Abrehot Library
917 subscribers
143 photos
21 videos
8 links
Abrehot Library is a public national library and the biggest library in Ethiopia also in East Africa.
Download Telegram
የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (ዩኒሳ) የኢትዮጵያ ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የተለያዩ መጻህፍትን አበረከተ

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (ዩኒሳ) የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ለአብርሆት ቤተ-መጻህፍት የተለያዩ መጻህፍትን አበረከተ።

የዩኒቨርስቲው ተወካይ ፕሮፌሰር ቴኒሰን ሙጉቺኒ፤ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ መጽሃፍቶቹን አስረክበዋል።

መጽሃፍቶቹ ከ1 ሺህ 100 በላይ ሲሆኑ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ይዘት ያላቸው መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ተወካይ ፕሮፌሰር ቴኒሰን ሙጉቺኒ፤ የትምህርት አሰጣጥ በመማሪያ ክፍሎች ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ ሰዎች እንዲያነቡ ቤተ መጽሃፍቶችን ሙሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዩኒሳ ለአብርሆት ቤተ መጻህፍት ያደረገው ድጋፍም ለዚሁ ተግባር አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል።

የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ዳይሬክተር ኢንጂነር ውባየሁ ማሞ፤ ዩኒሳ ለአብርሆት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት የህግ ታራሚዎች በዕውቀት እንዲበለጽጉ እንዲሁም በስነምግባር እንዲታነፁ ለማድረግ ከቃሊቲ ፌደራል ማረሚያ ቤት ጋር በቋሚነት መስራት ጀመረ።

የቤተ-መጽሐፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ ከማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ከታራሚዎች ጋር ባደረጉት ሰፊ ውይይት እንደገለፁት የህግ ታራሚዎች የፍርድ ግዜያቸውን በንባብ እንዲያሳልፉ ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። የህግ ታራሚዎች በእርማት በጊዜያቸው እንዲሁም ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ አምራች ዜጋ እና ከራሳቸው አልፈው ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ ለማድረግ አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ተነሳሽነቱን ወስዶ ከተለያዩ ማረሚያ ቤቶች ጋር ከፍተኛ ስራ እንደሚሰራ በተጨማሪ አሳስበዋል።

በውይይቱ ወቅትም አብርሆት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተፃፉ ወቅታዊ የስነ ልቦና ፣ የስነ ምግባር ፣ የስነ አዕምሮ፣ የስነ ሰብ ፣ ኪነ ጥበብ፣ የፍልስፍና፡ የሳይንስ ና ቴክኖሎጂ መጽሀሕቶችን ጨምሮ ሌሎች መጽሐፍቶችን ለታራሚዎች ተደራሽ እንዲሆን የበለጠ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። በዚህም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደርና ታራሚዎች ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውና ለአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዳይሬክተር ያላቸውን የላቀ አድናቆት ገልፀዋል።

Abrehot Library started working with Kaliti Federal Penitentiary in order to enrich the knowledge and morals of the inmates of the law.

The director of the library Engineer Wubayehu Mamo mentioned that it is necessary to do a lot of work so that the inmates of the law can spend their time in reading. He further emphasized that Abrehot Library will take the initiative and work closely with various prisons to make the inmates of the law become productive citizens and serve the community beyond during their correctional period and when they join the society.

During the discussion, the director mentioned that Abrehot will do more to make books accessible to the inmates, including latest books on psychology, ethics, psychatry, humanities, art, philosophy, science and technology. With this, the prison administration and the inmates felt great joy and expressed their great appreciation for the director of the Abrehot Library.
Calling All Tech Pioneers: Africa's Biggest Hackathon Awaits Your Brilliance!

Inviting all students across Africa! If you have a passion for technology and innovation, the A2SV Hackathon, organized by A2SV in Abrehot Library is an incredible opportunity you won't want to miss.

This is your chance to showcase your skills and creativity, and to win $30,000 in prizes🏆. Mark your calendars for a Workshop on August 19-20, 2023, as we gear up for an unparalleled hackathon experience that will redefine Africa's technological landscape. During the workshop, you will learn about the latest advances in generative AI, and how to apply them to your own projects.

During the hackathon, you will have the opportunity to work with a team of like-minded peers to develop a project that uses generative AI to solve a real-world problem. So get ready to unleash your creative genius and explore untapped applications of existing AI models during our immersive virtual workshops!

Whether you are an astute coding prodigy, an AI enthusiast, or a forward-thinking tech luminary, this event is designed for you. Our esteemed panel of judges will be looking for projects that are innovative, creative, and have the potential to make a positive impact. Assemble a dream team of 3 to 5 members, and together, let us reshape the future of technology! No team yet? No worries! We are committed to pairing you with like-minded peers who share your aspirations throughout the African continent.

