አቡ መሀመድ አብድልሰመድ ኢብኑ ጀማል
202 subscribers
400 photos
150 videos
78 files
592 links
👉 ይህ ቻናል በወንድማችን አብድልሰመድ ጀማል የተለያዩ አጠር ያሉ ጠቃሚ ምክሮች እንዲሁም ደርሶች እና መልእክቶች ይተላለፋሉ
Download Telegram
https://youtu.be/g3WVKNBcJ1U?si=6klKUbg63bcPCH60


💬 ይህን መልክ ልብ ብለህ አድምጥ ዑለማዎች ዝም ብለው አይናገሩም

👉 ሰላት ላይ ቁሞ ስለ መቅረፅ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

የፆም ህግጋቶች

▶️ የረመዳን ወር ፆም ማለት ከእስልምና ማዕዘናቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሁሉም ሙስሊሞች ላይ ይህንን ማዕዘን ማረጋገጥ ግድ ይላል::

ይህንን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ የፆም ህግጋትን በማወቅ ሲሆን ይህን እንዲረዳን ዘንድ ከዚህ በታች ያለውን የፆም ህግጋቶችን ከልብ በማንበብ ኢባዳችንን በእውቀት እንጠብቅ::

1-የፆም ገለፃ ( ፍቺ )
===============
👉ቋንቋዊ ፍቺው :- ከማንኛውም ነገር መቆጠብ ፆም ይባላል::
👉 ሼሪዓዊ ፍቺው :-ከሚበላ ከሚጠጣና ባለቤቱን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከመገናኘት እና ማንኛውም ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች በቀልብ ከመነየት ጋር ሁለተኛው የፈጅር ጒህ ከጀመረበት ሰዓት ፀሀይ እስክትጠልቅ ድረስ መታቀብ ማለት ነው::

2-የፆም ብይኑ
=============
👉 የረመዳን ወር ፆም መፆም ግዴታ መሆኑ በቁርዓን በሐዲስ እንዲሁም ኡለማዎች በሙሉ የተስማሙበት ነው::
የረመዳን ፆምን የለም ብሎ ያስተባበለ ሙስሊም እንዳልሆነ በሁሉም ዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው::

3-ፆም ግዴታ የሚሆንባቸው ቅድመ መስፈርቶች
===================
1♦️ ሙስሊም መሆን -- በካፊር ላይ ግድ አይሆንም::
2♦️ ንፁህ አቅል -- በእብድ ላይ ግድ አይሆንም::
3♦️ አቅመ አዳም መድረስ -- በህፃን ላይ ግድ አይሆንም::
4♦️ ጤነኛ መሆን-- በህመምተኛ ላይ ግድ አይሆንም::
5♦️ ሀገሩ ነዋሪ የሆነ ላይ--በመንገደኛ ላይ ግድ አይሆንም::
6♦️ ቻይ መሆን አለበት-- በማይችል ሰው ላይ ግዴታ አይሆንም እዴሜው የገፋ ሰውን ይመስል::

4-የፆም ማዕዘናት
================
1🔷️ መነየት :- የሚነየተውም በቀልብ ነው በምላስ መናገር የለበትም::
2🔷️ ፆምን ከሚያበላሹ ማንኛውም ነገር መታቀብ::
3🔷️ ጊዜን ( ሰዓትን) መጠበቅ እውነተኛው ጎህ ከወጣ ሰዓት ጀምሮ ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ::


5-ፆምን የተወ ሰው ፍርዱ ምንድነው? ===================
1🔶️ የፆምን ግዴታነት የሚያምን ሆኖ ሳለ ምንም እምነታዊ ምክንያት ሳይኖረው የሚያፈጥር ከሆነ አመፀኛ ወንጀለኛ ነው ከሀዲ ግን አይደለም::

2🔶️ የፆም ግዴታነቱን የሚያስተባብል የሚቃወም ከሆነ ይህ ሰው ከሀዲ (ካፊር) ነው ከእስልምና ይወጣል::


6-ፆምን የሚያበላሹ (የሚያፈርሱ )ነገሮች
===================
1⚡️ከመስፈርቶቹ ውስጥ አንዱን ማጓደል ከእስልምና ወደ ኩፍር መሄድን ይመስል::

2⚡️ከማዕዘናቶች ውስጥ አንዱን ማበላሸት ያለ ወቅት ማፍጠርን ይመስል::

3⚡️ሆን ብሎ ማስመለስ::
4⚡️ዋግምትን መሰራት::
5⚡️በአፍ ባይገቡም የምግብን ቦታ ሊተኩ የሚችሉ ነገሮችን መውሰድ እንደ ግልኮስ ደምን የመሳሰሉ ነገሮች
ፆምን ያበላሻሉ::

