Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።


ለከተማው ሕብረተሰብ ዘርፈብዙ ፋይዳ ያላቸውና በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተገነቡ የሚገኙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ ሂደት በዛሬው ዕለት በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተጎብኝቷል።


በምልከታው በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮስኮ) እየተገነቡ የሚገኙት የኮልፌ መንዲዳ ሆስፒታል፣የላፍቶ ሆስፒታል፣የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ማዕከል ምዕራፍ 2 ግንባታ ፣ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ማቋቋምያ ማዕከል ፕሮጀክቶች ተካተዋል።


በምልከታው በተለይ በሆስፒታሎቹ የግንባታ ሂደት ላይ የተስተዋለውን መዘግየት በአስቸኳይ በሚፈታበት አግባብ ዙሪያ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ፣ የስራ ተቋራጩ እንዲሁም የአማካሪ ድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችን ያሳተፈና ተስፋ ሰጪ ውይይት ተደርጓል።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታሕሳስ 23/2015 ዓ/ም


በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
በስልጠና የዳበረ እውቀት ለስራ ውጤታማነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡

በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እውቀትና ክህሎታቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች ሲያዳብሩና ሲያሻሽሉ በዘርፉ አመርቂ ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡

ይህን የተረዳው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት የፈፃሚዎችን የመፈፀም አቅም እንዲሻሻል እያረገ ይገኛል፡፡

ቢሮው የያዝነውን ሳምንት ጨምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት ከቢሮውና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የኮንትራት አስተዳደር ፣ የፕሮጀክት ኦዲት ፣ የምህንድስና ግዥ ፣ የላብራቶሪ እንዲሁም የዲዛይንና ዋጋ ተከላ ባለሙያዎች በ FIDIK, tender and bid procedure, construction manual, , PPA contract administration, claim and dispute resolution, ዙሪያ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ከ110 በላይ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት እና ከስራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተውጣጡ ሰራኞችም ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

ስልጠናው የስራ ተነሳሽነትን የሚፈጥር፣ አነቃቂ እንዲሁም ጉድለቶችን በመለየት የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል እንደሆነ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታህሳስ 25/2015 ዓ.ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
👍2
2015 2nd Quarter Construction Works (Only Direct Cost).pdf
24.3 MB
የ2015 ዓ.ም 2ኛ ሩብ ዓመት የግንባታ ሥራዎች የቀጥተኛ ዋጋ (Direct Cost) ጥናት

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ታሕሳስ 30/2015 ዓ/ም
👍101
ዜና መፅሄት.pdf
17.2 MB
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ #የመጀመሪያ_ግማሽ_ዓመት_ዜና_መፅሄት

ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጥር 04/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity

https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg
1👍1
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞግስ፤ አቶ ታከለ ኡማ፤ አቶ ኡመር ሁሴን እና አቶ ተፈሪ ፍቅሬን ዛሬ በክብር ሸኝቷቸዋል።

በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት አራቱንም የምክር ቤት አባላት ቀጣይ ጉዟቸው ስኬታማ እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።

#PMOEthiopia
Forwarded from Bizuayehu G.
ሰበር ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በጥቅሉ ስምንት በሙስና የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!!

አመራሮች
1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ
2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ

ፈፃሚዎች
3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)
4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)
6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)
7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)
8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡
የተጀመረው ህግን የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ የፀረ ሙስና ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

ምንጭ የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
1👍1
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ሁለተኛውን መስቀል አደባባይ ማለትም የለሚ ፓርክ ግንባታን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል፡፡


ብቸኛ የህዝብ አደባባይ የነበረውን የመስቀል አደባባይ የሚደግም ሁለተኛ ታላቅ ፕሮጀክት በ1.3 ቢሊዮን ብር በጀት በዛሬው እለት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት በይፋ ተጀምሯል፡፡


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ውጪ ሃገር ያሉ ፕሮጀክቶችን ስንመለከት ለሃገራችን ብለን እንመኝ ነበር ያሉ ሲሆን ነገር ግን በመመኘት ውጤት አይመጣም በመስራት ነው እንጂ ብለዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት መሃል ከተማ ያሉ ብቻ ናቸው የሚዋቡ የሚለውን ምላሽ የሚሰጥ ነው ዳር ላሉ የከተማዋ አካባቢዎችም እንዲህ አይነት ስፍራ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡


መስቀል አደባባይ በሚመረቅበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባስተላለፊት መልዕክት ተጨማሪ መስቀል አደባባዮች ለከተማዋ ያስፈልጓታል ብለው በተናገሩት መሰረት ቃላቸውን ፈፅመን ይህን ፕሮጀክት ዛሬ የመሰረት ድንጋይ እናስቀምጣን ብለዋል፡፡


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች ቦታው የተመረጠበት ዋነኛ ምክንያት አዲስ አፍሪካ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እዚህ አካባቢ እየተገነባ ያለ በመሆኑ ነውና አከባቢው ተጨማሪ አገልግሎቶችና ተያይዘው የሚመጡ ስፍራዎች የሚያስፈልጉት መሆኑንም አውስተዋል፡፡


በአሮጌ ወይም ባለፈበት አስተሳሰብ ከተማችን ልንቀይር አንችልም ያሉት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከዘመኑ ጋር የዘመነ አሰራርና አስተሳሰብ በመያዝ ነው መቀየር የሚቻለው በመሆኑም የግሉን ሴክተር በማሳተፍ የመንግስትን ክፍተት በመሙላት እና በአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ነው ሲሉ ተናግረዋል….
👍2