በቢሮው ለ63 ማሕበራት የስራ ትስስር ተፈጥሯል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ለ43 ደረጃ 6 ተመራቂ ማሕበራት እንዲሁም ለ20 ደረጃ 7 ባጠቃላይ ለ63 በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ትስስር በትላንትናው ዕለት ፈጥሯል፡፡
በቢሮው የማሕበራት ፍላጎትና ጥያቄ ላይ መሰረት በማድረግ ከከተማው የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዕጣ ወጥቶላቸው ለተላኩ 63 ማሕበራት ቢሮው ያዘጋጀውን ስራ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ተወካይ፣የደረጃ 6 ማሕበራት ተወካይ እንዲሁም ማሕበራቱ በተገኙበት ግልፅ በሆነ ዕጣ ደልድሏል፡፡
የስራ ድልድሉን የተከታተሉት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለማሕበራቱ የስራ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን እነዚህን ስራዎች ቢሮው ኃላፊነት ወስዶ ለማሕበራት ለማስተላለፍ ውሳኔ ላይ የደረሰው የስራ ዕድልን በማስፋት የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በተግባር ለማረጋገጥ ብቻም ሳይሆን የማሕበራቱን ዓቅም በመሰረታዊነት ለማሳደግ ተነሳሽነቱን ወስዶ ነው ብለዋል፡፡
ኃላፊዋ አክለውም ቢሮው ይህን ትልቅ ኃላፊነት ወስዶ ስራውን ለማሕበራቱ ሲያስተላልፍ ከነዚህ ማሕበራት ቢሮው የሚጠብቃቸው ያሏቸውን ነጥቦች ያስቀመጡ ሲሆን በዚህም መሰረት ለ G+4 ትምህርት ቤት ግንባታዎች የ4 ወር እንዲሁም ለሼዶቹ ደግሞ የ45 ቀናት ጊዜን ቢሮው ማስቀመጡን ጠቅሰው በተቀመጠው የጥራት ደረጃና ጊዜ ፕሮጀክቶቹን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችኋል በማለት በነገው ዕለት በየተደለደላችሁበት ሎት ተገኝታችሁ ሳይት ርክክብ እንድትፈፅሙ ሲሉ አሳስበዋል፡፡……..

………ቢሮ ኃላፊዋ በመጨረሻ መልዕክታቸው በሌብነትና መሰል እንቅስቃሴዎች ላይ ቢሮው ግልፅ እና የማይታጠፍ አቋም እንዳለው በመረዳት ማሕበራቱ ከዚህ አስተሳሰብ እና ተግባር እራሳቸውን እንዲያቅቡ አበክረው በማሳሰብ በዚህ ረገድ እንደቢሮ ማንኛውንም ክፍተቶች ለመድፈን የተቀናጀ ጥረት ያደርጋል ብለዋል፡፡
የዲዛይን ስራዎቹ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን ያነሱት ደግሞ የቢሮው የዲዛይንና ምህንድስና ግዢ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አርክቴክት ቴዎድሮስ አያሌው በበኩላቸው በነገው ዕለት ሳይቶቻችሁን ለማስረከብ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ያሉ ሲሆን እዚህ የተቀመጥነው ልናገለግላችሁ እንደመሆኑ መጠን በሂደቶቹ ሁሉ ከጎናችሁ ነን በማለት እንደቢሮ አምነን የሰጠናችሁን ይህን ኃላፊነት በብቃት ተወጥታችሁ እንደምታሳዩን ዕምነት አለን ብለዋል፡፡
ሌላው በመድረኩ ለማሕበራቱ መልዕክት ያስተላለፉት የቢሮው የኮንትራት አስተዳደር ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ዲሜጥሮስ ታደሰ እንዳሉት ከነገ ጀምሮ የስራ ቀናችሁ መሆኑን ተረድታችሁ በተቀመጠላችሁ ጊዜ ፕሮጀክቶቻችሁን ለማጠናቀቅ ከተለመደው የስራ ሰዓትና የአሰራር ዘይቤ የተለየ መንገድ ማሰብ አስፈላጊ ይሆናል በማለት በከተማ አስተዳደሩ በ60 እና 90 ቀናት እየተሰሩ ለአገልግሎት የበቁ ሕንፃዎችን እንደማሳያ አንስተዋል፡፡
የአዲ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታህሳስ 13/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity

በአዲስ አበባ የመግቢያ በሮች ላይ አራት ሜጋ ሁለገብ የግብርና ምርቶች ማከፋፈያ የገበያ ማዕከላትን እየገነባን ነው፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አንድ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ አንድ በግንባታ ላይ ይገኛሉ፡፡
እነኚህ የገበያ ማእከላት ከፍተኛ የግብርና ምርትን በመያዝ፣ የኑሮ ውድነቱን ጫና በመቀነስ፣ ገበያን በማረጋጋትና በመቆጣጠር የራሳቸውን ሚና የሚጫወቱ ብሎም ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እድልን የሚፈጥሩ ይሆናሉ፡፡

ከትላንት በስትያ ቢሮው የተለያዩ ስራዎችን ለማሕበራት መደልደሉን ተከትሎ የሳይት ርክክቦች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
በማሕበራቱ እንዲሰሩ ከተዘጋጁት 31 G+4 ትምሕርት ቤቶች፣20 የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሼዶች እንዲሁም 31 የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ከይዞታ እና ሌሎች ጉዳዮች የፀዱ ሳይቶችን ለማሕበራቱ ማስረከብ ተችሏል፡፡
የሳይት ርክክብ ሂደቱ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ለርክክቡ ተግባራዊነት መሳካት ከመሬት ልማት ማኔጅመንት ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የዚህ የትስስር ተጠቃሚ ማሕበራት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ድርሻ እንደሚኖራቸው የሚያምነው ቢሮው በዘርፉ ለተሰማሩ ማሕበራት የስራ ዕድል ፈጠራ ትግበራውን አጠናክሮ የሚከውን ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት 14/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity
በማሕበራቱ እንዲሰሩ ከተዘጋጁት 31 G+4 ትምሕርት ቤቶች፣20 የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሼዶች እንዲሁም 31 የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ ፕሮጀክቶች ውስጥ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ከይዞታ እና ሌሎች ጉዳዮች የፀዱ ሳይቶችን ለማሕበራቱ ማስረከብ ተችሏል፡፡
የሳይት ርክክብ ሂደቱ በዛሬው ዕለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ለርክክቡ ተግባራዊነት መሳካት ከመሬት ልማት ማኔጅመንት ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል፡፡
የዚህ የትስስር ተጠቃሚ ማሕበራት ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ድርሻ እንደሚኖራቸው የሚያምነው ቢሮው በዘርፉ ለተሰማሩ ማሕበራት የስራ ዕድል ፈጠራ ትግበራውን አጠናክሮ የሚከውን ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት 14/2015 ዓ/ም
በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡
https://www.facebook.com/AddisConstruction/
https://t.me/AddisCityCon
https://twitter.com/AddisCity
ለ6 በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ዕድል የፈጠረው የእንጦጦ ጋቢዮን ተጠናቋል፡፡
========++++++++++==========+++++++++++
በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው እንጦጦ ኪዳነምሕረት እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የተገነባው ጋቢዮን ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ ተደርጓል፡፡
ከ6 እስከ 13 ሜትር ከፍታ እንዲሁም ከ24 እስከ 65 ሜትር ርዝመት ያላቸው አምስት የተለያዩ ክትሮች ሲሰሩለት የቆየው የእንጦጦ ኪዳነምሕረት ረባዳማ ስፍራ አሁን ላይ ባጠቃላይ 3036 ሜትር ኪዩብ የሚሆነው የጋቢዮን ስራ ተጠናቆ ለርክክብ ዝግጁ ተደርጓል፡፡
ለ6 በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የስራ ዕድልን የፈጠረው ፕሮጀክቱ ከማሕበራቱ በተጨማሪ በዕለት ከ100 እስከ 120 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድሎችን በመፍጠር በአካባቢው የነበረውን ከፍተኛ የአደጋ ተጋላጭነት ስጋት ከመቅረፉ በተጨማሪ ቢሮው በኮንስትራክሽን ዘርፉ የተደራጁ ዜጎችን ፍትሀዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት ስራ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታሕሳስ 14/2015 ዓ/ም