7-ፆም ላይ የሚፈቀዱነገሮች
=================
1💠 የሻወር ትጥበትን ከፈጅር አዛን በዃላ ማዘግየት ጀናባ ላይ እንዲሁም የወር አበባ ላይ ለነበሩ ሴቶች የፀዱ
ከሆነ መታጠብን ይችላሉ::

2💠 መጠንቀቅ የማይቻልን ነገር መዋጥ ምራቅን አዋራን የመሳሰሉ::
3💠 ለምክንያት ብሎ ምግብን መቅመስ::
4💠 ጥሩ መዓዛ ያላቸውን ነገሮች ማሽተት ሽቶን ይመስል::
5💠 እራሱ ላይ ውሀን ማፍሰስ እንዲሁም ሻውር መውሰድ::
6💠 ወደ ሆድ በማይደርስ ነገር ህክምና ማድረግ መርፌን ይመስል::

8-ፆም ላይ የሚወደዱ ነገሮች
==================
1✨️ ስሁርን አዘግይቶ መብላት::
2✨️ዱዓን ማብዛት በተለይ ሊያፈጥር ሲል::
3✨️ ፀሀይ ከጠለቀች በዃላ ቶሎ ማፍጠር::
4✨️ ቢቻል ዊትር በሆነ ቴምር ማፍጠር ከሌለ በውሀ ወይም በማንኛውም ነገር ማፍጠር::
5✨️ ፆመኛን ማስፈጠር::
6✨️ ሱና ነገሮችን ማብዛት ቁርዓንን መቅራት ሱና ሰላትን ማብዛት ተርሀዊን ለይልን መስገድ::
7✨️ ሰላተል ጀመዓን መስጂድ በመሄድ መጠባበቅ ሌሎችም ኸይር ስራዎችን ማብዛት::


9-ፆም ላይ የተጠሉ ነገርች
==================
1🌳 የተፈቀዱ ነገሮች ላይ ድንበር ማለፍ::
2🌳 የፆም ተወዳጅ ነገሮችን መተው::
3🌳 አላህን ከማውሳት ውጪ ንግግርን ማብዛት::
4🌳 የተጠሉ ስነምግባሮች ምቀኝነት ተንኮል ሀሜት ሰው ለሰው ማጋጨት ወደ ሀራም ነገሮች መመልከት::


10-ፆም የተደነገገበት ጥበቡ
===================

1🏝አላህን መፍራት የሚባለውን ነገር ያስገኛል::
2🏝የአላህን ፀጋ እንድናመሰግን ይረዳል::
3🏝ለመሳኪኖች እንድናዝን ያስተምረናል::
5🏝ነፍስን እንዴት መምራት እንዳለብን እናቃለን::
6🏝ትልቁ የአምልኮ ዘርፍ ነው::

11-የፆም ትሩፋቶቹ
================

1📌 የአላህን ማርታ ያስገኛል::
2📌 የፆመኛ ከአፋ የሚወጣው ጠረኑ አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽቶ የበለጠ ተወዳጅ ነው::
3📌 ፆመኞች ጀነት ውስጥ ረያን በተባለ በር እነሱ ብቻ እንዲገቡ ይጠራሉ::
4📌 የፆም ምንዳው አላህ ብቻ እንጂ ማንም የማያውቀው መሆኑ::


አላህ ፆማቸውን ከሚቀበላቸው ሰዎች ያድርገን

💬 ከኢብኑ ተይሚያህ (25) መድረሳ ጀመዓ የተላለፈ መልዕክት
🙏1
📌📌 በእራስ መደነቅ 📌📌
ቁ. 2
========================

💬 በእራስ መደነቅ ( መኮፈስ ) የሚባለው በሽታ በጣም አደገኛ አጥፊ የሆነ በሽታ መሆኑን እና ወደ እዚህ በሽታ የሚወስዱ ስበቦችን ጠቅሰን ነበር ::
👉 በዚህ ክፍል ደግሞ አንድ ሰው በዚህ በሽታ ስለመጠቃቱ የሚያመላክቱ አንድ አንድ ምልክቶች አሉ ከእነርሱም ውስጥ በጥቂቱ:-

