Addis Ababa Design And Construction Works Bureau
20.4K subscribers
12.1K photos
193 videos
88 files
758 links
Government Organization
Download Telegram
አራዳ ፓርክ የምሽት ገፅታ
13👍12
ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች።

የሀገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሞያቸው ለኢትዮጵያ ሀገራችን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በከተማችን አዲስ አበባ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል።
ሚያዚያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም

ፈጣሪ ኢትዮዽያና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍4👏32
ሀገር ለጠቢባን የሕያው ሥራዎቻቸው ምስክር ሐውልት ታቆማለች!

ዛሬ በአርበኞች ቀን በተለያዩ መስኮች የጀግንነት ሚና የተወጡ አርበኞቻችንን በማስታወስ እየዘከርናቸው ነው።

ሀገር በልማት ስራዎች፣ ድንበርን በመከላከል፣ በሰንደቅ ዓላማ እና በሕግ ብቻ አትገነባም። ሀገር የምትገነባው በሕዝብ የጋራ ትውስታ፣ በጋራ ስሜት እና በታላላቅ የጥበብ ውጤቶችም ጭምር ነው። ይህ እውነት ዛሬ በቆሙት የሀገር ባለውለታ ታላላቅ ጠቢባን ሐውልቶች በአዲስ አበባ ከተማችን እውን አድርገናል።

ከተማ አስተዳደራችን በኮሪደር ልማት እና በታላላቅ ፕሮጀክቶች ውስጥ፣ ጥበብን ማዕከል አድርጓል።

ዛሬ ሃውልት የቆመላቸው ለሃገራቸው ሰላም፣ ለኢትዮጵያዊነት ግንባታ፣ ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት፣ ለወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ ለፍትሃዊነት፣ ለነፃነትና እኩልነት ላቀነቀኑት አንጋፋዎቹ የሀገር ባለውለታዎች ሎሬት ጸጋዬ ጸጋዬ ጋብረ መድኅን፣ የክብር ዶ/ር ጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ ዓሊ ቢራ፣ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር እና ሐጫሉ ሑንዴሣ ናቸው። ከእነዚህ በተጨማሪም ልናከብራቸው የሚገባን የሀገር ባለውለታዎች የሆኑ የጥበብ ሰዎች መኖራቸው ስለሚታወቅ ይህ ስራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም።

ጥበብ ሀገርን ትስራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታስታውሳለች።


ፍጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍8👏42