Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
በተለወጠ የስራ ባህል እራስንም ሀገርንም መጥቀም እንደሚቻል በተጨባጭ እያረጋገጡ የሚገኙት የስራ ዕድል ተጠቃሚ ማሕበራቱ አሁንም ውጤቶችን እያስመዘገቡ ነው፡፡

ለከተማው የት/ት ስርጭትና ተደራሽነት ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱ የሚጠበቁት የት/ቤት ግንባታዎች በፍጥነትና በስፋት እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 14 አባዶ ኮንዶሚኒየም 3,085 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኘውና በአንድ ክፍል ውስጥ 59 ተማሪዎችን የሚያስተናግደው የጎዴ ት/ቤት አዲስ SB+G+4 ሕንፃ በአስገራሚ ፍጥነት እየተገነባለት ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በመጀመሪያው ዙር የስራ ዕድል ካመቻቸላቸው ማሕበራት ውስጥ የሚጠቀሱት ቢ.ጂ.ኤች.ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በስራ ተቋራጭነት እያከናወኑት የሚገኘውና ሲጫሌ፣ብሩክ እና ጓደኞቻቸው ኮ/ማ/ማ የማማከር ስራውን የሚሰሩት ይህ ፕሮጀክት አሁን ላይ 80 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ የውለታ መጠን ያለው ፕሮጀክቱ የተሰጠው የ120 ቀናት ዕድሜ ሲሆን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በግንባታ ሳይቱ ላይ የምሽት ፈረቃ ስራ ተግባራዊ ተደርጎ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ህንፃው አሁን ላይ ጣራ የማልበስ ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ የብሎኬት እና የልስን ስራዎች 4ኛ ወለል ላይ የደረሱ ሲሆን 3ኛ ወለል የቻክ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ኮሙኒኬሽን ጉ/ዳ/ሚያዝያ 03/2015 ዓ/ም

መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
5👍4
ቢሮው ከፊታችን ባሉት ቀናት የሚከበሩትን ሀይማኖታዊ በዓላት ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት አድርጓል፡፡

በመጪው ቀናቶች በክርስትና እና በእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በከፍተኛ ሀይማኖታዊ ስርዓቶች በድምቀት የሚከበሩትን የትንሳዔ እና የኢድ አል ፈጥር በዓላትን ምክንያት በማድረግ ቢሮው ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ ሰራተኞቹ የማዕድ ማጋራት አከናውኗል፡፡

በዚህም መሰረት ለ96 የተቋሙ ሰራተኞች በዓላቱን ምክንያት በማድረግ 15 ኪሎ ዱቄትና 5 ሊትር ዘይት ተሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በማዕድ ማጋራት ስነስርዓቱ ላይ ለሁለቱም ዕምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ የማዕድ ማጋራቱ እኛ ኢትዮጵያውያን በዓላትን አብሮ የመብላት የኖረ ዕሴታችንን የሚወክል ነው ያሉ ሲሆን እነዚህን የመተሳሰብ፣የመደጋገፍና አብሮ የመብላት ድንቅ ዕሴቶቻችንን ዓቅም በፈቀደ መጠን ጠብቀናቸው ለትውልድ ልናስተላልፋቸው ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 05/2015 ዓ/ም

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍52
farmers pdf.pdf
319.9 KB
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያና የእንስሳት ተዋፅዖ ማምረቻ ማዕከል ግንባታን በተመለከተ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ ያሰናዳውን ዘገባ ይመልከቱ፡፡
👍6👎1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የስራ ዕድል መፍጠሩን ተከትሎ በማሕበራቱ እየተከናወኑ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል ጥቂቶቹ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 10/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍61
Audio
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በቢሮው የፕሮጀክቶች አፈፃፀም ቁመና በተለይም በ60 እና 90 ቀናት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከኤፍ ኤም 97.1 ራዲዮ ጋር ያደረጉት አጭር ቆይታ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ሚያዝያ 10/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍71
ከተለያዩ ክፍለከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ በመገንባት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ ፡፡

በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ በተዘጋጀው በዚህ ጉብኝት ወጣቱ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ-ልማት ግንባታዎችን እንዲያውቅና ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡትን የልማት ስኬቶች እንዲረዳ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

በወጣቶቹ ከተጎበኙት ፕሮጀክቶች ውስጥ በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እየተገነቡ የሚገኙት የኮልፌ መንዲዳ እና የንፋስ ስልክ ጠቅላላ ሆስፒታሎች እንዲሁም የአቃቂ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለወጣቶቹ ፕሮጀክቶች ባስጎበኙበት ወቅት እንዳሉት ቢሮው በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ ከ500 በላይ ፕሮጀክቶችን ከ17 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በማስገንባት ላይ እንደሚገኝ አስታውሰው ከዚህ ውስጥም 7 ቢሊየን ብር ገደማው የወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይውል ዘንድ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ 125 ኢንተርፕራይዞች የስራ ትስስር የተፈጠረበት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪ በትልልቅ ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት፣በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፣በመንገዶ ባለስልጣን እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የጉብኝቱ አካል ሆነው ውለዋል፡፡

ሚያዝያ 11/2015

ለከተማችን መሻሻል እንሰራለን!!!! Dedicated for the betterment of our City!!!!

የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍91👎1