Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
#ማስታወቂያ

ለሁሉም ክፍለከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤቶች
1👍1
#ማስታወቂያ

በደብዳቤው ላይ ለተጠቀሳችሁ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት
3👍3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቢሮው የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ባደረጋቸው ኢንተርፕራይዞች እየተገነባ የሚገኘው የለሚከኩራ ወረዳ 06 ስምንት ኢንዱስትሪያል ሼዶች ግንባታ አፈፃፀም

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 07/2015


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍8
የቂርቆስ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ግንባታ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በቂርቆስ ክፍለከተማ ሜክሲኮ ገነት ሆቴል አካባቢ እያስገነባው የሚገኘው የወረዳ 11 2B+G+4 ጤና ጣቢያ ቀድሞ በግንባታ ሳይቱ የነበረውና ከወሰን ማስከበር እንዲሁም ከዲዛይን ያለመጣጣም ጋር የተገናኙ ችግሮች ተፈተው ጤና ጣቢያው ተጠናቆ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ የግንባታ ስራው በምሽት ፈረቃ ጭምር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

247,539,748.96 ብር የውለታ መጠን ተይዞለት በፍቃዱ ሙላቱ ሕ/ስ/ተቋራጭ የግንባታ ስራው እየተከናወነ የሚገኘው ጤና ጣቢያው አሁን ላይ 23 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን የአ/አ/ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የማማከሩን ኃላፊነት ወስዶ እየተከታተለ ይገኛል፡፡

በግንባታ ሳይቱ በአጠቃላይ 2ኛ ቤዝመንት የኮንክሪት ስራ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን የ1ኛ ቤዝመንት ወለል ስራ፣የውሀ ስርገት መከላከያ ስራዎች፣የአናፂና የብረት ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በሕንፃው ውስጥ የፋርማሲ፣የመዳኒት ስቶሮች፣የመኪና ፓርኪንግ፣ሬሳ ማቆያ ክፍሎች፣ቢሮዎች፣የምርመራ ክፍሎች፣የህጻናት ማቆያዎች፣ላብራቶሪ፣የስብሰባ አዳራሽ እና የመሳሰሉት አገልግሎት መስጫዎች የሚካተቱ ይሆናል፡፡.......
2👍2
.......ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 09/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍4
በግንባታ ሳይቶች ላይ እየተስተዋለ የሚገኘው የማህበራቱ አስደናቂ የመፈፀም አቅም፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ስራዎችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት ሰጥቶ ልዩ ክትትል እያደረገና ማሕበራቱም የተሰጣቸውን ድርብ ኃላፊነት በመወጣት ሀገራቸውንም እራሳቸውንም እየጠቀሙ ይገኛል፡፡

በዚህ ረገድ የማሕበራትን ቀደምት ስም የሚሽሩና አዲስ እይታን የሚፈጥሩ ውጤቶች በየግንባታ ሳይቱ እጠየተስተዋሉ ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያ በ3ር ከ15 ቀናት ጊዜያት ብቻ 96 በመቶ ፊዚካል አፈፃፀም ላይ የደረሰው የየካ ወረዳ 10 ሳላይሽ የመጀመሪያ ደረጃ G+4 ት/ቤት ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ፕሮግራም ተጠቃሚ በሆኑት አቻ ሁለገብ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እና ሲጫሌ ብሩክ እና ጓደኞቻቸው አማካሪ ማህበር አማካሪነት እንዲገነባ ከቢሮው ውል የታሰረለት ፕሮጀክቱ ከውለታ ጊዜው ቀድሞ ለመጠናቀቅ የሚያስችለው ቁመና ላይ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

በግንባታ ሳይቱ የሚቀሩትን የውስጥ ቀለም ስራ፣ የኤሌክትሪክ ፊቲንግ ገጠማ እና የደረጃ ማርብል ስራዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት ዕድሜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ በሁለት ፈረቃ እየተሰራ እንደሚገኝ የሚጠቅሱት የማሕበሩ ስራ አስኪያጅ ድርጅታቸው ይህንን ለማድረግ የሚያስችል በቂ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

120 ቀናት የማጠናቀቂያ ዕድሜ ተሰጥቶት ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የመስታወት ገጠማ፣የኮርኒስ ጂፕሰም ስራ እንዲሁም የሴራሚክ ስራዎች እየተጠናቀቁለት ይገኛል፡፡……..
👍84