ3,364 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ባለ 13 ወለል ሕንፃ ሲጠናቀቅ የክፍለከተማውን አስተዳደር ከፍተኛ የህንፃ ኪራይ ወጪ ከማስቀረቱም ባሻገር አስተዳደሩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ ሕብረተሰቡ የተሻለና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡…..
👍2👏21
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 20/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1444ኛው ዓመተ ሂጂራ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡

#የአዲስ_አበባ_ከተማ_አስተዳደር_ዲዛይንና_ግንባታ_ስራዎች_ቢሮ
👍6
በዛሬው ዕለት በ2389 ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ 12 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች የመስሪያ ቦታ አስረክበናል።
ከ2 ወራት በፊት ከከተማችን ሴቶችና ወጣቶች ጋር ባደረግናቸው ውይይቶች ከመስሪያ ቦታና የስራ ዕድል ፈጣራ ጋር የተያያዘ ኢ-ፍትሀዊነት መኖሩን በነገሩን መሰረት አጣርተን ችግሮች መኖራቸውን በማረጋገጥ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ባልተወጡና የአሰራር ጥሰት በፈፀሙ አመራሮችና ባለሙያዎች ላይ ተገቢ የእርምት እርምጃ ወስደን በ2389 ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ 12 ሺህ የከተማችን ነዋሪዎች የመስሪያ ቦታ አስረክበናል።
እንዲሁም በሸራ ቤት ሲነግዱ የነበሩት የመስሪያ ቦታ የሚገባቸውን አካል ጉደተኞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች መሆናቸውን በማረጋገጥ የመስሪያ ቦታ በመስጠት ስራዎቻቸውን በህጋዊ መንገድ እንዲቀጥሉ አድርገናል።

ዛሬ የመስሪያ ቦታ የሰጠናቸው የአካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶችና ሴቶች የመስሪያ ቦታ ማግኘት በራሱ ግብ አይደለምና፣ ተግታችሁ በመስራት ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር ራሳችሁን እንድትለውጡ አደራ ማለት እወዳለሁ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍6😁21
👉በኮንስትራክሽን ውል ስለ ግንባታ ስራ ርክክብ/Acceptance after completion/

🌟በኮንስትራክሽን ውል ሁለት አይነት የግንባታ ስራ ርክክብ ያለ ሲሆን ይሄውም
ግዚያዊ ርክክብ (provisional acceptance) እና የመጨረሻ ርክክብ (final acceptance) የሚያካትት ነው፡፡

📜በዚህ ጽሁፍ በዋናነት በኮንስትራክሽን ውል ህግ እውቅና የተሰጣቸውን
የርክክብ አይነቶች ምንነትና ተያያዥ ውጤታቸውን አስመልክቶ የህግ
ድንጋጌዎችን እና አሁን ላይ በመንግስት ተቋማት እየተሰራበት ያለውን የፒፒኤ
2011 ጀኔራል ኮንዲሽን ድንጋጌዎችን ባካተተ ሁኔታ ለማብራራት ተሞክሯል፡፡
**
🚧 ግዚያዊ ርክክብ /Provisional Acceptance/

▶️ግዜአዊ ርክክብ በተለይ በኮንስትራክሽን ውል የተመለከቱ የግንባታ ስራዎች ተከናውነው ካበቁ በኋላ ወዲያውኑ ሁለቱ ወገኖች ማለትም አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በስራው ላይ የሚደረግ የምርመራ ማረጋገጫ ስለ መሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3274(1) ይደነግጋል ይሄውም አሰሪው በትክክል የተገነባውን ግንባታ በእጁ አግብቶ መያዙን ጭምር ያረጋግጣል ስለዚህ ጊዜአዊ ርክክብ በዋናነት የተሰራውን የግንባታ ስራ አሰሪው መብቱን ጠብቆ በመጀመሪያ
የሚረከብበት ሂደት ነው ማለት ነው በስራው ላይ ምርመራ መደረጉንም
የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ፒፒኤ 2011 ክሎስ 84.1 ላይ የስራ ምርመራ/verification and test/
በመሀንዲሱ ተቋራጭ ባለበት ሊደረግ እንደሚገባ በመርህ ደረጃ ተቀምጧል፡፡

