Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች እያሳዩት የሚገኙት የስራ እንቅስቃሴ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 12/2015 ዓ/ም


ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍52👎1
የጀነራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ሀውልት በይፋ ተመረቀ፡፡

የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ሀውልት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣የሀገር መከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸቸው በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡

‹‹ #ወታደር_ሀገር_እንጂ_ብሄር_የለውም ›› በሚለው አይረሴ ንግግራቸው በብዙዎች ዘንድ በስፋት የሚታወቁትና ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ እስከ ህልፈተ ህይወታቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ከተዋጊነት እስከተለያዩ የአዛዥነት ሚናዎች ያገለገሉት ጀነራል ሰዓረ መኮንን ለመታሰቢያቸው የቆመላቸው ሀውልት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጀነራል መኮንኑን መታሰቢያ ሀውልት በክብር ለማኖር በወሰደው ኃላፊነት ቦታ ከማዘጋጀት አንስቶ ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ በቦሌ መንገድ ሩዋንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ያሰራውን መታሰቢያ ሀውልት ባስመረቀበት መርኃ-ግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብረሀም በላይ እንዲሁም ባለቤታቸው ኮ/ል ፅጌ አለማየሁ ንግግር አድርገዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ባለቤታቸው ኮ/ል ፅጌ አለማየሁ እንደገለፁት የጀነራል መኮንኑን ታሪክ እየዘከረ ለትውልድ እንዲያስተላልፍ በማሰብ ይህን መታሰቢያ ሀውልት ዕውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለወሰዱት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በመከታተልና በማጠናቀቅ ረገድ ትልቅ ሚና ለተጫወተው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ያላቸውን ምስጋና በቤተሰቦቻቸው ስም አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 14/2015 ዓ/ም
👍73👎1
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች ቢሯችን እያስገነባው በሚገኘው የንፋስ ስልክ ላፍቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ፕሮጀክት ላይ ሳይት ኢንጂነር በመሆን ሲያገለግሉ በነበሩትና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን/ኢኮስኮ/ ባልደረባ በነበሩት ኢ/ር አንዱአለም ገዳሙ ሕልፈተ-ህይወት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለነፍሳቸው እረፍትን፤ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡
👍53🔥1
2015_3rd_Quarter_CIS_Roof_Work_Revised_Rate_Only_Direct_Cost.pdf
632 KB
የ2015 3ኛ ሩብ ዓመት የጣራ ክዳን (CIS Roof) ዋጋ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (Revised Direct Cost) ጥናት።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 16/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍132
ባለፉት 9 ወራት 217 ግንባታዎችን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ እንደተቻለ ተመላከተ፡፡

******************/////////////******************
የቢሮው ዋነኛ ተግባር የሆነው የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታን በተመለከተ በቢሮ ደረጃ 40 እንዲሁም በክፍለከተማ 137 ግንባታዎችን ባለፉት 9 ወራት ማጠናቀቅ እንደተቻለ ቢሮው በ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም የከተማዋን መሪ ፕላን መሰረት ያደረገ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከመገንባት አንፃር በማዕከልና በክፍለከተማ ለ228 ፕሮጀክቶች ዲዛይን ማዘጋጀት ከመቻሉም ባሻገር ለ205 ፕሮጀክቶች የአዋጪነት ጥናት ስራ እንደተሰራ ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በቢሮው የተከናወኑ የምህንድስና ግዢ ስራዎችን በተመለከተ 184 የውል ሰነድ የማዘጋጀትና ውል የማዋዋል ተግባር እንደተከናወነና 9 የግልፅ እንዲሁም 7 የውስን ጨረታ ሰነዶች ማዘጋጀት እንደተቻለ በሪፖርቱ ተጠቁሟል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዓቅም ከማሳደግ አንፃር በዘጠኝ ወራቱ ለ1,229 ስራ ተቋራጮች፣አማካሪዎችና ሞያተኞች በ16 የስልጠና ርዕሶች ዙሪያ የዓቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት እንደተቻለና ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ከቢሮው ዘርፍና ዳይሬክቶሬቶች ለመጡ 4,683 የግንባታ ግብዓት የዋጋ ተከላ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ባሻገር 3 ጊዜ የግንባታ ግብዓት ላይ ወቅታዊ ጥናት በማድረግ መረጃው በወቅቱ ተደራሽ እንደተደረገ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የግብዓት ፍተሻ በማከናወን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ክትትልን ለማሻሻል ከሚሰሩ ስራዎች ውስጥ 6,695 አይተሞች በቤተሙከራ በመፈተሽ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ ስራ እንደተሰራ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡….
👍43
…….ተያይዞም በጊዜ ማዕቀፉ በማዕከል ደረጃ 65 እንዲሁም በክፍለከተማ ደረጃ 319 በአጠቃላይ 384 በመንግስት በጀት የሚገነቡ ፕሮጀክቶች ላይ የክዋኔና ፋይናንሺያል ኦዲት ስራዎችን እንደተሰሩና በዚህም በማዕከል 4.2 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በክፍለከተማ 443,600.43 ብር የኦዲት ግኝት መገኘቱን ከቀረበው ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቢሮው ትኩረት እየሰጠው ከሚገኘው የስራ ዕድል ፈጠራ አንፃር በዘርፉ ለ15,941 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ ዕድል በመፍጠር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የገበያ ትስስር ማሳካት እንደተቻለ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7
የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ግንባታን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በበጀት ዓመቱ እያከናወናቸው ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል የሚጠቀሰውና በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ስራው ተጓቶ የቆየው የምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ G+7 ህንፃ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ ይውል ዘንድ የቢሮው ማኔጅመንት ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት ችግሮቹ ተፈተው ወደስራ በመመለስ ከውሳኔው በኋላ በነበረው 1 ወር በተሰሩ ስራዎች ፍሬያማ ውጤቶች በመመዝገብ ላይ ናቸው፡፡

በምስራቅ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ በ567.2 ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ያረፈውና በቢ.ጂ.ኤም ኮንስትራክሽን ስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኤ.ቲ.ኤም አርክትክቶችና ኢንጂነሮች አማካሪነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ባለ 8 ወለል ሕንፃ ባለፈወ 1 ወር በተሰሩ ስራዎች የሴራሚክ ወለል ንጣፍ ስራ፣የመጨረሻ ወለል የስርገት መከላከያና የሴራሚክ ስራ፣የሳኒተሪ ስራዎች፣የሴፕቲክ ታንክ ስራዎች፣የአርምስትሮንግ ኮርኒስ ስራዎች እና ሌሎችንም ስራዎች ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ተቋሙ ምቹ የመማር ማስተማር ከባቢ ኖሮት አምራችና ስኬታማ ትውልድ ማፍራት በሚያስችለው የጥራት ልክ እንዲጠናቀቅ የህንፃው ውጫዊ አካል እጅግ ውብ እና ማራኪ ገፅታን የመፍጠር ዓቅም ባለው Calla Contextra የቀለም ቅብ ስራ በ5 እጅ እየተከናወነለት የሚገኝ ሲሆን የግራናይትና የአልሙኒየም ስራዎችም ደረጃቸውን ጠብቀው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡………….
👍3👏21