Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ የዘራው አዝመራ ወቀቱን ጠብቆ ፍሬ እያፈራ ይገኛል፡፡

**************************************************************
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በቅርቡ 140 ለሚሆኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ዕድል መፍጠሩን ተከትሎ በፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ላይ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 14 አባዶ ኮንዶሚኒየም ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውና 3,085 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ ለሚገኘው የጎዴ ት/ቤት ተጨማሪ ዓቅም ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው SB+G+4 ሕንፃ 94 በመቶ የአፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ በሆኑት ቢ.ጂ.ኤች.ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ሲጫሌ፣ብሩክ እና ጓደኞቻቸው በማማከር እያከናወኑት የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑለት ሲሆን የኳርትዝ ስራ፣የሴራሚክ ንጣፍ እንዲሁም የጂፕሰም ቦርድ ገጠማዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይ ቀናትም የኤሌክትሪክ ፊቲንግ፣የመስታወት ገጠማዎች፣የውስጥ ግድግዳ ቀለም ስራ እና የፅዳት ስራዎች እንደሚከናወኑ የተያዘው የስራ መርኃ-ግብር ያሳያል፡፡

በግንባታ ሳይቱ በቀሪዎቹ 10 ቀናት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የሚያስችል የግብዓት ክምችትና የሰው ኃይል ዝግጅት መኖሩን ለማየት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 26/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!
👍103
ቋሚ ኮሚቴው ቢሮው እያከናወነው የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ተመለከተ፡፡

==================================================
የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቢሮው በኢንተርናሽናል ደረጃ እያስገነባው የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ተመልክቷል፡፡

በከተማችን ብቻም ሳይሆን በሀገራችንም ጭምር በብቸኝነት ዓለም ዓቀፍ ደረጃንዎችን እንዲያሟላ ተደርጎ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት፣በዛምራ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በኔማድ ኮንሰልቲንግ አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ላይ ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

በመስክ ምልከታው ወቅት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዳስረዱት ይህን ዘርፈብዙ ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን ስቴዲየም የዓለም ዓቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን /FIFA/ እና የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን/CAF/ ባስቀመጡት መመዘኛ መስፈርቶች ልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ለማዋል ቢሮውና የሚመለከታቸው አካላት በጥምረት እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሰው በዚህ ረገድ የተሻለ ልምድ ካላቸው ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ አስፈላጊው ሁሉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡……….
👍3
…………የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ በበኩላቸው ይህን የኢትዮጵያውያን ሁሉ ሕልም የሆነውንና ከዚህ ቀደም የመጓተት ዕጣ ገጥሞት የነበረውን ስቴዲየም ዕውን ይሆን ዘንድ ቢሮውን እንዲሁም ለዚህ ፕሮጀክት ትልቅ ሞያዊ አበርክቶ እያደረገ የሚገኘውን ኔማድ ኮንሰልታንሲን በልዩነት አመስግነው በግንባታ ሳይቱ ላይ በተመለከቱት ለውጥ ትልቅ ተስፋ እንደሰነቁ በመጥቀስ በተያዘለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲውል ቢሮው ድጋፍና ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው በቋሚ ኮሚቴው ስም አሳስበዋል፡፡

ስቴዲየሙ አሁን ላይ 65 በመቶ አፈፃፀም ላይ መድረሱ በመርኃ-ግብሩ ላይ ተጠቅሷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 26/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍3
ሲሚንቶን ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ይወሰዳል፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
************************

የሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ አከፋፋዮች እና ችርቻሮ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

በዚህም ቢሮው በሲሚንቶ ምርት ላይ ከተተመነው ዋጋ በላይ በሚሸጡ የንግድ ድርጅቶች ላይ ከማሸግ ጀምሮ ሌሎች ሕጋዊ እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስታውቋል።

ኅብረተሰቡ በተለይም ሸማቾች ከተተመነው ዋጋ በላይ ከፍለው መሸመት እንደሌለባቸው እና ጉዳዩ ሲያጋጥማቸው በነፃ የስልክ ቁጥር 8588 በመደወል ጥቆማ እንዲያደርሱትም ጠይቋል።
👍132
የአዲስ_አበባ_ዲዛይንና_ግንባታ_ስራዎች_ቢሮ_#የሚያዝያ_ወር_ዜና_መፅሄት.pdf
6.5 MB
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የሚያዝያ ወር ዜና መፅሄት

በኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ

ሚያዝያ 30/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍8
የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃ እና የሲኒማ ኮምፕሌክስ 4B+G+8 ግንባታዎችን ቀሪ ስራዎች ለማከናወን የሚያስችል አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተካሂዷል፡፡

ቀድሞ ግንባታውን ያከናውን የነበረው ስራ ተቋራጭ እቴቴ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶቹ በተለያየ አፈፃፀም ደረጃ ላይ እያሉ አቋርጦ በመውጣቱ ምክንያት ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ መነሻ ሆነው የቆዩት የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ግንባታዎች አዲስ ውለታ የመፈራረም ስነስርዓት ተከናውኗል፡፡

ጉዳያቸው በፍርድቤት በመያዙ እንዲሁም በጨረታ ሂደቶች ምክንያት ለ16 ወራት ገደማ ተቋርጠው የቆዩት እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጨረታውን ካሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ጋር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ውለታ የማሰር ስነ-ስርዓት አካሂዷል፡፡

የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ህንፃን ከ833 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም የሲኒማ ኮምፕሌክስ ቀሪ ስራዎች ከ954 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የፕሮጀክት ውል መጠን ጨረታውን ያሸነፈው ባማኮን ኢንጂነሪንግ ስራዎቹን አጠናቆ ለማስረከብ የ6 ወራት ዕድሜ የተሰጠው ሲሆን ከፕሮጀክቱ አንገብጋቢነት አንፃር የሚሰጠው ቅድመ ክፍያ በጥምር ሂሳብ / Joint Account / የሚተዳደር ሆኖ ለግብዓት ግዢ ብቻ የሚውል መሆኑን ከስራ ተቋራጭ ጋር መግባባት ላይ እንደተደረሰና ይህም ወደፊት ሊከሰት ከሚችል የግብዓት ዋጋ ንረት እንደሚታደግ በስነ-ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡…….
👍82
……….የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በስነስርዓቱ ላይ እንዳሉት ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቢሮው ቢሮው በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አበክረው በማንሳት ለውጥኑ ስኬታማነት ሁሉንም አካላት በማስተባበር አስቻይና ሁሉን ዓቀፍ መደላድሎች እንዲፈጠሩ ቢሮው ከዛሬዋ ዕለት ጀምሮ እንቅስቃሴ ማድረጉን እንደሚጀምር አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት ቢሮው ቴክኒካል ድጋፍ ከማድረግም በዘለለ በልዩ ሁኔታ ሳምንታዊ የፕሮጀክት ግምገማ መርኃ-ግብር እንደሚኖር አሳስበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 30/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍42
የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በሚያስገነባው አዲስ ስቱዲዮ የመጀመሪያ ንድፍ ስራ ላይ ውይይት ተደረገ፡፡

የቀድሞው ትምባሆ ሞኖፖል በመባል በሚታወቀው ተቋም ውስጥ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደአዲስ ለሚያስገነባው ዘመናዊ ስቱዲዮ መነሻነት በተዘጋጀው የመጀመሪያ መነሻ ንድፍ ከአሰሪ መስሪያቤት፣ከመጨረሻ ተጠቃሚ ተቋም እንዲሁም ዲዛይኑን ካዘጋጀው ድርጅት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሞያዎች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የባለቤትነት ሚናውን በመውሰድ ሊያከናውነው በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስቱዲዮ ግንባታ የውስጥ ዲዛይኑን ባዘጋጀው ጥበብ ዲዛይን መነሻ ንድፉ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድኩ ላይ የመነሻ ንድፉን ሊያዳብሩ የሚችሉ በርካታ ሀሳቦች ከስራ ኃላፊዎቹ እና ከባለሞያዎቹ ቀርቧል፡፡

በመድረኩ ሀሳብ ያነሱት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም እንዳሉት አዲሱ የሚዲያ ተቋሙ መገኛ በአፍሪካ ሕብረት አቅራቢያ እንደመሆኑ መጠን በርካታ የውጪ ሀገር ዜጎች አይን የሚያርፍበት እንደሆነና የከተማችንን ብቻም ሳይሆን የሀገራችንን ቀለም በሚገባ በሚወክል መልኩ መሰራት እንደሚኖርበት ገልፀው ይህንንም ዕውን ለማድረግ በሀገር ውስጥ ብቻም ሳይሆን ሌሎች አህጉር-ዓቀፍና ዓለም-ዓቀፍ የሚዲያ ተቋማት የተሰሩበትን ሁኔታ መቃኘት ተገቢ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ግንቦት 02/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!
👍10