ሆኖም ግን ተቋራጩ ምርመራው ከሚካሄድበት እለት ከ30 ቀን በፊት በተገቢ ሁኔታ እንዲያውቀው ተደርጐ በምርመራው እለት ያልተገኘ እንደሆነ የስራ ምርመራው ተቋራጩ በሌለበት ሊካሄድ እንደሚችል ይፈቅዳል፡፡

▶️እንግዲህ መሀንዲሱ ስራውን ከመረመረ በኋላ ያላመነበትን የስራ ክፍል ፈርሶ እንደገና እንዲሰራ ወይም እንዲጠገን ተደርጐ የጥራት ደረጃውን ባሟላ ሁኔታ እንዲከናወን ለማዘዝ እንደሚችል ፒፒኤ ክሎስ 85 ይፈቅድለታል፡፡

በዚህም መሰረት ግንባታው የስራ ምርመራውን ካለፈ አሰሪው ግንባታውን
የሚረከበው ይሆናል ማለት ነው ስለዚሁም የጊዜአዊ ርክክብ ሰርተፍኬት
ለተቋራጩ የሚሰጠው ይሆናል፡፡

በመሰረቱ ተቋራጩ የጊዜአዊ ርክክብ
ሰርተፍኬት እንዲሰጠው መጠየቅ ያለበት ስራው ሊጠናቀቅ ይችላል ብሎ
ከሚያስብበት ከ15 ቀን በፊት መሆን ይኖርበታል ከዚያም መሀንዲሱ ጥያቄው
በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ የስራ ምርመራውን አጠናቆ ሰርተፍኬቱን መስጠት ወይም ጥያቄውን ውድቅ ማድረግ ይኖርበታል፡፡

መሀንዲሱ ሰርተፍኬቱን ሳይሰጥ
ወይም ጥያቄውን ውድቅ ሳያደርግ 30 ቀኑ ያለፈ እንደሆነ ለተቋራጩ የጊዜአዊ
ርክክብ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው ግምት እንደሚወሰድ ፒፒኤ ክሎስ 87
ያስቀምጣል፡፡

▶️ሌላው ተቋራጩ በስራው ላይ ያደረገው መሻሻል/መለወጥ ቢኖር እንኳ
በዝምታ ግዜአዊ ርክክብ ከተደረገ መሻሻሉ ተቀባይነት እንዳገኘ የህግ ግምት እንደሚያስወስድ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(2) ይደነግጋል እዚህ ላይ ተቋራጩ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት የመስራት ግዴታ ያለበት መሆኑ ይታዎቅ ስለዚህ የህግ ግምቱ እሳቤ ተቋራጩ ከዲዛይኑ በመውጣት አሻሽሎ የሰራው
ስራ ኖሮ በግዜአዊ ርክክብ ወቅት በዝምታ አሰሪው ካለፈው እንደተቀበለው
ይቆጠራል ነው፡፡

እንዲሁም ግዜአዊ ርክክብ መደረጉ የመድህንነት ጊዜው (warranty period) መጀመሩን እንደሚያመለክት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3275(3) ይደነግጋል፡፡
**
📌የመድህንነት ጊዜ (warranty period/Defects Liability period)

🌟የመድህንነት ጊዜ(warranty period) የሚባለው ከጊዜአዊ ርክክብ እስከ መጨረሻ ርክክብ ያለው ጊዜ ሲሆን አሰሪው ግንባታው በተቋራጩ በደህና ሁኔታ ስለመሰራቱ ለመመርመርና ለማረጋገጥ የሚያስችለው ጊዜ ነው፡፡

የጊዜው ርዝማኔም በውላቸው ላይ የሚወሰን ስለመሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3277 ይደነግጋል ሆኖም በውሉ ላይ የመድህንነት ጊዜው ርዝማኔ ያልተጠቀሰ እንደሆነ ከጊዜአዊ ርክክብ ቀን ጀምሮ 365 ቀን ስለመሆኑ የፒፒኤ ክሎስ 88.7 ያስቀምጣል፡፡

