የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሚያስገነባው አዲስ ስቱዲዮ የመጀመሪያ ንድፍ ስራ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
የቀድሞው ትምባሆ ሞኖፖል በመባል በሚታወቀው ተቋም ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደአዲስ ለሚያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ መነሻነት በተዘጋጀው የመጀመሪያ መነሻ ንድፍ ከአሰሪ መስሪያቤት፣ከመጨረሻ ተጠቃሚ ተቋም እንዲሁም ዲዛይኑን ካዘጋጀው ድርጅት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሞያዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የባለቤትነት ሚናውን በመውሰድ ሊያከናውነው በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስቱዲዮ ግንባታ የውስጥ ዲዛይኑን ባዘጋጀው ጥበብ ዲዛይን መነሻ ንድፉ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድኩ ላይ የመነሻ ንድፉን ሊያዳብሩ የሚችሉ በርካታ ሀሳቦች ከስራ ኃላፊዎቹ እና ከባለሞያዎቹ ቀርቧል፡፡
በመድረኩ ሀሳብ ያነሱት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት አዲሱ የሚዲያ ተቋሙ መገኛ በአፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ የውጪ ሀገር ዜጎች አይን የሚያርፍበት እንደሆነና የከተማችንን ብቻም ሳይሆን የሀገራችንን ቀለም በሚገባ በሚወክል መልኩ መሰራት እንደሚኖርበት ገልፀው ይህንንም ዕውን ለማድረግ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ሌሎች አህጉር-ዓቀፍና ዓለም-ዓቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተሰሩበትን ሁኔታ መቃኘት ተገቢ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 02/2015 ዓ/ም
ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

👍10
በማሕበራቱ ትጋት፣በአመራሩ ቁርጠኝነትና በቢሮው ያላሰለሰ ድጋፍና ክትትል ፕሮጀክቶች በሚታይ ደረጃ በተያዘላቸው ዕቅድ እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
ቢሮው የስራ ዕድል ፈጥሮ ማሕበራቱን ተጠቃሚ ማድረጉን ተከትሎ እያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ በውድድርና በጊዜ የለም መንፈስ 24/7 በመስራት ፕሮጀክቶቻቸውን በተሰጣቸው ጊዜ ለማስረከብ ከጊዜ ጋር ትንቅንቅ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ዕውን መሆን እየሰሩ ውጤትም እያስመዘገቡ ይገኛል፡፡
ከዚህም መካከል ቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ ባደረጋቸው ማሕበራት እየተገነባ የሚገኘው የለሚኩራ ወረዳ 06 ኢንዱስትሪያል ሼዶች ግንባታ ይገኝበታል፡፡
ይህ ግንባታ ብዛታቸው 6 የሆኑ G+4 ኢንዱስትሪያል ሼዶችን በአንድ ላይ የያዘ ሲሆን በያንዳንዱ ፕሮጀክት ላይ አንድ አንድ ማሕበራት ተሳታፊ ሆነው የሚሰሩበት ሲሆን አንድ ሌላ ማሕበር በማማከር እያከናወኑት ይገኛል፡፡
እያንዳንዱ G+4 ሕንፃዎች 68 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው እኚህ ፕሮጀክቶች ስራቸው የተጀመረው የካቲት 19 ሲሆን በውለታው መሰረት ሰኔ 19 እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል፡፡
አጠቃላይ በሳይቱ ላይ የሚገኙት ስድስቱም ፕሮጀክቶቹ ከ409 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጁ ሲሆን አሁን ባላቸው አፈፃፀም በአማካኝ 39 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 03/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity
https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg

👍7
የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ግንባታ እየተፋጠነ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ እያስገነባቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ግንባታን ለማጠናቀቅ በርብርብ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማዕከልን ተዋስኖ እየተገነባ የሚገኘው የጀሞ ቁ.1 G+4 የእሳት አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ሕንፃ ፕሮጀክትን ለማጠናቀቅ በሚያስችል ዝርዝር የስራ ዕቅድ በመመራትና 24/7 መርህን በመከተል እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን አሁን ላይ 65 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ከ225 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘለትና በታቡ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማ ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በስኬል ኮንሰልቲንግ አርክቴክትና ኢንጂነርስ አማካሪነት እየተሰራ የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የብሎኬትና የልስን ስራዎች እየተጠናቀቁለት ሲሆን በተጨማሪም የመጨረሻ ወለል ስላብ ፎርም ዎርክ እንዲሁም የብረት ስራዎችም በመገባደድ ላይ ይገኛሉ፡፡
ፕሮጀክቱ የጣራ ውቅርና የቆርቆሮ ማልበስ ስራዎች፣የማርብል ስራዎች፣የበርና መስኮት ገጠማዎችን የመሳሰሉ ዋና ዋና ተግባራት እና ሌሎች የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ስራዎች በቀጣይ የሚከናወኑለት ሲሆን ለዚህም ተግባራዊነት በግንባታ ሳይቱ የግብዓት አቅርቦትና ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ኮሚዩኒኬሽን ጉ/ዳ ግንቦት 03/2015
መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ገፆች ይከተሉ፡፡

👍3