Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.5K subscribers
12.1K photos
193 videos
89 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በከተማዋ የሚገነቡ ግንባታዎች ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ድሕረ-ግንባታ ድረስ የአካል ጉዳተኞችን ከግምት ያስገቡ መሆን እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡

በአካል ጉዳተኝነት እና በኮንስትራክሽን ስራዎች ቁርኝት እንዲሁም መደረግ ስለሚገባው አፅንዖት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው ይህ ስልጠና በቢሮው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አስተባባሪነት እና አዲስ አበባ ሴቶች፣ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በምህንድስና እና ሌሎችም ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡

አካል ጉዳተኞች በታሪክ ውስጥ ተገቢውን ቦታ እና ሰብዓዊ ክብር ሳያገኙ መቆየታቸውና በዚህና በሌላም ምክንያቶች በማሕበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና በሌሎች ልማታዊ ስራዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተሳታፊ ሳይሆኑ እንደቆዩ ተጠቅሶ ይህን የተሳሳተ ዕሳቤ ለመቃወም በዓለም ዓቀፍ ብሎም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተደረጉ የሚገኙ ትግሎችም ለውጦችን እያመጡ እንደሚገኙ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አሉላ ሲሳይ በስልጠና ወቅት ጠቅሰዋል፡፡


በከተማችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሰፊ ድርሻ ያለው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተሰማራበት ዘርፍ እንደ ተቋም የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ አካቶ ስራ ላይ በተግበር ከማዋል በተጨማሪ የሚሰሩ ዲዛይኖች አካል ጉዳተኞችን አካታች ስለመሆናቸው እና ግንባታዎቹም እነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በማረጋግጥ ረገድ የማይናቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡…….
1👍1
የኮሙኒኬሽ ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 17/2015 ዓ.ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባው በሚገኘው የአቃቂ ስታዲየም ግንባታ ዙሪያ በዘርፉ ዓለም ዓቀፍ ልምድ ካላቸው ተቋማት ተቋማት ጋር ያደረገውን ውይይት በተመለከተ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍ.ኤም.96.3 ያጋራው መረጃ።

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 17/2015
👍1
የጎዴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡

መገኛው በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 14 አባዶ ኮንዶሚኒየም የሆነውና ቁጥራቸው 3,085 የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግደው የጎዴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ 100 % ተጠናቋል፡፡

የወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ት/ት ተቋሙ የማምጣት ፍላጎት መጨመሩን ተከትሎ ማስፋፊያ ሕንፃ በማስፈለጉ ከዛሬ አራት ወር በፊት የግንባታ ስራው አንድ ብሎ የጀመረው የጎዴ አንደኛ ደረጃ SB+G+4 ት/ቤት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ባደረጋቸው በ ቢ.ጂ.ኤች. ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በ ሲጫሌ፣ብሩክ እና ጓደኞቻቸው አማካሪነት የተከናወነው ይህ ግንባታ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ተይዞለት የተከናወነ ሲሆን በተያዘለት የጊዜ ማዕቀፍ እንዲሁም በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ ተከናውኖ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል፡፡

ቢሮው እየተከተለው የሚገኘው ፕሮጀክት ማኔጅመነት ስርዓት ውጤታማነት እንዲሁም የማሕበራቱ ፕሮጀክቶችን የማጠናቀቅ ዓቅም መጎልበት ማሳያ የሆነው ሕንፃው አስፈላጊው የትምህርት መሰረተልማቶች ሁሉ የተሟሉለት ሲሆን አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ላይ የራሱን አዎንታዊ ሚና እንደሚጫወት ይጠበቃል፡፡…
3👍3
….ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍3
የሳላይሽ አንደኛ ደረጃ G+4 ት/ቤት ሕንፃ ሙሉ በሙሉ ተጠናቀቀ፡፡

በየካ ክፍለከተማ ወረዳ 10 የሚገኘውና 3500 ተማሪዎችን ተቀብሎ የአፀደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርትን በጥምረት የሚሰጠው የሳላይሽ ት/ቤት ማስፋፊያ የሆነው ባለ 5 ወለል ሕንፃ ከተያዘለት የውለታ ጊዜ ቀድሞ በመጠናቀቅ ለርክክብ ዝግጁ ተደርጓል፡፡

ቢሮው በዘረጋውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲሁም በጠንካራ የክትትል ስርዓት እየተመራ የሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ውጤት የሆነው የሳላይሽ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት G+4 ሕንፃ ከተያዘለት የ120 ቀናት የማጠናቀቂያ ጊዜ ቀድሞ መጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ይህም የቢሮውን የፕሮጀክት ማኔጅመንት ስርዓት ፍሬያማነት እና የማሕበራቱን የመብቃት ደረጃ የሚያሳይ ፕሮጀክት ሆኖ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ ተይዞለት በ380 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የተገነባውን ይህን ህንፃ አቻ ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማ በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ሲጫሌ ብሩክ እና ጓደኞቻቸው አማካሪ ማህበር በአማካሪነት ያከናወኑት ሲሆን ተሞክሮ የተወሰደበትና ለማህበራቱም ዓቅም መፍጠር የቻለ ፕሮጀክት መሆኑ ታይቷል፡፡

የዛሬ አራት ወር ሀሳብ ብቻ የነበረውና አሁን ላይ 100 % ተጠናቆ ለወላጆችና ተማሪዎች መልካም ብስራት ይዞ ብቅ ያለው ይህ ፕሮጀክት የስራ ዕድሉ ተጠቃሚ ከሆኑት ስራ ተቋራጭና አማካሪ ማሕበራት በተጨማሪ በየዕለቱ ለ120 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል፡፡….
👍43