Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.1K photos
194 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የኮልፌ ወረዳ 2 ጤና ጣቢያ ግንባታ 83 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ እያስገነባቸው ከሚገኙ 6 የጤና መሰረተልማቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የኮልፌ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩለት ይገኛል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ ወረዳ 02 በተለምዶ ካራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ተይዞለት በ7,445 ካ.ሜ.ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘውን ይህን ጤና ጣቢያ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

83 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ በደረሰው በዚህ ፕሮጀክት አሁን ላይ የምድረ ጊቢ ስራን ጨምሮ የድጋፍ ግንብ፣የአጥር፣የኤሌክትሪክ፣የሳኒተሪ እና መሰል የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይም ሊፍት ገጠማ፣የበርና መስኮት ስራ፣ስካይላይት ገጠማ፣የውስጥ ቀለም ቅብ ስራ፣የዋናው መግቢያ በር እና ተያያዥ የአጥር ስራዎችን የመሳሰሉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ከቢሮው ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ጤና ጣቢያው የመድሀኒት ቤት፣የቲቢ ህክምና ማዕከል፣የንፅህን መስጫ ክፍል፣ካፍቴሪያና ፓርኪንግን ጨምሮ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች እንዲሟሉለት ሆኖ እየተገነባ ይገኛል፡፡

ግንባታውን በተቋራጭነት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያከናውነው ሲሆን የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ደግሞ በማማከሩ ይሳተፉበታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 07/2015
👍12😁1
bejing terunesh
<unknown>
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባው በሚገኘው የጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዙሪያ ኢትዮ ኤፍ. ኤም. የሰጠው ሽፋን።

ሰኔ 07/2015
👍6
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገነባው የሚገኘው የኮልፌ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግንባታ አፈፃፀም፡፡

የዲዛይንን ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 09/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍83🔥1
የወጣቱን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ግንባታዎች በጥራት እየተከናወኑ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ ዘርፈ ብዙ ማሕበራዊ አገልግሎት ሰጪ ግንባታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የየካ 3 በ1 ስፖርት ሜዳ ግንባታ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ ደርሷል፡፡

በየካ ክፍለከተማ በተለምዶ ሾላ መብራት ወይም የካ ፓርክ ውስጥ በ3,600 ስኩዌር ካሬ ሜትር ቦታ ላይ እየተገነባ የሚገኘውና 22 ሚሊዮን ብር የውለታ ገንዘብ የተያዘለት ስፖርት ሜዳው 93 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

ይህ 3 በ 1 ስፖርት ሜዳ ደረጃቸውን የጠበቁ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ እና የመረብ ኳስ መጫወቻ ሜዳዎች የሚኖሩት ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ባለ ጥላ የተመልካች መቀመጫ፣የስፖርተኞች ልብስ መቀየሪያ እና መታጠቢያ ክፍሎች እንዲሁም ለስፖርት ማሕበረሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ካፍቴሪያና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ-ልማቶች ተሟልተውለት እየተገናባ ይገኛል፡፡

በፕሮጀክቱ የስፖርት ሜዳ ኢፖክሲ ስራ ፣ የበር እና መስኮት ገጠማ ፣የኤሌክትሪክ እና ሳኒተሪ እቃዎች ገጠማ እንዲሁም የመጫወቻ እቃዎች ገጠማ በሚቀጥሉት 2 ሳምንታት ተከናውነው ለርክክብ ዝግጁ እንደሚደረግ ከኮንትራት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡…….
👍73
…….ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
2👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
‹‹ #ነገን_ዛሬ_እንትከል››

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አምስተኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ ቀደም በቢሮው የነበሩ የአረንጓዴ አሻራ መርኃ-ግብር ትውስታዎች

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 16/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7😁31
#ቀጥታ_ከአርቲስት_አሊ_ብራ_አደባባይ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ያስገነባው የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ብራ መታሰቢያ ሀውልት በይፋዊ ምርቃት ላይ ይገኛል።

በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመርኃ-ግብሩ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ የክብር እንግዶች ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
4👍4
የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ብራ መታሰቢያ ሀውልት በይፋ ተመረቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ያስገነባው የክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ብራ መታሰቢያ ሀውልት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

2 ሜትር መቆሚያና ዋነኛው የሀውልቱ አካል 4 ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ በተስፋዬ ገብሬ ስዕልና ቅርፃቅርፅ ስራ የተቀረፀው ይህ ሀውልት የአርቲስቱን ጥበባዊ ህይወት በሚያንፀባርቅ መልኩ ተሰርቶ በአርቲስቱ ስም በተሰየመው አደባባይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ፣የፋይናንስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ሌሎች የፌዴራልና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የአርቲስቱ ቤተሰቦችና አድናቂዎች ተገኝተዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ላበረከተው አስተዋፅዖ ከከተማው አስተዳደር ከንቲባ ምስጋና ተችሮታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሰኔ 18/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍94