Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.1K photos
193 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
🆕የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተለያዩ ወረዳዎች ለሚያሰራቸው ጤና ጣቢያዎች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ህጋዊና ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት (Calendar Day)ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ 8ኛ ፎቅ ምሕንድስና ግዥ ዘርፍ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ)በመክፈል መውሰድና መወዳደር እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የካቲት 22/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍11
ኢ.ቢ ኤስ. (EBS)ቴሌቪዥን ሙሉበሙሉ ከምድር በታች የተገነባውንና የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት አስገንብቶት በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ባለ4 ወለሉን የትራፊክ ማኔጅመንት ሕንፃ የግንባታ ሂደት የተመለከተ ዘገባ ለመስራት በግንባታ ሳይቱ ላይ መረጃዎችን እየወሰዱ ይገኛል።


ግንባታውን በተመለከተ የቢሮው የኮንትራት አስተዳደር ቡድን መሪ እና የፕሮጀክቱ ተቆጣጣሪ መሀንዲስ ኢ/ር ማዕረጉ ሰለሞን ለጋዜጠኞቹ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የካቲት 22/2015 ዓ/ም
👍9
እንኳን ለዓለም ዓቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ አደረሰን

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የካቲት 28/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍5
ለማህበራት በዕጣ የተላለፉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ዕቅድ፣ የጥራት ደረጃ እና በጀት ተጠናቀው ለርክክብ ዝግጁ መደረግ እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በቅርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን በዕጣ ማስተላለፉን ተከትሎ ሳምንታዊ የፕሮጀክት አፈፃፀም ገምግሟል፡፡

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኮንትራት አስተዳደር ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ዲሜጥሮስ ታደሰ በፕሮጀክት ግምገማው ላይ እንዳሉት ፕሮጀክቶቹን በተቀመጠላቸው የጊዜ ዕቅድ፣ በተያዘላቸው በጀት እንዲሁም በሚጠበቀው የጥራት አጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ አንስተው ይህን ዕውን ለማድረግ ቢሮው ያልተገደበ ድጋፉን እያደረገ እንደሚገኝ በተግባር እያሳየ መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡

በዛሬው ሳምንታዊ የፕሮጀክት ግምገማ መድረክ ማሕበራቱ በስራ ሂደታቸው ላይ ስላጋጠማቸው ተግዳሮቶችና ሌሎች ምቹ ሁኔታዎች ያነሱ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩትን ማሕበራት በመድረኩ በማበረታታትና ክፍተት የታየባቸውን ወደፊት ለማምጣት የሚያስችል ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የካቲት 29/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍12
በለሚኩራ ክፍለከተማ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

በለሚኩራ ክፍለከተማ በ90 ቀናት ዕቅድ ተይዘው ግንባታቸውሲከናወን የቆዩ የልማት ስራዎች በዛሬው ዕለት በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በይፋ ተመርቀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ በልበ መልካም ባለሀብቶች ፋይናንስ አቅራቢነትና በክንደ ብርቱ የሀገር ልጆች ትጋት በ 3 ወራት ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ የተደረገው የጋራ መኖሪያ ቤት ይገኝበታል፡፡

ህዝባቸውን የሚወዱ ባለሃብቶች ከፍተኛ መዋለ-ንዋይ መድበው ያሰሯቸውና 240 ቤቶችን የያዙ 6 ባለ 5 ወለል ሕንፃዎች በዛሬው ዕለት ተመርቀው ተጠቃሚዎቹ ከክብርት ከንቲባ እጅ ቁልፍ ተረክበዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በክፍለከተማው በተለይ በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲፈታ ታስቦ ግንባታው ተጠናቆ የነበረውንና በቅርቡ የመቃጠል አደጋ ደርሶበት ሕንፃ በዛሬው ዕለት በይፋ ከተመረቁት ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን እጅግ በተዋበና አስፈላጊው ቴክኖሎጂዎች ተሟልተውለት የመሬት አስተዳደር ስርዓቱን ሙሉ ለሙሉ ዲጂታላይዝድ የማድረግ ዓቅም ተላብሶ በይፋ ተመርቋል፡፡

ከነዚህ በተጨማሪ የምገባ ማዕከልና የዳቦ ፋብሪካን ጨምሮ ሌሎች በ90 ቀናት ዕቅድ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበ በዛሬው ዕለት ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት መጋቢት 01/2015
👍7