Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.5K subscribers
12.1K photos
193 videos
89 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የወረዳ 10 ብሎክ 7 ስትራክቸራል ስራ ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ 7 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ አጠቃላይ ወጪ የተያዘላቸውና ቁጥራቸው 140 የሚሆን የ G+4 የትምህርትቤቶችና ማምረቻ ሼዶች ግንባታዎችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት በመስጠት በጠንካራ ዲሲፕሊን የሚመራ የፕሮጀክት ግምገማ ስርዓት ዘርግቶ ፕሮጀክቶቹን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የዚህ ፕሮግራም አካል የሆኑትና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እየተገነቡ ከሚገኙ ብዛታቸው 8 የሆኑ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ውስጥ የብሎክ 07 ሕንፃ በመልካም የግንባታ አፈፃፀሙ የሚጠቀስ ነው፡፡

ከተጀመረ የ2 ወራት ዕድሜ ያስቆጠረው ይህ ባለ አምስት ወለል ኢንዱስትሪያል ሼድ አሁን ላይ የስትራክቸራል ስራው ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ ሲሆን የብሎኬትና የልስን ስራዎች 2ኛ ፎቅ ከመድረሳቸውም በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት ለሚከናወነው የጣርያ ስራ ውቅር እንደተጀመረ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ካደረጋቸው ኢንተርፕራይዞች ውስጥ አንዱ በሆነው ሳዶር ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የግንባታ ስራው እየተከናወነ የሚገኘውና ቢኒያም፣ዶናት እና ጓደኞቻቸው የህንፃ አማካሪ ድርጅት በማማከር እየተሳተፉበት የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የፊዚካል አፈፃፀሙ 67 በመቶ ላይ መድረስ ችሏል፡፡

ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለት ይህ ህንፃ ቢሮው ባስቀመጠው የ120 ቀናት የኮንትራት ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይችል ዘንድ በሳይቱ የምሽት ፈረቃ ተግባራዊ ተደርጎ የግንባታ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡……….
3👍1😁1
………..የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 15/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍6
የአቃቂ ስቴዲየም ግንባታ ላይ እሴት የሚጨምር ውይይት ተካሄደ፡፡

የዓለም ዓቀፉን የእግርኳስ ፌዴሬሽን /FIFA/ እንዲሁም የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን /CAF/ መስፈርቶች እንዲያሟላ ታስቦ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እየተገነባ ለሚገኘው የአቃቂ ስቴዲየም ግንባታ ስኬት በዘርፉ ዓለም ዓቀፍ ልምድ ካላቸው ተቋማት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በከተማችን ብቻም ሳይሆን በሀገራችን ጭምር በብቸኝነት ዝቅተኛውን የዓለምዓቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ ለስፖርቱ ማሕበረሰብ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተስፋ ለተጣለበት የአቃቂ ስቴዲየም ግንባታ ዕውን መሆን ተጨማሪ ዓቅም የሚፈጥር ውይይት ከአራት ዓለም ዓቀፍ ተሞክሮ ካላቸው ተቋማት ጋር ተደርጓል፡፡

መቀመጫውን ማሌዢያ በማድረግ በደቡብ ምስራቅ ኤዢያ ሰፊ የገበያ ድርሻ ያለው የስፖርት መሳሪያዎች አምራቹ AFN sport ን ጨምሮ የመሮጫ ትራኮችን እና የተለያዩ የወለል ንጣፍ አይነቶችን የሚያመርተው የጀርመኑ VIACOR እንዲሁም በሃይብሪድ ቴክኖሎጂ የስቴዲየም ሳር በማብቀልና በመግጠም በአውሮፓ ገበያ ላይ ሰፊ ልምድ ያለው HATKO እና የተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ስቴዲየም መብራቶችን አምርቶ በመግጠም የሚታወቀው የማሌዢያው EXELUX ኩባንያዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የግንባታ ስራውን በስራ ተቋራጭነት ከሚያከናውነው ዛምራ ኮንስትራክሽን እና አማካሪ ድርጅቱ ኔማድ ኮንሰልቲንግ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይቱም መጪው የዝናብ ወቅት የግንባታ ስራውን በማያውክ መልኩ ይከናወን ዘንድ የትኛው ስራ መቅደም እና የትኛው መከተል እንደሚገባው ከባለሞያዎቹ ጋር ንግግር የተደረገ ሲሆን የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮም ለስራው አስፈላጊ የተባሉ የአየር ንብረትና መሰል መረጃዎችን ከሚመለከተው አካል እንዲያቀርብ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ……
👍5
…..የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 16/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2
በከተማዋ የሚገነቡ ግንባታዎች ከዲዛይን ጀምሮ እስከ ድሕረ-ግንባታ ድረስ የአካል ጉዳተኞችን ከግምት ያስገቡ መሆን እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡

በአካል ጉዳተኝነት እና በኮንስትራክሽን ስራዎች ቁርኝት እንዲሁም መደረግ ስለሚገባው አፅንዖት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገው ይህ ስልጠና በቢሮው የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አስተባባሪነት እና አዲስ አበባ ሴቶች፣ሕፃናትና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮ በትብብር የተዘጋጀ ሲሆን በምህንድስና እና ሌሎችም ዘርፎች ተሰማርተው የሚገኙ የቢሮው ሰራተኞች ተሳትፈውበታል፡፡

አካል ጉዳተኞች በታሪክ ውስጥ ተገቢውን ቦታ እና ሰብዓዊ ክብር ሳያገኙ መቆየታቸውና በዚህና በሌላም ምክንያቶች በማሕበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና በሌሎች ልማታዊ ስራዎች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ተሳታፊ ሳይሆኑ እንደቆዩ ተጠቅሶ ይህን የተሳሳተ ዕሳቤ ለመቃወም በዓለም ዓቀፍ ብሎም በሀገር ዓቀፍ ደረጃ እየተደረጉ የሚገኙ ትግሎችም ለውጦችን እያመጡ እንደሚገኙ ስልጠናውን የሰጡት የአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ አሉላ ሲሳይ በስልጠና ወቅት ጠቅሰዋል፡፡


በከተማችን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሰፊ ድርሻ ያለው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተሰማራበት ዘርፍ እንደ ተቋም የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ አካቶ ስራ ላይ በተግበር ከማዋል በተጨማሪ የሚሰሩ ዲዛይኖች አካል ጉዳተኞችን አካታች ስለመሆናቸው እና ግንባታዎቹም እነዚህን የሕብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን በማረጋግጥ ረገድ የማይናቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡…….
1👍1
የኮሙኒኬሽ ጉዳዩች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 17/2015 ዓ.ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
1