Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
ቢሮው 7 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የውል መጠን ያላቸውን ፕሮጀክቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት በመስጠት የግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ተወዳዳሪ እና በኢኮኖሚ ረገድም ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ለማብቃት በያዘው ውጥን መሰረት ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 140 በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማሕበራትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 140 ፕሮጀክቶችን በመስጠት ግንባታውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በማሕበራቱ እየተከናወኑ የሚገኙት ፕሮጀክቶች 3 ዓይነት ምድብ ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው 21 G+4 ትምህርት ቤቶች፣እያንዳንዳቸው ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው 70 G+4 ሁለገብ የማምረቻ ሼዶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘላቸው 49 G+0 የማምረቻ ሼዶች ይገኙበታል፡፡

ቢሮው ለ G+4 ፕሮጀክቶቹ የ 4 ወራት እንዲሁም ለ G+0 ፕሮጀክቶቹ ደግሞ የ45 ቀናት የማጠናቀቂያ ጊዜ የሰጠ ሲሆን በዚህ መነሻነት ለያንዳንዱ ማሕበር አንድ አንድ ፕሮጀክት በዕጣ ተደልድሎ እየተከናወነ በሚገኘው ስራ አስደናቂ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል፡፡……..
👍3
……….በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በዚህ በጀት ዓመት ሁሉም ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለታለመላቸው ዓላማ ይውሉ ዘንድ ቢሮው ተግባራዊ ባደረገው የምሽት ፈረቃ የስራ መርኃ-ግብር መሰረት በጥብቅ የስራ ስነምግባር እየተከናወነ ሲሆን አሁን ላይ 22 ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ከዚህ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ 35 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 25/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍5
ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ የዘራው አዝመራ ወቀቱን ጠብቆ ፍሬ እያፈራ ይገኛል፡፡

**************************************************************
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በቅርቡ 140 ለሚሆኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ዕድል መፍጠሩን ተከትሎ በፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ላይ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 14 አባዶ ኮንዶሚኒየም ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውና 3,085 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ ለሚገኘው የጎዴ ት/ቤት ተጨማሪ ዓቅም ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው SB+G+4 ሕንፃ 94 በመቶ የአፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ በሆኑት ቢ.ጂ.ኤች.ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ሲጫሌ፣ብሩክ እና ጓደኞቻቸው በማማከር እያከናወኑት የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑለት ሲሆን የኳርትዝ ስራ፣የሴራሚክ ንጣፍ እንዲሁም የጂፕሰም ቦርድ ገጠማዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይ ቀናትም የኤሌክትሪክ ፊቲንግ፣የመስታወት ገጠማዎች፣የውስጥ ግድግዳ ቀለም ስራ እና የፅዳት ስራዎች እንደሚከናወኑ የተያዘው የስራ መርኃ-ግብር ያሳያል፡፡

በግንባታ ሳይቱ በቀሪዎቹ 10 ቀናት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የሚያስችል የግብዓት ክምችትና የሰው ኃይል ዝግጅት መኖሩን ለማየት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 26/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!
👍103
ቋሚ ኮሚቴው ቢሮው እያከናወነው የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ተመለከተ፡፡

==================================================
የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የከተማ ልማት፣ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቢሮው በኢንተርናሽናል ደረጃ እያስገነባው የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ተመልክቷል፡፡

በከተማችን ብቻም ሳይሆን በሀገራችንም ጭምር በብቸኝነት ዓለም ዓቀፍ ደረጃንዎችን እንዲያሟላ ተደርጎ በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት፣በዛምራ ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም በኔማድ ኮንሰልቲንግ አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘውን የአቃቂ ስቴዲየም የግንባታ ሂደት ላይ ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

በመስክ ምልከታው ወቅት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዳስረዱት ይህን ዘርፈብዙ ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን ስቴዲየም የዓለም ዓቀፉ እግርኳስ ፌዴሬሽን /FIFA/ እና የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን/CAF/ ባስቀመጡት መመዘኛ መስፈርቶች ልክ ተገንብቶ ለአገልግሎት ለማዋል ቢሮውና የሚመለከታቸው አካላት በጥምረት እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቅሰው በዚህ ረገድ የተሻለ ልምድ ካላቸው ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ አስፈላጊው ሁሉ ማሻሻያዎች እየተደረጉ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡……….
👍3