Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
197 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የአቃቂ እህል መካዘን ፕሮጀክት የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው ባጃጅ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የእህል መካዘን ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራን ጨምሮ ሌሎች የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩለት ይገኛል፡፡

በ9183.5 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ፕሮጀክቱ ለመካዘን፣ለመሸጫ እና ለወፍጮ አገልግሎት የሚውሉ 4 የተለያዩ ብሎኮች ያሉት ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ G+1 የቢሮ እና የካፍቴሪያ ሕንፃና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገባው የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት አሁን ላይ 98 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአስፋልት ስራውን የማጠናቀቅ እንዲሁም የአጥር ኳርትዝ ስራ እና አንዳንድ የለቀማ ስራዎች በቀጣይ አምስት ቀናት ውስጥ ተከናውነው ለርክክብ ዝግጁ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ከቢሮው የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ተረክቦ የሚያስተዳድረው ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 18/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክትን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማዋል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክትን አስፈላጊውን መሰረተ ልማቶች አሟልቶ ለማስረከብ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ በማዕከሉ ውስጥ ተግባራዊ ለሚደረገው ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ የሚውሉ የዶሮ ጎጆዎች፣መመገቢያ እና ውሃ መጠጫዎች የምርት ሂደት ጎንለጎን እየተከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የA-አይነት የዶሮ ጎጆዎች፣መመገቢያ እና አውቶማቲክ ውሀ መጠጫዎች፣ጋልቫናይዝድ ሽቦ ሳጥኖች እና የመመገቢያ ገንዳዎች እንዲሁም RHS መወጠሪያና መቆሚያ ምርቶች እየተመረቱ ይገኛሉ፡፡

የዶሮ ዕርባታው እያንዳንዱ ዩኒት 160 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን የሚይዙ 297 ዩኒቶች የሚኖሩት ሲሆን በዚህም አጠቃላይ 47,250 ዶሮዎችን የመያዝ ዓቅም አለው፡፡

በማዕከሉ የእንቁላል ዶሮዎች ሼዶችን ጨምሮ የወተት ለሞች እና የእርድ የከብቶች ማደለብያ በአጠቃላይ 38 ሼዶች እንዲሁም 40 የምርት ማሳያ ሱቆች ተገንብተው ተጠናቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 18/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍1
🔊መረጃ

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያሰራው የሚገኘውና መልካም አፈፃፀም እየታየበት የሚገኘውን የኮልፌ መንዲዳ አጠቃላይ ሆስፒታል የግንባታ አፈፃፀምን በተመለከተ #ፋና_ቴሌቪዥን በ6:00ሰዓት የቀትር ዜና ስርጭቱ ላይ ከግንባታ ሳይቱ በቀጥታ ስርጭት የሚያስተላልፈውን ዘገባ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን።

ጥር 22/2015 ዓ/ም
Forwarded from Bizuayehu G.
ከደቂቃዎች በኋላ በቀጥታ ስርጭት አየር ላይ ለሚውለው የኮልፌ መንዲዳ አጠቃላይ ሆስፒታል የግንባታ አፈፃፀም ቅድመ ዝግጅትና የስርጭት ቴክኒክ ሙከራ በመደረግ ላይ።