Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.2K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
PPA 2011ላይ መነሻ ተደርጎ በቢሮው እየተጠና የሚገኘው የ standard bid document የመጀመሪያ ረቂቅ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በቢሮ ደረጃ ወጥ የሆነ የጨረታ ሰነድ እንዲኖርና ለውለታ አስተዳደር ስራው ምቹ እና ግልፅ መደላድል እንዲፈጥር ታስቦ እየተዘጋጀ የሚገኘው ስታንዳርድ የመጀመሪያ ረቂቅ በዛሬው ዕለት የቢሮው አመራሮችና ከምህንድስና ግዢ፣ከኮንትራት አስተዳደር፣ ከኢንዱስትሪ ቁጥጥር ልማት ዘርፎችእንዲሁም ከዲዛይን ጥራት ቁጥጥር የተወከሉ ባለሞያዎች በተገኙበት የቀረበ ሲሆን ሰነዱን ለማዳበር የሚያችሉ አስተያየቶች እና ግብዓቶች ተሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታሕሳስ 14/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
ለመቆጣጠር በሚል በኬላዎች ሲሚንቶን መያዝ ‹‹በጥብቅ›› ተከለከለ

በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ጸድቆና ተግባራዊ ተደርጎ ሲሠራበት የነበረው የሲሚንቶ አቅርቦትና ሥርጭት መመርያ ተቀይሮ፣ ሲሚንቶን ለቁጥጥርና ለክትትል በሚል በየኬላዎችና ሌሎች ሥፍራዎች መያዝና መውረስ በጥብቅ ተከለከለ፡፡

ከባለፈው ሐሙስ ታኅሳስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ መመርያ፣ በተቀየረው መመርያ ላይ ይከናወኑ የነበሩ ሲሚንቶን በየኬላው በቁጥጥር ምክንያት መያዝ፣ እንዲሁም አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን ለፋብሪካዎች መምረጥ የመሰሉ ዓይነት ተግባራት፣ በማንኛውም የመንግሥት አካላት እንዳይከናወኑ ተከለከሉ፡፡ በአዲሱ መመርያ ‹‹በጥብቅ ለተከለከሉ ጉዳዮች›› መካከልም ሲሚንቶን ካለ ደረሰኝ መሸጥና ተሽከርካሪዎች ከፋብሪካ ሲወጡ ካለ መዳረሻ ሰነድ መያዝ እንደማይችሉም ይገኙበታል፡፡

መመርያውን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተሻለ በልሁ እንደገለጹት፣ ከዚሁ መመርያ በኋላ መኪኖች ክትትልና ቁጥጥር እየተባለ ‹‹የሚታደኑበት ምክንያት የለም›› ብለዋል፡፡ ለዚህም ተቆጣጣሪ አካላት ተሰጥቷቸው የነበረው ኃላፊነት ከዚህ መመርያ በኋላ መነሳቱን ተናግረዋል፡፡

‹‹በጣም የሚያሳዝነው የባለፈው መመርያ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ በቁጥጥር ስም የሲሚንቶ አዳኙ ብዙ ነው ሆነው፤›› ሲሉ አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ ከዚህ በኋላ ቁጥጥር የሚኖረው መንገድ ላይ የሲሚንቶ ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ሳይሆን በደረሰኝና በዋጋው እየተሸጠ መሆን አለመሆኑን በመሸጫ መጋዘን ውስጥ መቆጣጠር ብቻ ነው፡፡ ‹‹ይህ ምርት ከዚህ በኋላ በነፃ ይንቀሳቀሳል›› ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

የክልልና የከተማ መስተዳደሮች ከፋብሪካ አውጥተው የሚያከፋፍሉና የሚቸረችሩ የመንግሥትና የማኅበር ድርጅቶችን ከዚህ በፊት ይመርጡ የነበረ ሲሆን፣ እንደ ሚኒስቴር ዴኤታው ገለጻ ይህ ተግባር ከዚህ መመርያ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ አምራች ፋብሪካዎች በራሳቸው አከፋፋዮችንና ቸርቻሪዎችን መምረጥ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ሲሚንቶን ‹‹ነፃነቱ የተጠበቀ ሸቀጥ›› ሆኗል በማለት በነፃነት ከማምረቻው እስከ ፋብሪካዎች መሄድ እንደሚችል አቶ በልሁ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የሚያሳልጥና ቀልጣፋ ይሆንልናል ያሉትን ነገሮች ፋብሪካዎች ይመርጣሉ›› በማለት አክለዋል፡፡

በተጨማሪም ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ የሲሚንቶ ተሽከርካሪዎችን ከፋብሪካ ያለ መዳረሻ ሰነድ ማስወጣት ሲሆን፣ መዳረሻቸውን የሚያሳውቅ ሰነድ አዘጋጅተው ፋብሪካዎች መሸኘት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዙሪያም ከፋብሪካዎች ጋር በመነጋገር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡

በሲሚንቶ ሥርጭትና ግብይት ላይ የመንግሥት ድርሻ ሰፊ እንደበረና ከዚህ በኋላ ግን፣ ‹‹በረባ ባልረባ ውስጥ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ይቆማል›› ሲሉ አቶ ተሻለ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የመንግሥት ድርሻ ሊሆን የሚችለው የሲሚንቶ ሽያጩ በደረሰኝ መሆን አለመሆኑን መቆጣጠር፣ እንዲሁም አጠቃላይ የበላይ ክትትልና ቁጥጥር ብቻ ይሆናል፡፡

