Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
89 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የተመራ ከፍተኛ አመራር ቡድን በክፍለከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት እያስገነባቸው የሚገኙ ዘጠኝ ማሕበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች ያሉበትን ሁኔታ ለመገንዘብ የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተካሂዷል፡፡

የክፍለከተማው የካቢኔ አባላትን፣የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችን፣ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን፣የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የፓርቲ ኃላፊዎችን ባካተተውና በክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የተመራው የዚህ የመስክ ምልከታ ዓላማ አመራሩ በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን አውቆና በፕሮጀክቶቹ ላይ ያሉ ችግሮችን ተረድቶ መፍትሄ በመስጠት ሂደቱ ላይ የራሱን አበርክቶ እንዲያሳርፍ ዕድል ከመፍጠሩም ሌላ በበጀት ድልድል ወቅት የእነዚህን ፕሮጀክቶች አንገብጋቢነት ተረድቶ የአመራሩን በቂ ትኩረት እንዲያገኝ አስቻይ አጋጣሚን ይፈጥራል ሲሉ የክፍለከተማው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ኃላፊው ኢ/ር ስንታየሁ ማሞ አስረድተዋል፡፡

የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አበራ ብሩ የመስክ ምልከታውን ሲያጠቃልሉ እንዳሉት ምልከታ ከተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የወረዳ 12 ወጣት ማዕከል ፕሮጀክቶች ግንባታ አፈፃፀሞችን አድንቀው በዛሬው ዕለት ምልከታ የተደረገባቸው አጠቃላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው የታለመላቸውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሁሉም አመራር በባለቤትነት ይዞ ማስፈፀም እንደሚገባው አደራ ሰጥተው ይህም በጋራ የመምራታችን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡…….
👍52
……..በመስክ ምልከታው የወረዳ 05 ስፖርት ሜዳ፣ቃሊቲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማስፋፊያ፣ የወረዳ 08 ፖሊስ ጣቢያ፣የህዳሴ ሲኒማ አዳራሽ ጥገና፣የወረዳ 01 ማኑፋክቸሪንግ ሼዶች፣የወረዳ 01 ደረቅ ቆሻሻ ቅብብሎሽ ጣቢያ፣ኤላ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት፣አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የወረዳ 12 ወጣት ማዕከል ፕሮጀክቶች ተካተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 13/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
የለሚኩራ ወረዳ 6 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ብሎክ 4 ግንባታ 65 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ 140 ለሚሆኑ ኢንተርፕራይዞች ስራዎችን መስጠቱን ተከትሎ የነገው የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ተስፋ የሚሆኑ ማሕበራት እየተስተዋሉ ይገኛል፡፡

ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 06 እየተገነቡ የሚገኙትና ብዛታቸው 8 የሆነ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በዚህ የግንባታ ሳይት ላይ ከሚገነቡ ብሎኮች ውስጥ የብሎክ 04 የግንባታ ፍጥነት በመልካም አፈፃፀሙ በማሳያነት ይጠቀሳል፡፡

የግንባታ ስራው የካቲት መጨረሻ የተጀመረው የዚህ ሕንፃ አሁናዊ ሁኔታ ከውለታው ቀድሞ መጠናቀቅ በሚያስችለው አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን አሁን ላይ ቶፕ ታይ ቢም የሙሌት ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል በተጨማሪም የብሎኬት እና የልስን ስራ እስከ 2ኛ ፎቅ መጠናቀቅ የቻለ ሲሆን ጎን ለጎንም የኤሌክትሪክ ስራዎች እየተሰሩና የጣራ ከንች እየተመረተ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

