Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሰውና በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ስራው ተጓቶ የቆየው የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ህንፃ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ ይውል ዘንድ የቢሮው ማኔጅመንት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ችግሮቹ ተፈተው ወደስራ በመመለስ ከውሳኔው በኋላ በነበረው 1 ወር በተሰሩ ስራዎች ፍሬያማ ውጤቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

በምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በ567.2 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ያረፈውና በቢ.ጂ.ኤም ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኤ.ቲ.ኤም አርክትክቶችና ኢንጂነሮች አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ባለ 8 ወለል ሕንፃ ባለፈወ 1 ወር በተሰሩ ስራዎች የሴራሚክ ወለል ንጣፍ ስራ፣የመጨረሻ ወለል የስርገት መከላከያና የሴራሚክ ስራ፣የሳኒተሪ ስራዎች፣የሴፕቲክ ታንክ ስራዎች፣የአርምስትሮንግ ኮርኒስ ስራዎች እና ሌሎችንም ስራዎች ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢ ኖሮት አምራችና ስኬታማ ትውልድ ማፍራት በሚያስችለው የጥራት ልክ እንዲጠናቀቅ የህንፃው ውጫዊ አካል እጅግ ውብ እና ማራኪ ገፅታን የመፍጠር ዓቅም ባለው Calla Contextra የቀለም ቅብ ስራ በ5 እጅ እየተከናወነለት የሚገኝ ሲሆን የግራናይትና የአልሙኒየም ስራዎችም ደረጃቸውን ጠብቀው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡………….
👍3👏21
………..የሳይት ስራ፣የሊፍት ገጠማ ፣የውሀ ፓምፕ ገጠማ፣የበር ገጠማ፣የመስኮት መስታወት ገጠማ፣የህንፃው የውስጥ ቀለም ስራ፣የጀነሬተር እና የመሳሰሉት ዋና ዋና ስራዎች በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በቀጣይ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

በተቋሙ ከፍተኛ አመራር ያላሰለሰ ክትትል እየተደረገለት የሚገኘውና ሲጠናቀቅ በክህሎት፣በዕውቀት እንዲሁም በስነምግባር የላቀ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ማሕበራዊ ፋይዳ የሚኖረው ይህ ፕሮጀክት ከ1 ወር ባነሰ ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይውል ዘንድ በከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ ሲሆን ፊዚካል አፈፃፀሙ 91.37 በመቶ ደርሷል፡፡


ቢ.ጂ.ኤም ኮንስትራክሽን ተመሳሳይ ንድፍ ያለውን የተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አውቶሞቲቭ ዎርክሾፕ ከቢሮው ጋር በነበረው ውል መሰረት ባሳለፍነው በጀት ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ማዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 24/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍10😁1
ቢሮው 7 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የውል መጠን ያላቸውን ፕሮጀክቶች በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት በመስጠት የግንባታ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ለወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ተወዳዳሪ እና በኢኮኖሚ ረገድም ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ለማብቃት በያዘው ውጥን መሰረት ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 140 በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማሕበራትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 140 ፕሮጀክቶችን በመስጠት ግንባታውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በማሕበራቱ እየተከናወኑ የሚገኙት ፕሮጀክቶች 3 ዓይነት ምድብ ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ63 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው 21 G+4 ትምህርት ቤቶች፣እያንዳንዳቸው ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያላቸው 70 G+4 ሁለገብ የማምረቻ ሼዶች እንዲሁም እያንዳንዳቸው ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን የተያዘላቸው 49 G+0 የማምረቻ ሼዶች ይገኙበታል፡፡

ቢሮው ለ G+4 ፕሮጀክቶቹ የ 4 ወራት እንዲሁም ለ G+0 ፕሮጀክቶቹ ደግሞ የ45 ቀናት የማጠናቀቂያ ጊዜ የሰጠ ሲሆን በዚህ መነሻነት ለያንዳንዱ ማሕበር አንድ አንድ ፕሮጀክት በዕጣ ተደልድሎ እየተከናወነ በሚገኘው ስራ አስደናቂ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል፡፡……..
👍3
……….በተያዘላቸው ዕቅድ መሰረት በዚህ በጀት ዓመት ሁሉም ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለታለመላቸው ዓላማ ይውሉ ዘንድ ቢሮው ተግባራዊ ባደረገው የምሽት ፈረቃ የስራ መርኃ-ግብር መሰረት በጥብቅ የስራ ስነምግባር እየተከናወነ ሲሆን አሁን ላይ 22 ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቅ ችለዋል፡፡

ከዚህ ፕሮግራም ጋር ተያይዞ 35 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 25/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍5
ቢሮው በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ የዘራው አዝመራ ወቀቱን ጠብቆ ፍሬ እያፈራ ይገኛል፡፡

**************************************************************
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በቅርቡ 140 ለሚሆኑ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ዕድል መፍጠሩን ተከትሎ በፕሮጀክቶቹ አፈፃፀም ላይ አመርቂ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 14 አባዶ ኮንዶሚኒየም ውስጥ እየተገነባ የሚገኘውና 3,085 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተናገደ ለሚገኘው የጎዴ ት/ቤት ተጨማሪ ዓቅም ይፈጥራል ተብሎ የሚጠበቀው SB+G+4 ሕንፃ 94 በመቶ የአፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

የቢሮው የስራ ዕድል ተጠቃሚ በሆኑት ቢ.ጂ.ኤች.ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ሲጫሌ፣ብሩክ እና ጓደኞቻቸው በማማከር እያከናወኑት የሚገኘው ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተከናወኑለት ሲሆን የኳርትዝ ስራ፣የሴራሚክ ንጣፍ እንዲሁም የጂፕሰም ቦርድ ገጠማዎች በመሰራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይ ቀናትም የኤሌክትሪክ ፊቲንግ፣የመስታወት ገጠማዎች፣የውስጥ ግድግዳ ቀለም ስራ እና የፅዳት ስራዎች እንደሚከናወኑ የተያዘው የስራ መርኃ-ግብር ያሳያል፡፡

በግንባታ ሳይቱ በቀሪዎቹ 10 ቀናት ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅና ለማስረከብ የሚያስችል የግብዓት ክምችትና የሰው ኃይል ዝግጅት መኖሩን ለማየት ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 26/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!
👍103