Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.6K subscribers
12.3K photos
198 videos
90 files
759 links
Government Organization
Download Telegram
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በባለቤትነት እያስገነባው የሚገኘው የሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ባለ 11 ወለል ሕንፃ አሁናዊ ገፅታ፡፡

ሕንፃውን ለማጠናቀቅ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች በሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታሕሳስ 12/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
የወረዳ 12 አስተዳደር B+G+7 ሕንፃ ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ሕንፃ ግንባታ ከዚህ ቀደም በተገባው ውል መሰረት ግንባታውን ለማከናወን እንቅፋት ሆነው የነበሩ ችግሮች ተፈተው አሁን ላይ ግንባታው በመልካም ሁኔታ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተመለከተ፡፡

760 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውና ከ84 ሚሊዮን ብር በላይ ተበጅቶለት በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ባለቤትነት እንዲሁም በባንቲዋሉ ኮንስትራክሽን ድርጅት ስራ ተቋራጭነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ ባለ ዘጠኝ ወለል ሕንፃ አሁን ላይ 70 በመቶ ፊዚካል የአፈፃፀም ላይ ደርሷል፡፡

በቂ የመኪና ማቆሚያ፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ካፍቴሪያ፣ቢሮዎች እና ሌሎችም መሰረተ-ልማቶች የሚሟሉለት ሕንፃው አሁን ላይ የመጨረሻው ወለል ኮለን ሙሌት እየተጠናቀቀ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ የአልሙኒየም ፓርቲሽን፣የጂፕሰም፣የጣራ፣የኤሌትሪክና ሳኒተሪ፣የበርና የመስኮት ገጠማ ስራዎች የሚሰሩለት ሲሆን በተያዘለት ዕቅድ መሰረት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር እየተሰራ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ታህሳስ 12/2015 ዓ/ም

በቢሮው የሚወጡ አዳዲስ ጨረታዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን የቢሮውን ይፋዊ ገፆች ይከተሉ፡፡

https://www.facebook.com/AddisConstruction/

https://t.me/AddisCityCon

https://twitter.com/AddisCity
1
ለረጅም ዓመታት ሲጓተት የቆየውን የቃሊቲ-ቱሉ ዲምቱ መንገድ ፕሮጀክት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን)ታህሳስ 12/2015
ለረጅም ዓመታት የተጓተተው የቃሊቲ-ቱሉ ዲምቱ መንገድ ፕሮጀክት በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ስራው የተጀመረው የቃሊቲ-ቱሉ ዲምቱ የመንገድ ፕሮጀክት ከሰባት አመታት በኋላም ከግማሽ በላይ መጓዝ አልቻለም፡፡ ይሁንና ለፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያት ናቸው የተባሉ ችግሮች ተለይተዋል ተብሏል፡፡

የግንባታ ስራውም ባለፈው ጥቅምት 2015 በድጋሚ ተጀምሮ እየተፋጠነ ይገኛል፡፡

በሁለት ወራት የመንገዱ ግንባታ ስራም ለመጀመርያ ደረጃ የአስፓልት ንጣፍ የሚሆኑ የጠጠርና መሰል አስፈላጊ ግብዓቶች መዘጋጀታቸውን የፕሮጀክቱ ተጠሪ መሃንዲስ ኢ/ር ሙሉጌታ አበበ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በመንገዱ የግራ ክፍል የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎችን የመቅበር ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ኢ/ር ሙሉጌታ ገልጸዋል፡፡

ቀሪ የመንገዱ ስራዎች በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቁ በፍጥነት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኢ/ር ሙሉጌታ ክረምት ከመግባቱ በፊት መጨረስ የምንችልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡

ለመንገዱ ግንባታ እስካሁን ድረስ ከ1 ቢሊዮን በላይ ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የግንባታ ሂደቱም 58 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል፡፡

ዘገባው የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ነው
በቢሮው ለ63 ማሕበራት የስራ ትስስር ተፈጥሯል፡፡

የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ለ43 ደረጃ 6 ተመራቂ ማሕበራት እንዲሁም ለ20 ደረጃ 7 ባጠቃላይ ለ63 በጥቃቅንና አነስተኛ ለተደራጁ ማሕበራት የስራ ትስስር በትላንትናው ዕለት ፈጥሯል፡፡

በቢሮው የማሕበራት ፍላጎትና ጥያቄ ላይ መሰረት በማድረግ ከከተማው የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ዕጣ ወጥቶላቸው ለተላኩ 63 ማሕበራት ቢሮው ያዘጋጀውን ስራ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ፣ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ተወካይ፣የደረጃ 6 ማሕበራት ተወካይ እንዲሁም ማሕበራቱ በተገኙበት ግልፅ በሆነ ዕጣ ደልድሏል፡፡

የስራ ድልድሉን የተከታተሉት የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር አያልነሽ ሐብተማርያም ለማሕበራቱ የስራ መመሪያ ያስተላለፉ ሲሆን እነዚህን ስራዎች ቢሮው ኃላፊነት ወስዶ ለማሕበራት ለማስተላለፍ ውሳኔ ላይ የደረሰው የስራ ዕድልን በማስፋት የዜጎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በተግባር ለማረጋገጥ ብቻም ሳይሆን የማሕበራቱን ዓቅም በመሰረታዊነት ለማሳደግ ተነሳሽነቱን ወስዶ ነው ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ አክለውም ቢሮው ይህን ትልቅ ኃላፊነት ወስዶ ስራውን ለማሕበራቱ ሲያስተላልፍ ከነዚህ ማሕበራት ቢሮው የሚጠብቃቸው ያሏቸውን ነጥቦች ያስቀመጡ ሲሆን በዚህም መሰረት ለ G+4 ትምህርት ቤት ግንባታዎች የ4 ወር እንዲሁም ለሼዶቹ ደግሞ የ45 ቀናት ጊዜን ቢሮው ማስቀመጡን ጠቅሰው በተቀመጠው የጥራት ደረጃና ጊዜ ፕሮጀክቶቹን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ ይጠበቅባችኋል በማለት በነገው ዕለት በየተደለደላችሁበት ሎት ተገኝታችሁ ሳይት ርክክብ እንድትፈፅሙ ሲሉ አሳስበዋል፡፡……..