ከ69 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለትን ይህን ግንባታ ራሄል እና ፀዳለ ኮንስትራክሽን በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም አደይ ፍሬህይወት እና ጓደኞቻቸው በማማከር እያከናወኑት የሚገኙ ሲሆን ፕሮጀክቱን ከውለታው ቀድመው እንደሚያጠናቅቁና ይህንንም ዕውን ለማድረግ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጋቸውን የማሕበሩ ስራ አስኪያጅ ጠቅሰዋል፡፡.......
3👍3😁2
.........የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 13/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👎4👍2
የብሎክ 10 ግንባታ ስራ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ያደረጋቸው ኢንተርፕራይዞች በከተማዋ የተለያዩ ክፍለከተሞች የተሰጣቸውን ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጥራትና ጊዜ እንዲሁም በተመደበላቸው በጀት አጠናቀው እንዲያስረክቡና ፕሮጀክቶቹ በዕቅዳቸው መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የድጋፍ እና ክትትል ስርዓት በመዘርጋት ፕሮጀክቶቹ መልካም አፈፃፀም እንዲያስመዘግቡ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ ረገድ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እየተገነቡ ከሚገኙ ስምንት G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ውስጥ 66 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ የደረሰው ብሎክ 10 ይጠቀሳል፡፡

120 ቀናት የማጠናቀቂያ ጊዜ ተሰጥቶት መጋቢት 12/2015 ዓ/ም የግንባታ ስራው በተጀመረው በዚህ ፕሮጀክት አሁን ላይ ቶፕ ታይ ቢም ተጠናቆ የብሎኬትና ልስን ስራዎች 3ኛ ወለል ላይ ከመድረሳቸው ጎን ለጎን የጣሪያ ማዋቀር ስራዎች ተሳልጠው እየተከናወኑ ሲሆን በተያዘለት የጊዜ ማዕቀፍ ይጠናቀቅ ዘንድ የምሽት ፈረቃ ተግባራዊ ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቢሮው በየግንባታ ሳይቱ ተግባራዊ እያደረገውና ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበበት የሚገኘው 7/24 የስራ ፕሮግራም ዕውን የተደረገበት ይህ ኢንዱስትሪያል ሼድ ፕሮጀክት 68 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ተይዞለት የግንባታ ስራውን አለሙ ፈጠነ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ሲያከናውነው ቢኒያም፣ዶናትና ጓደኞቻቸው የማማከር ኃላፊቱን ተቀብለው እየተከታተሉት ይገኛሉ፡፡…..
👍82
…….የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 14/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2
የወረዳ 10 ብሎክ 7 ስትራክቸራል ስራ ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ 7 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ አጠቃላይ ወጪ የተያዘላቸውና ቁጥራቸው 140 የሚሆን የ G+4 የትምህርትቤቶችና ማምረቻ ሼዶች ግንባታዎችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት በመስጠት በጠንካራ ዲሲፕሊን የሚመራ የፕሮጀክት ግምገማ ስርዓት ዘርግቶ ፕሮጀክቶቹን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የዚህ ፕሮግራም አካል የሆኑትና በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 10 እየተገነቡ ከሚገኙ ብዛታቸው 8 የሆኑ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ውስጥ የብሎክ 07 ሕንፃ በመልካም የግንባታ አፈፃፀሙ የሚጠቀስ ነው፡፡

ከተጀመረ የ2 ወራት ዕድሜ ያስቆጠረው ይህ ባለ አምስት ወለል ኢንዱስትሪያል ሼድ አሁን ላይ የስትራክቸራል ስራው ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ ሲሆን የብሎኬትና የልስን ስራዎች 2ኛ ፎቅ ከመድረሳቸውም በተጨማሪ በቀጣይ ቀናት ለሚከናወነው የጣርያ ስራ ውቅር እንደተጀመረ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ ካደረጋቸው ኢንተርፕራይዞች ውስጥ አንዱ በሆነው ሳዶር ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የግንባታ ስራው እየተከናወነ የሚገኘውና ቢኒያም፣ዶናት እና ጓደኞቻቸው የህንፃ አማካሪ ድርጅት በማማከር እየተሳተፉበት የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የፊዚካል አፈፃፀሙ 67 በመቶ ላይ መድረስ ችሏል፡፡

ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለት ይህ ህንፃ ቢሮው ባስቀመጠው የ120 ቀናት የኮንትራት ጊዜ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይችል ዘንድ በሳይቱ የምሽት ፈረቃ ተግባራዊ ተደርጎ የግንባታ ስራው እየተከናወነ ይገኛል፡፡……….
3👍1😁1