Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
በማሕበራቱ ትጋት፣በአመራሩ ቁርጠኝነትና በቢሮው ያላሰለሰ ድጋፍና ክትትል ፕሮጀክቶች በሚታይ ደረጃ በተያዘላቸው ዕቅድ እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

ቢሮው የስራ ዕድል ፈጥሮ ማሕበራቱን ተጠቃሚ ማድረጉን ተከትሎ እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ በውድድርና በጊዜ የለም መንፈስ 24/7 በመስራት ፕሮጀክቶቻቸውን በተሰጣቸው ጊዜ ለማስረከብ ከጊዜ ጋር ትንቅንቅ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ዕውን መሆን እየሰሩ ውጤትም እያስመዘገቡ ይገኛል፡፡

ከዚህም መካከል ቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ ባደረጋቸው ማሕበራት እየተገነባ የሚገኘው የለሚኩራ ወረዳ 06 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ግንባታ ይገኝበታል፡፡

ይህ ግንባታ ብዛታቸው 6 የሆኑ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶችን በአንድ ላይ የያዘ ሲሆን በያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ አንድ አንድ ማሕበራት ተሳታፊ ሆነው የሚሰሩበት ሲሆን አንድ ሌላ ማሕበር በማማከር እያከናወኑት ይገኛል፡፡

እያንዳንዱ G+4 ሕንፃዎች 68 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው እኚህ ፕሮጀክቶች ስራቸው የተጀመረው የካቲት 19 ሲሆን በውለታው መሰረት ሰኔ 19 እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡

አጠቃላይ በሳይቱ ላይ የሚገኙት ስድስቱም ፕሮጀክቶቹ ከ409 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጁ ሲሆን አሁን ባላቸው አፈፃፀም በአማካኝ 39 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 03/2015 ዓ/ም


በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7
የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ግንባታን ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማዕከልን ተዋስኖ እየተገነባ የሚገኘው የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ በሚያስችል ዝርዝር የስራ ዕቅድ በመመራትና 24/7 መርህን በመከተል እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ 65 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

ከ225 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለትና በታቡ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በስኬል ኮንሰልቲንግ አርክቴክትና ኢንጂነርስ አማካሪነት እየተሰራ የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የብሎኬትና የልስን ስራዎች እየተጠናቀቁለት ሲሆን በተጨማሪም የመጨረሻ ወለል ስላብ ፎርም ዎርክ እንዲሁም የብረት ስራዎችም በመገባደድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ፕሮጀክቱ የጣራ ውቅርና የቆርቆሮ ማልበስ ስራዎች፣የማርብል ስራዎች፣የበርና መስኮት ገጠማዎችን የመሳሰሉ ዋና ዋና ተግባራት እና ሌሎች የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በቀጣይ የሚከናወኑለት ሲሆን ለዚህም ተግባራዊነት በግንባታ ሳይቱ የግብዓት አቅርቦትና ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡

ኮሚዩኒኬሽን ጉ/ዳ ግንቦት 03/2015

መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 04/2015


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2
እንቅልፍ የሸሹ እና ድካም የረሱ እንዲሁም ከፍተኛ የስራ ሞራል የሰነቁ ማሕበራት እዚህም እዚያም እየተስተዋሉ ፤ውጤትም እያስመዘገቡ ይገኛሉ፡፡

ቢሮው ልዩ ውሳኔ በመወሰን የስራ ዕድል ፈጥሮ ወደስራ ያሰማራቸው 140 ማሕበራት በተሰጣቸው ጊዜ ፕሮጀክቶቻቸውን አጠናቀው ለማስረከብ ከቀንም አልፈው በምሽት ፈረቃም ጭምር ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡

ለዚህም ማሳያ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 06 እየተገነቡ የሚገኙትን ብዛታቸው 8 የሆነ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶችን እያከናወኑ የሚገኙ ማሕበራት ጥሩ የፕሮጀክት አፈፃፀም እያስመዘገቡ መሆናቸውን መጥቀስ ይቻላል፡፡

8 ኢንዱስትሪያል ሼዶች በሚገነቡበት በዚህ ሳይት ላይ 8 ማሕበራት በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም 2 አማካሪ ማሕበራት በማማከር እየተሳተፉበት የሚገኙ ሲሆን ቢሮው ለያንዳንዱ G+4 ሕንፃ ግንባታ 68,500,000 ብር በመመደብ እያከናወነው ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ ከ540 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ተይዞላቸው እየተከናወኑ የሚገኙት G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶቹ ስራቸው የካቲት 19/2015 ተጀምሮ አሁን ላይ በአማካኝ 50 በመቶ አፈፃፀም ደረጃ ላይ መድረስ ችለዋል፡፡

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍51😁1