Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
👍3
farmers pdf.pdf
319.9 KB
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያና የእንስሳት ተዋፅዖ ማምረቻ ማዕከል ግንባታን በተመለከተ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ ያሰናዳውን ዘገባ ይመልከቱ፡፡
👍6👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተከትሎ በማሕበራቱ እየተከናወኑ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 10/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍6❤1
Audio
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በቢሮው የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ቁመና በተለይም በ60 እና 90 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከኤፍ ኤም 97.1 ራዲዮ ጋር ያደረጉት አጭር ቆይታ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 10/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍7❤1
ከተለያዩ ክፍለከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ በመገንባት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ ፡፡

በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በተዘጋጀው በዚህ ጉብኝት ወጣቱ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ-ልማት ግንባታዎችን እንዲያውቅና ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡትን የልማት ስኬቶች እንዲረዳ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

በወጣቶቹ ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች ውስጥ በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እየተገነቡ የሚገኙት የኮልፌ መንዲዳ እና የንፋስ ስልክ ጠቅላላ ሆስፒታሎች እንዲሁም የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለወጣቶቹ ፕሮጀክቶች ባስጎበኙበት ወቅት እንዳሉት ቢሮው በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ500 በላይ ፕሮጀክቶችን ከ17 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማስገንባት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ከዚህ ውስጥም 7 ቢሊየን ብር ገደማው የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይውል ዘንድ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ 125 ኢንተርፕራይዞች የስራ ትስስር የተፈጠረበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪ በትልልቅ ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት፣በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፣በመንገዶ ባለስልጣን እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የጉብኝቱ አካል ሆነው ውለዋል፡፡

ሚያዝያ 11/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍9❤1👎1
❤1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች እያሳዩት የሚገኙት የስራ እንቅስቃሴ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 12/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍5❤2👎1
የጀነራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ሀውልት በይፋ ተመረቀ፡፡

የቀድሞው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ሀውልት የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች፣የሀገር መከላከያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦቻቸቸው በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡

‹‹ #ወታደር_ሀገር_እንጂ_ብሄር_የለውም ›› በሚለው አይረሴ ንግግራቸው በብዙዎች ዘንድ በስፋት የሚታወቁትና ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ እስከ ህልፈተ ህይወታቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ከተዋጊነት እስከተለያዩ የአዛዥነት ሚናዎች ያገለገሉት ጀነራል ሰዓረ መኮንን ለመታሰቢያቸው የቆመላቸው ሀውልት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጀነራል መኮንኑን መታሰቢያ ሀውልት በክብር ለማኖር በወሰደው ኃላፊነት ቦታ ከማዘጋጀት አንስቶ ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ በቦሌ መንገድ ሩዋንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ያሰራውን መታሰቢያ ሀውልት ባስመረቀበት መርኃ-ግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብረሀም በላይ እንዲሁም ባለቤታቸው ኮ/ል ፅጌ አለማየሁ ንግግር አድርገዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ባለቤታቸው ኮ/ል ፅጌ አለማየሁ እንደገለፁት የጀነራል መኮንኑን ታሪክ እየዘከረ ለትውልድ እንዲያስተላልፍ በማሰብ ይህን መታሰቢያ ሀውልት ዕውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለወሰዱት የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በመከታተልና በማጠናቀቅ ረገድ ትልቅ ሚና ለተጫወተው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ያላቸውን ምስጋና በቤተሰቦቻቸው ስም አስተላልፈዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 14/2015 ዓ/ም
👍7❤3👎1