▶️ተቋራጩ በዚሁ በመድህንነት ጊዜ በተለይ የተበላሹ ስራዎችን እንዲያድሳቸው በአሰሪው በታዘዘ ጊዜ የማስተካከል ግዴታ እንዳለበት የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ
3278 ይደነግጋል ለዚህም ለጥገና ወጭ ሲባል ከተቋራጩ ክፍያ ላይ ሪቴንሽን ገንዘብ (retention money or bond) 5% እየተቀነሰ በአሰሪው ይያዛል፡፡

በመድህንነት ጊዜ ውስጥ የተለዩ ብልሽት ያለባቸው ስራዎችን እንዲያስተካክል ተቋራጩ ተጠይቆ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያላስተካከለ
እንደሆነ አሰሪው የማስተካከያ ስራውን በተቋራጩ ወጭ በራሱ ወይም ሌላ
ቀጥሮ ሊያሰራው ወይም ውሉን ሊያቋርጥ ስለመቻሉ ፒፒኤ ክሎስ 88.3
ለአሰሪው መብት ይሰጠዋል፡፡
**
📌ከፊል ርክክብ/Partial Acceptance/

🌟በፒፒኤ ክሎስ 86 ላይ የግንባታ ስራው በከፊል እርክክብ የሚደረግበትንም አማራጭ ያስቀምጣል ይህ ማለት የተወሰነውን የስራ ክፍል (part of the work) ከአጠቃላይ ውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ በውል ላይ ከተቀመጠ ተቋራጩ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከአጠቃላይ የውሉ ጊዜ በፊት ለማስረከብ ይገደዳል ማለት ነው በዚህም በአንድ ውል ውስጥ በተለያየ ጊዜ ጊዜአዊ ርክክብ ሊደረግ የሚችልበትን ሁኔታ ይፈጥራል ማለት ነው፡፡
**
🚧የመጨረሻ ርክክብ/Final Acceptance/

📌የመጨረሻ ርክክብ /Final Acceptance/ በተለይ የመድህንነት ጊዜ ካለቀ በኋላ እና ተቋራጩ ጠቅላላ ግዴታዎቹን በደህና ሁኔታ የፈጸመ መሆኑን አሰሪው ሲያረጋግጥ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በእጁ የሚያደርግበት (definitively appropriate) ስለ መሆኑ የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279 ይደነግጋል፡፡

▶️የመጨረሻ ርክክብ አሰሪውና ተቋራጩ ባሉበት በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት በአስገዳጅ ሁኔታ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3279(2) ላይ ተደንግጓል፡፡

ሆኖም ጊዜአዊ ርክክብ/ Provisional Acceptance/ በሚመለከት ግን በጽሁፍ መደረግ እንዳለበት የሚያስገድድ ግልጽ ህግ የለም፡፡

ስለዚህ ስራው ተጠናቆ አሰሪው ግንባታውን በእጁ ካስገባ ጊዜአዊ ርክክብ መደረጉን የሚያስገነዝብ
ይሆናል ማለት ነው፡፡
በእርግጥ በጽሁፍ መደረጉ ይመከራል፡፡

▶️በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3282 ላይ እንደተቀመጠው ከመጨረሻ ርክክብ
በኋላ ተቋራጩ እስከ 10 አመት ድረስ ስለስራው አሰራር ጉድለት ተቋራጩ
ሀላፊነት አለበት፣መድህን ሆኖ ይቀጥላል፡፡

በመጨረሻ ርክክብ ወቅት የሚታዩ ለነበሩ ጉድለቶች(apparent defect) ግን ተቋራጩ ሀላፊነት የለበትም፡፡
ሀላፊነቱ የሚመለከተው ግንባታው በውሉ የተመለከተውን የታለመለትን ጥቅም እንዳይሰጥ የሚያደርጉ ወይም አጠቃቀሙን በጣም ውድ የሚያደርጉና አክሳሪ የሚያደርጉ ጉድለቶችን ነው፡፡

የመጨረሻ ርክክብ መደረጉ የተቋራጩን መሰረታዊ ግዴታ የሚያወርድለት ሲሆን ቀሪ ክፍያ ካለው እንዲከፈለው እና ዋስትና እንዲወርድለትና የዋስትና መያዣ ገንዘብ ካለም እንዲለቀቅለት ለተቋራጩ መብት የመስጠት ውጤት እንደሚኖረው የፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3281 ይደነግጋል፡፡

▶️ፒፒኤ ክሎስ 89 በተመሳሳይ ስለመጨረሻ ርክክብ የደነገገ ሲሆን የመጨረሻ ርክክብ ሰርተፍኬትም በመሀንዲሱ ለአሰሪውና ለተቋራጩ እንደሚሰጥ ያስቀምጣል፡፡

Source=Gubaie Assefa

#ConstructionLaw

@etconp
👍173
ተቋራጭን ከሳይት ስለማባረር/Expel right/ 

By: Gubaie A.

          ---------   ---------------   ----  
📜በዚህ ጽሁፍ ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብት ለማን የተሰጠ ነው?በየትኛው ህግ?በምን ሁኔታ?በየትኛው የውል አይነት?በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት?የሚሉትን በአጭሩ ለመጠቆም እንሞክራለን፡፡

*ይህ መብት ያለው የትኛው አካል ነው? የሚለውን በተመለከተ ተቋራጭን ከግንባታ ሳይት/ከግንባታ ስፍራ ለማባረር መብት ያለው አሰሪው ነው ስለዚህ መብቱ የግንባታው ባለቤት ወይም የአሰሪው ነው፡፡

ስለዚህ ይህን መብት ተቋራጮች ሆኑ አሰሪ ያልሆነ ሌላ አካል ተግባራዊ ሊያደርገው አይችልም ማለት ነው፡፡
.
*በየትኛው ህግ? ለሚለው ምላሹ በፍትሀብሄር ህጉ እና በጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት ነው፡፡በዝርዝር ሲታይ፡-

▶️በግንባታ ውሎች በተለይ ጀኔራል ኮንዲሽነን ኦፍ ኮንትራክት መጠቀም የተለመደ ነው፡፡እነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች በራሳቸው ህግ አይደሉም፡፡እዚህ ላይ አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደ መመሪያ እና ህግ ስለሚቆጥሩት ይህ የግንዛቤ ክፍተት መታረም ይኖርበታል፡፡የግንባታ ውል ተዋዋዮች በስምምነታቸው እነዚህን ጀኔራል ኮንዲሽኖች የውሉ አካል ሲያደርጓቸው በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1731 መሰረት በተዋዋዮች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ፡፡እዚህ ላይ ሌላው ጉዳይ ስፔሻል ኮንዲሽን ኦፍ ኮንትራክት ተብለው የሚቀመጡት ከጀኔራል ኮንዲሽኑ ድንጋጌዎች የተፈጻሚነት ቅድሚያ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ ከነዚህ ጀኔራል ኮንዲሽኖች ውስጥ የሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ/Standard condition of contract for the construction of civil work projects/ አንዱ ነው፡፡ይህ ጀኔራል ኮንዲሽን በከተማ ልማት ሚኒስቴር በኩል የተዘጋጀ ሲሆን ይዘቱ በዋናነት ከFIDIC 1987 version የተወሰደ ነው፡፡

በአብዛኛው MoWUD 1994 ተብሎ ይጠራል፡፡ሆኖም ዋናው ነጥብ ተዋዋዮች ጥቅም ላይ ያዋሉትና የውላቸው አካል ያደረጉት የትኛውን ጀኔራል ኮንዲሽን እንደሆነ መለየትና ማወቅ የግድ ይላል፡፡