🎯To be eligible, meet these prerequisites:
• All team members must be based in Africa
• Enrolled students in a University, College (undergrad, Associates, Diploma program), or High School throughout the hackathon.
• The countdown has begun! Seize the moment and etch your name in history. The registration deadline is August 17, 2023!

For deeper insights into the hackathon and to explore the A2SV Foundation, visit our websites:

A2SV Hackathon Website: https://hacks.a2sv.org/
A2SV Foundation Website: https://a2sv.org/
“አብርሆት ቤተ መጽሐፍት ተዘረፈ” የሚለው መረጃ ሀሰት መሆኑን ስለመግለፅ

ከአብርሆት ቤተ መጽሐፍት ወደ 24 ሚሊዮን የሚጠጋ ዋጋ የሚያወጣ መጽሐፍ ተዘረፈ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን ዋና ዳይሬክተር ገልፀዋል

በተጨማሪም የአብርሆት ቤተ መጻህፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ እንደተናገሩት፤ ቤተ መጻህፍቱ ተዘረፈ በሚል እርሳቸውን ዋቢ አድርጎ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም ከእውነት የራቀ የፈጠራ መረጃ ነው ብለዋል።

ከአብርሆት ቤተ መጻህፍት በተጠቀሰው ልክ ብዛት ያለውን ያህል መጽሀፍ ሊዘረፍ ቀርቶ አንድ መጽሀፍ እንኳን ለማውጣት ቢሞከር በዘጠኙም በሮች ላይ ያሉ ካሜራዎችና የተገጠሙ ሲስተሞች ሙከራውን ማስቀረት እንደሚችሉ ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት።

ሀሰተኛ መረጃውን ያሰራጩ አካላት 14 የቤተመጻህፍቱ ሰራተኞች ታስረዋል ያሉትም ፍጹም ስህተት መሆኑን ጠቅሰው፤ አንድም ሰራተኛ የታሰረ እንደሌለ አራጋግጠዋል።

በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት ቤተመጻህፍቱ መደበኛ ስራውን እያከናወነ መሆኑንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Think and Grow Rich

- Napoleon Hill

#napoleonhill#Abrehotlibrary#Enlightenment#Ethiopia
Coding program for Girls at Abrehot Library.

Join our Coding program that is completely free and it starts on Oct 28, 2023 at abrehot library the program is for girls age group from 10 - 17 , they will learn scratch programming and website development , register using the link below.

Criteria For Application:

-Any young girl in the age group of 10-17 who is interested in coding

Deadline For application:

October 26, 2023 [until Mid-night]

https://forms.gle/YggFqMZRowbV8rZv9
ዛሬ አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጋር በመተባበር የህግ ታራሚዎች በዕውቀት እንዲበለጽጉ እንዲሁም በስነምግባር እንዲታነፁ የማበረታቻ ሽልማቶች እና የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ተካሄደ።

የቤተመፅሀፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ዉብአየሁ ማሞ እንደገለፁት
አሁን ዓለም ከምትገኝበት የስልጣኔና የእድገት ደረጃ ልትደርስ የቻለችው በተጻፉና በተነበቡ የእውቀትና የመረጃ ስርጭትና ክምችት ሃብቶች የተነሳ ነው ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም ንባብ ለአጠቃላይ ሰብእና እድገት የሚሰጠው ጠቀሜታ እጅግ ከፍ ያለ ሲሆን አንድ ሰው አውቆ በድፍረት፣ ሳያውቅ በስህተት በተሠራ ስህተት ምክንያት ወደ ማረሚያ ቤት የሚሄድ ሰው፣ ከቤተሰቦቹና ከጓደኞቹ በላይ የቅርብ ወዳጁ መጻሕፍት ናቸው ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የታሰረ ሰው እስሩ እረፍት የሚሆንለት ከንባብ ጋር ከተቆራኘ ሲሆን ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በማረሚያ ቤት በሚቆይባቸው ዘመናት ጊዜውን የሚያባክንበት ግላዊና ማኅበራዊ ጉዳይ ስለሌለው ከስንፍና፣ ከሞራል ውድቀት፣ ከቀቢጸ-ተስፋ፣ መዳን የሚቻለው በንባብ አማካኝነት ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

የማረሚያ ቤት የማረም ማነፅና ተሀድሶ ልማት ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት ም/ኮሚሽነር ጀነራል ደስታ አስመላሽ እንደገለፁት የአብርሆት ቤተመፃህፍት ለታራሚዎች እያደርገ ያለውን በማመስገን በቀጣይም በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች እንደዚህ አይነት ድርጊቶች እንዲቀጥሉ አሳስበዋል፡፡