Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
197 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
በለያዩ ቦታዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ጅምር ግንባታዎች የእንቅስቃሴ ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተደርጓል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም በቅርቡ በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የተሰጡ G+4 የመማሪያ ሕንፃዎችን፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ሼዶችን እንዲሁም በተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶች ወጪ እየተገነቡ የሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የግንባታ ሂደት ለመገምገም ያለመ የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ቢሮ ኃላፊዋ በምልከታቸው በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 08 ሰሚት ፔፕሲ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሆራ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ፋይናንስ አቅራቢነትና በዳዊት እምሩ ኮንስትራክሽን ድርጅት ስራ ተቋራጭነት በመገንባት ላይ የሚገኘውን ጨምሮ በአያት ሪልስቴት፣በአልሳም ሪልስቴት፣በአሰር ኮንስትራክሽን፣በጊፍት ሪልስቴት እንዲሁም በውሀና ፍሳሽ እየተገነቡ የሚገኙና ከ2 ወራት ባነሰ ጊዜ በልዩ አፈፃፀም ተገንብተው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙትን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ተመልክተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ቢሮው በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የስራ ትስስር ፈጥሮ ግንባታቸው በመጀመር ላይ የሚገኙትን በለሚኩራ ክፍለከተማ የሚገኙትን የጎዴ ትምህርት ቤት፣ወረዳ 04 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ወረዳ 04 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ወረዳ 06 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመለከቱ ሲሆን የካ ወረዳ 10 ሳላይሽ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተጨማሪም ኮልፌ ክፍለከተማ የሚገኘውን የህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤቶች ውስጥ የተጀመሩትን የ G+4 ሕንፃ ጅምር ስራዎች ተመልክተዋል....
👍21🔥1
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 14/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
#የጨረታ_ማስታወቂያ

ቢሮው በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ የሚገነባውን B+G+10 የአርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ማዕከል ግንባታን ለማከናወን ፍላጎት ያላቸውን ስራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾችን እየጋበዘ ጥር 11 /2015 የወጣውን ሄራልድ ጋዜጣ መመልከት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
ቢሮው ተግባራዊ ባደረገውና የስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ በሆኑ ማሕበራት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ለሚገነባው የመስሪያ ቦታ ግንባታ የአፈር ቆረጣ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 17/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍1
የአፈርና የማቴሪያል ጥራት ፍተሻዎችን በተመጣጣኝ ክፍያ በስፋት እያከናወነ የሚገኘውና በሰለጠነ የሰው ኃይል እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የግንባታ ግብዓት ጥራት ፍተሻ ማዕከል በኢንዱስትሪው ተሳታፊ የሆኑ የመንግስት ተቋማትን፣ድርጅቶችን እንዲሁም የግል አልሚዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

አድራሻ፡-ከጀርመን አደባባይ ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍1
የአቃቂ እህል መካዘን ፕሮጀክት የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው ባጃጅ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እየተገነባ የሚገኘው የእህል መካዘን ፕሮጀክት የአስፋልት ንጣፍ ስራን ጨምሮ ሌሎች የማጠናቀቂያ ስራዎች እየተሰሩለት ይገኛል፡፡

በ9183.5 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ፕሮጀክቱ ለመካዘን፣ለመሸጫ እና ለወፍጮ አገልግሎት የሚውሉ 4 የተለያዩ ብሎኮች ያሉት ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ G+1 የቢሮ እና የካፍቴሪያ ሕንፃና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ተሟልተውለታል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገባው የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት አሁን ላይ 98 በመቶ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን የአስፋልት ስራውን የማጠናቀቅ እንዲሁም የአጥር ኳርትዝ ስራ እና አንዳንድ የለቀማ ስራዎች በቀጣይ አምስት ቀናት ውስጥ ተከናውነው ለርክክብ ዝግጁ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ከቢሮው የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ተረክቦ የሚያስተዳድረው ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 18/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
👍2
የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክትን አጠናቆ ለአገልግሎት ለማዋል የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

የልማት ተነሺ አርሶአደሮች ማቋቋሚያ ፕሮጀክትን አስፈላጊውን መሰረተ ልማቶች አሟልቶ ለማስረከብ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ከዚህም ውስጥ በማዕከሉ ውስጥ ተግባራዊ ለሚደረገው ዘመናዊ የዶሮ ዕርባታ የሚውሉ የዶሮ ጎጆዎች፣መመገቢያ እና ውሃ መጠጫዎች የምርት ሂደት ጎንለጎን እየተከናወነ ይገኛል፡፡

አሁን ላይ የA-አይነት የዶሮ ጎጆዎች፣መመገቢያ እና አውቶማቲክ ውሀ መጠጫዎች፣ጋልቫናይዝድ ሽቦ ሳጥኖች እና የመመገቢያ ገንዳዎች እንዲሁም RHS መወጠሪያና መቆሚያ ምርቶች እየተመረቱ ይገኛሉ፡፡

የዶሮ ዕርባታው እያንዳንዱ ዩኒት 160 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን የሚይዙ 297 ዩኒቶች የሚኖሩት ሲሆን በዚህም አጠቃላይ 47,250 ዶሮዎችን የመያዝ ዓቅም አለው፡፡

በማዕከሉ የእንቁላል ዶሮዎች ሼዶችን ጨምሮ የወተት ለሞች እና የእርድ የከብቶች ማደለብያ በአጠቃላይ 38 ሼዶች እንዲሁም 40 የምርት ማሳያ ሱቆች ተገንብተው ተጠናቀዋል፡፡