ሆኖም ግን መንግሥት የሲሚንቶ የፋብሪካ ዋጋን አሁንም ‹‹ለተወሰነ ጊዜ›› በየስድስት ወር እያወጣ የሚቀጥል ሲሆን፣ ባለፈው መስከረም ወር አውጥቶት የነበረውን ዋጋ አሁን በድጋሚ ከልሶታል፡፡ ይህም ለቀጣይ ስድስት ወራት የሚቆየውና እንዳዲስ የተከለሰው ዋጋ ፋብሪካዎች ሲሸጡበት ከነበረው የተወሰነ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

ለ11 ፋብሪካዎች ከተደረገው ጭማሪ በአማካይ በፊት ከነበረበት በኩንታል ከ590 ብር ወደ 758 ብር ከፍ ብሏል፡፡ ባለፈው አምስት ወራት ከተመረተው 18.7 ሚሊዮን ኩንታል ሲሚንቶ ውስጥ 10.2 ሚሊዮኑን ያመረተው ዳንጎቴ ሲሚንቶ፣ ከመስከረም ወር ጀምሮ ሲሸጥበት ከነበረው በኩንታል 549.49 ብር አሁን በኩንታል 795.93 ብር እንዲሸጥ ተወስኖለታል፡፡ ፋብሪካው ግን የጠየቀው በኩንታል 811 ብር እንዲሸጥ ነበር፡፡ ሌሎችም አብዛኞቹ ፋብሪካዎች ለመሸጥ ከጠየቁበት ዋጋ አነስ ባለ ነው መንግሥት ለቀጣይ ስድስት ወራት እንዲሸጡ የፈቀደላቸው።

(ሪፖርተር)
😁1
የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት ይኖርባቸዋል ተባለ

የሲሚንቶ አቅርቦትና ፍላጎት እንዲጣጣም ሁሉም የሲሚንቶ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ መግባት እንደሚገባቸው ተገለጸ::

የሲሚንቶ አምራቾች ማህበርና የሲሚንቶ አምራቾች ባለቤቶች ማህበር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷በተለያዩ የፀጥታ ችግሮችና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ ምርት ያቆሙና በሙሉ አቅማቸው የማያመርቱ ፋብሪካዎች መኖራቸውን ገልጸዋል::

ከዚህ ጋር ተያይዞ የአዳዲስ ፋብሪካዎች ግንባታም መፋጠን እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ምርት አቁሞ የነበረው መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካም በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ በመግለጫው ተነስቷል::

ፋብሪካው በቅርቡ ስራ እንዲጀምር ለማድረግም አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንደሚላኩ ተመላክቷል፡፡

የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርት ማቆሙ ከ 20 እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የሲሚንቶ ምርት አቅርቦት እንዲቀንስ አድርጎት እንደነበረም ነው የተገለጸው ።

ቸርቻሪዎችም የሚሸጡበትን የሲሚንቶ ዋጋ የመለጠፍ ግዴታ እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው::

(FBC)
👍1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማው እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።


ለከተማው ሕብረተሰብ ዘርፈብዙ ፋይዳ ያላቸውና በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተገነቡ የሚገኙ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ ሂደት በዛሬው ዕለት በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተጎብኝቷል።


በምልከታው በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮስኮ) እየተገነቡ የሚገኙት የኮልፌ መንዲዳ ሆስፒታል፣የላፍቶ ሆስፒታል፣የላፍቶ አትክልትና ፍራፍሬ መሸጫ ማዕከል ምዕራፍ 2 ግንባታ ፣ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ማቋቋምያ ማዕከል ፕሮጀክቶች ተካተዋል።


በምልከታው በተለይ በሆስፒታሎቹ የግንባታ ሂደት ላይ የተስተዋለውን መዘግየት በአስቸኳይ በሚፈታበት አግባብ ዙሪያ የአሰሪ መስሪያ ቤቱ፣ የስራ ተቋራጩ እንዲሁም የአማካሪ ድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችን ያሳተፈና ተስፋ ሰጪ ውይይት ተደርጓል።


የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታሕሳስ 23/2015 ዓ/ም


በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
በስልጠና የዳበረ እውቀት ለስራ ውጤታማነት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡

በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች እውቀትና ክህሎታቸውን በተለያዩ ስልጠናዎች ሲያዳብሩና ሲያሻሽሉ በዘርፉ አመርቂ ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡

ይህን የተረዳው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት ጋር በመተባበር ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች ስልጠናዎችን በመስጠት የፈፃሚዎችን የመፈፀም አቅም እንዲሻሻል እያረገ ይገኛል፡፡

ቢሮው የያዝነውን ሳምንት ጨምሮ ለተከታታይ 12 ቀናት ከቢሮውና ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ የኮንትራት አስተዳደር ፣ የፕሮጀክት ኦዲት ፣ የምህንድስና ግዥ ፣ የላብራቶሪ እንዲሁም የዲዛይንና ዋጋ ተከላ ባለሙያዎች በ FIDIK, tender and bid procedure, construction manual, , PPA contract administration, claim and dispute resolution, ዙሪያ የሚያተኩር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በስልጠናው ከ110 በላይ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት እና ከስራ ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የተውጣጡ ሰራኞችም ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

ስልጠናው የስራ ተነሳሽነትን የሚፈጥር፣ አነቃቂ እንዲሁም ጉድለቶችን በመለየት የማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል እንደሆነ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታህሳስ 25/2015 ዓ.ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
👍2