ከዚህ አንጻር MoWUD 1994 ክሎዝ 63 ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት የማባረር መብትን አስመልክቶ በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡በዚህ ድንጋጌ መሰረት በዋናነት አማካሪ መሀንዲሱ ለአሰሪው የተቋራጩን እንደውሉ ያለመፈጸም ሲያሳውቅ በተለይም ተቋራጩ ስራውን እንደተወው አማካሪው ሲያስታውቅ፣ተቋራጩ በአማካሪ መሀንዲሱ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ለ28ቀናት ስራውን ሳይጀምር ሲቀር፣በመሀንዲሱ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ የግንባታ ቁሳቁሶችን በ28 ቀናት ውስጥ ከሳይት ያላስወጣ እንደሆነ፣በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው ስራውን በውሉ አግባብ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነ እንደሆነ፣አማካሪ መሀንዲሱ እየከለከለው የስራውን ክፍል ለሌላ ተቋራጭ አሳልፎ የሰጠ እንደሆነ ወይም ተቋራጩ የከሰረ እንደሆነ አሰሪው የ14 ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ተቋራጭን ከግንባታ ስፍራ/ሳይት ማባረር የሚችል ይሆናል፡፡በዚህ ጊዜ ውሉ ይቋረጣል ማለት ነው፡፡/Termination of contract/
በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 3288 አና ተከታዮቹ ላይ የተደነገገውም ተቋራጩ የውል ግዴታውን ባልፈጸመ ጊዜ የግንባታ ባለቤት ለሆነው ለአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ስራውን ከተቋራጩ ለመንጠቅ እና ውሉ ሳይቋረጥ ስራው በስራ መሪ ስር ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ መብት ይሰጠዋል፡፡እንዲሁም ውሉ ሊሰረዝ የሚችልበት ፈቃጅ የውል ቃል በግንባታ ውሉ ላይ ያለ እንደሆነ አሰሪው ቀሪውን ስራ ለሌላ ተቋራጭ በጨረታ ወይም በስምምነት በማሰራት እንዲጠናቀቅ ማድረግ ይችላል፡፡/የፍ/ህ/ቁ 3291(1) በዚህም ምክንያት አሰሪው ለተጨማሪ ወጭ/Additional cost/ የተዳረገ እንደሆነ ከተቋራጩ ላይ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 3291(2) በግልጽ መብት ይሰጠዋል፡፡ሆኖም በውል ህግ ላይ አሰሪው የተቋራጩን ግዴታ በሚያከብድ ሁኔታ ቀሪውን ስራ ማከናወን እንደሌለበት የሚያስገነዝበውን ግዴታውንም ማክበር አለበት፡፡

በየትኛው የውል አይነት? ለሚለው በዋናነት የአስተዳደር መስሪያ ቤት የግንባታ ውሎችን በሚመለከት ሊተገበር የሚችል ነው፡፡ በግል የግንባታ ውሎች/private construction contract/ በተለይ ከፍ/ህ/ቁ 2610 እና ተከታዮቹ እንዲሁም ከፍ/ህ/ቁ 3019 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ውስጥ ተቋራጭን ስለማባበር አስመልክቶ ግልጽ ድንጋጌ አለመኖሩ ይህ መብት ለግለሰቦች ለመተግበር አስቸጋሪ የመሆኑን ሁኔታ ታሳቢ ተደርጐ በህግ አውጭው በማወቅ/ፐርፐዝሊ/ የተተወ ይመስላል፡፡ተዋዋዮች የግንባታ ውል ሲዋዋሉ ጀኔራል ኮንዲሽን ቢጠቀሙና በዚህም ስለተቋራጭ የማባረር መብት ድንጋጌ ቢኖረውስ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል?ይሄን እንዴት ይተገብረዋል የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ ውሉ ግን ለተዋዋዮች ህግ ስለሚሆን በተቻለ መጠን ሊተገበር ይገባዋል የሚል እሳቤ አለኝ፡፡  

በዚህ ጊዜ ማን ምን መስራት አለበት? ለሚለው በዋናነት በ MoWUD 1994 ክሎዝ 63(2) ላይ እንደተቀመጠው በግንባታ ሳይት ላይ የተገኘ ቁሳቁስ በሙሉ በዝርዝር መመዝገብና ዋጋ ወጥቶለት መጠኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡በተቋራጩ የተሰራው ስራ መጠን/level of work done/ በትክክል መታወቅና በዝርዝር መመዝገብ አለበት፡፡ተቋራጩ ያለበት እዳ/ከወሰደው የቅድሚያ ክፍያ ውስጥ ያልመለሰው ማለት ነው/ መታወቅ አለበት ለተቋራጩ የተከፈለው የስራ ክፍያ ሊታወቅ ይገባል፡፡