1= ሀቅን ባለመቀበል መመለስ እና ሰዎችን አሳንሶ ( ንቆ) ማየት

2= በያዘው እውቀት መኮፈስ ከሱ በላይ አዋቂ ያለ የማይመስለው መሆኑ

3= በአካሄዱ በንግግሩ የሚኮፈስ

4= የእዕውቀት እና የአቅል ባልተቤቶችን ያለ ማማከር መናቅ

5= በዘር በጎሳ በገንዘቡና በቁንጅና መኮፈስ

6= ሰዎችን ሆን ብሎ መቃረን ለመታወቅ ብሎ የበላይነትን ለማሳየት ተፈልጎ

7= የዑለማዎችን ክብር አሳንሶ መግለፅ እነሱን ዝቅ ማድረግ

8= እራስን ማወደስ እና ማጥራራት

9= የሰራውን ወንጀል አሳንሶ ማየት እንዲሁም ብሎ መርሳት

10= የለመንኲት ዱዓ ተቀባይነቱ እና የአላህን ምንዳ ለማግኘት የተገባው ሰው ስለሆንኩ ብሎ ማሰብ ማመን

11= በስህተት ላይ ማዘውተር

12= የሙሉነት ደረጃ የደረሱኩኝ ነኝ ብሎ በማሰብ ከዒባዳ መሸሽ

13= ወንጀል የሚሰሩ ሰዎችን በንቀት አይን መመልከት

14= ዑለማዎችን የማዳመጥ ሁኔታ አነስተኛ መሆን

15= በቁጥር ብዛት መደነቅ ............


==============================
# እነዚ ብቻ ናቸው ማለት አይደለም ለናሙና ያህል ቢሆን እንጂ

ከእነዚህ ከተጠቀሱት ውስጥ አንዱም ይሁን ሌላ እኛላይ ካለብን ልንጠነቀቀው ልንርቀው ይገባል
በቀጣይ إن شاء الله መድሀኒቱን እንጠቅሳለን
👍1
Audio
📚በ አምነት ላይ መፅናት


👉 በዑስታዝ   አቡ መሀመድ       አብድልሰመድ  ጀማል
https://t.me/Abdelsemd_ibnu_jemal
📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ
ይቺን አለም ተሰናብተን፤ ቀብር ሆነን የማይቋረጥ ሰደቃ!!
➤የኢብኑ ተይሚያህ መድረሳ የሂሳብ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000531011191
Forwarded from Bil Ab
👉ከዓስር እስከ መግሪብ ባለው የሕፃናት የቂራት ፕሮግራም ከ100 በላይ ተማሪዎች በዚች ጠባብ ክፍል ውስጥ ለጤናቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ እርስ በእረስ ተደራርበው ደርስ እየተከታተሉ ይገኛል፡፡
👉ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት የመድረሳው አስተዳደር፣ የተማሪ ወላጃችና አጠቃላይ የአካባቢው ማህበረሰብ ሰፊ መድረሳ ለመግዛት በገንዘቡ፣ በእውቀቱ፣ በጉልበቱ እንዲሁም በዱዓ እየተባበሩ ይገኛሉ፡፡
✍🏻እርስዎም አላህ ከሰጠዎት የአቀመዎን በመነየት በሕይወት ላሉትም ለሞቱም ቤተሰቦቻቹ ለአንድ ሰው 1‚000 ብር
❖ ለራስዎና ለሚስትዎ
❖ ለልጆችዎ
❖ ለእናትና ለአባትዎ
❖ለጓደኛ ለዘመዶዎ
አንድ ላይ ሰብስበው ከስር በተጠቀሱት የባንክ አካውንቶች በማስገባት መድረሳውን ለመግዛት በሚደረገው እርብርብ የበኩሎን አሻራ ያስቀምጡ
❖ የመድረሳው ሕጋዊ የባንክ ሂሳቦች
➢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000531011191
➢ ዘምዘም ባንክ 0020015820101 ወይም 200158
➢ ኦሮሚያ ህብረት ባንክ 1056600021008
➢ ንብ ባንክ 7000039004459
➢ አቢሲኒያ ባንክ 124379733
➢ አዋሽ ባንክ 014251085217200
👍1
Forwarded from Mila (nur husen)
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድ እና የተከበራችሁ ወንድምና እህቶቼ አላህ ካለ ነገ የጁምአ ሶላት ላይ በ ሁዳ መስጅድ እና በ ኮዬ ፈጬ አቡዘር መስጂድ ላይ የገቢ ማሰባሰብ ፕሮግራም ስላለ የተመቸው ሁሉ እንዲሁም ያልተመቸውም በማመቻቸት አብራችሁን እንድትሄዱ ስንል በትህትና እንጠይቃለን
ሴቶች 5:00 ላይ 25 አስባልት ጋር እንድትገኙ
ወንዶች 4:30 ላይ 25 አስባልት ጋር እንድትገኙ
ትራንስፖርት ተዘጋጅቱዋል
مدرسة شيخ الإسلام إبن تيمية رحمه الله
Forwarded from Abdelsemed Jemal