እነዚህን የሂሳብ ሁኔታዎች አመዛዝኖ እና ዋጋ አስቀምጦ ተቋራጩ የሚከፈለው ገንዘብ ካለ እንዲከፈለው ለአሰሪው የሚመልሰው ገንዘብ ካለም እንዲመልስ ሂሳብ የማስተሳሰብና ሪፖርት የማቅረብ ሀላፊነቱ የአማካሪ መሀንዲሱ ነው፡፡
በዚህ ረገድ አማካሪ መሀንዲሶች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሪፖርት ስለማያቀርቡ የግንባታ ክርክሮች ያልተሸከፉ ይሆኑና ለፍርድ ቤቶች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ አስቸገሪ ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

አሰሪው ይህን መብቱን ለመጠቀም ሀይል መጠቀም የሚችልበት ግልጽ ፈቃጅ ህግ ግን የለም፡፡

በመጨረሻም አሰሪና ተቋራጮች ለግንባታ ጥራት በመስራትና ለትክክለኛ እና እውነተኛ ነገር በመተባበር የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እድገት እንዲያሳይ ማገዝና አለመግባባቶችን በስምምነት መፍታት ቢችሉ ጠቀሜታው ለሀገርም ለራሳቸውም ነው፡፡

በአሰሪና ተቋራጭ ክርክር ብዙ ትምህርት ቤት እና የጤና ተቋም እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው ተቋርጦ ማህበረሰቡን ከተጠቃሚነት የሚያዘገይበት ሁኔታ ወደፊት ተቀርፎና ተቃልሎ ማየት የዘወትር ምኞታችን ነው፡፡

#ConstructionLaw

@etconp
👍113
በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ላይ ያለውን የኤች .ኤይ ቪ ተጋላጭነት ለመቀነስ ያስችላል የተባለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡

የአዲስ አባባ ዲዛይንና ግንበታ ሥራዎች ቢሮ ባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዩችና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በመተባበር በኮንስትራክሽን የስራ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለውን ተጋላጭነት ለመቀነስ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለአጠቃላይ ሰራተኛው ተሰጥቷል፡፡

የኮንስትራክሸን የሥራ ዘርፍ በርካታ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት እና የመስክ ስራዎች የሚበዙበት እንዲሁም ወጣቱን የሕብረተሰብ ክፍል በስፋት የሚያሳትፍ በመሆኑ ቀላል የማይባል የኤች .አይ ቪ ተጋላጭነት ይስተዋልበታል የተባለ ሲሆን በዘርፉ ያለውን ስርጭት ለመቀነስና ለመከላከል ተቋሙ ቅንጅታዊ አሰራርን ማሳደግ ፤ የድጋፍና እንክብካቤ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ፤ የመከላክያና መቆጣጠሪያ ፕሮግራሞችን ማጠናከር/ የባህሪ ለውጥ ላይ መስራት እና አሁን ካለው በተሻለ መልኩ የሜየንስትሪሚንግ ስራዎችን ማሳደግ እንደሚገባው በስልጠናው ላይ ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል በከተማ ደረጃ አሁናዊ የኤች. አይ ቪ ኤዲስ ስርጭት ተቀልብሶ በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ እየጨመረ እንደሚገኝ ተጠቁሞ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመደረሱና መዘናጋቱ እየጨመረ በምጣቱ በግለስብ ፤ በቤተሰብና በተቋም ደረጃ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚስችል ውጫዊና ውስጣዊ የሜየንስትሪሚንግ አካቶ መስራታን አጠናክሮ መስራትና የመከላከልና የመቆጣጠር ፕሮግራሞችን ማጠናከር እንደሚስፈልግም በመድረኩ ተገልፇል፡፡…..
2👍1