Abbay TV
7.1K subscribers
7.67K photos
8 videos
1.78K links
Abbay TV 'News & Entertainment"
Download Telegram
አርቲስት ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

አንጋፋው ፀሐፌ ተውኔት፣ አዘጋጅ እና ተዋናይ ሰለሞን አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተገልጿል፡፡

በ"አብዬ ዘርጋው" የሬዲዮ ድራማ ይበልጥ የሚታወቀው ሰለሞን አለሙ በ5 ቋንቋዎች ከ500 በላይ የሬዲዮ ድራማዎችን፣ የመድረክ ቴአትሮችን እና መነባንቦችን ሰርቷል።

ለአብነትም፥ ከዳንኪራው ጀርባ፣ ፍራሽ ሜዳ፣ ገመዱ እና አዙሪትን የመሳሰሉ ተወዳጅ ስራዎች አበርክቷል።

በኢትዮጵያ ሬዲዮ ታሪክ በተለይ ከ1975-1980 ገናና ስራዎችን ያበረከተበት ወርቃማ ዘመኑ ነበር።

ሰለሞን በቅርቡ ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሌሊቱን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

@Abbay_Media
ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ መታሰሩን ጠበቃው ገለፀ፡፡

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በድጋሚ መታሰሩን ጠበቃው ታደለ ገ/መድህን ገልጿል።

ጋዜጠኛው ዛሬ ማለዳ ላይ ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል በለበሱ የፀጥታ አካላት መወሰዱን ነው ጠበቃው መናገሩን ታሪክ አዱኛ ዘግባለች፡፡

ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ባሳለፍነው ሳምንት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በሰጠው የዋስትና መብት ከእስር መፈታቱ ይታወሳል።

@Abbay_Media
https://www.youtube.com/channel/UClZPsyv-1PgxCqDHfBIq46A
"#Man_Yikenes (ማን ይቀነስ) በአርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝ የሚቀርብ ልብ አንጠልጣይ የጨዋታ ትዕይንት (Game Show).

ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት በዓባይ ሚዲያ ቴሌቪዥን

Sunday @ 7:00 PM only on Abbay Media TV"
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥር በማውጣት ወንጀል መከሰሱ ተገለፀ፡፡

መንግስት በእስር ላይ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን መክሰሱንና ክሱ ትናንት የተከፈተ ሲሆን ዛሬ ለተከሳሽ ደርሶ በችሎት መነበቡ ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል፡፡

ጋዜጠኛው በሚሰራበት ፍትሕ መጽሔት የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥራዊ ተግባራትን በማውጣትና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት ዐቃቤ ሕግ ክስ ማቅረቡን የተናገሩት ጠበቃው፤ ጋዜጠኛው በበኩሉ ሀሳብን ከመግለጽና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ ከመጻፍ ባለፈ ምንም ወንጀል እንዳልፈጸመ ለችሎቱ ማስረዳቱንም አክለዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ቋሚ አድራሻ ያለውና ህግን የሚያከብር በመሆኑፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ጠይቀዋል፡፡

ዐቃቢ ህግ ጋዜጠኛው በተደራራቢ ክስ በመከሰሱና በልዩ ሁኔታ ዋስትና ሊያስከለክል እንደሚችልና የሰበር ውሳኔ ድንጋጌዎች ዋስትናን ሊያስከለክል እንደሚችል ጠቅሶ ዋስትና ሊሰጥ አይገባም ሲል ተከራክሯል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለአርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱም ተዘግቧል፡፡

@Abbay_Media
በመዲናዋ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ውል ለተጨማሪ ስድስት ወራት ተራዘመ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶችን ውል ለተጨማሪ ስድስት ወራት ማራዘማቸው ተገልጿል፡፡

ውሉ ከመጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ፊታችን መስከረም 2 ቀን 2015 ዓ.ም ነው የተራዘመው ፡፡

በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደ ስራ ከገቡ በኋላ በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተገልጿል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት በሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በኩል ስምሪት እየተሰጣቸው የሚገኙ አውቶብሶች አገልግሎት መስጠታቸውን እንዲቀጥሉ ውላቸው መራዘሙን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሁሉም አውቶብሶች ጂፒ ኤስ በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር ስራው የተጠናከረ እና አገልግሎት አሰጣጡም የተሻሻለ እንዲሆን በትኩረት እንዲከወንም ቢሮው አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ከጥቅምት 9 ቀን2013 ዓ.ም ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች በኪራይ መልክ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ የሚታወስ ነው።

@Abbay_Media
በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በሁሉም ክፍለ ከተማዎች መሠጠት ተጀምሯል::

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተመላክቷል።

የፈተና ደህንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በዚህም 71 ሺህ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተመሳሳይ በኦሮሚያ እና በሀሪሪ ክልሎች የ2014 የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል፡፡


@Abbay_Media
የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዋሳኝ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች ዙርያ መከሩ፡፡

የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን የሰላምና የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በእንጅባራ ከተማ መክረዋል፡፡

በምክክር መድረኩም በክልሎቹ አዋሳኝ በሆኑ የመተከል ዞንና ወረዳዎች በግብረ ሃይሉ አማካኝነት የተሰሩ የ5 ወራት አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

በወቅቱም የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ፤ ትናንት የነበረውን አለመግባባት በውይይት በመፍታትና የግጭት መንስኤ የሆኑ አጀንዳዎችን በማስወገድ የአዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ የሰላምና የልማት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ምክክሩ በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ነውም ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አቢዮት አልቦሮን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮችና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መገኘታቸውን ከመተከል ዞን ኮሚኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Abbay_Media
መከላከያ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የክብር ኒሻን አበረከተ፡፡

መከላከያ ሰራዊት የአፋር ክልል ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻ ፣ ህዝባዊ ሰራዊትና የአፋር ህዝብ ህወሀት በአፋር ክልል በኩል በመግባት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ያደረገውን ሙከራ በመመከት ለከፈሉት ሀገርን የማዳን መስዋእትነት እንዲሁም ዘመቻውን በዋናነት የመሩትን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ፈጽመውታል ላለው ጀብድ እውቅና ሰጥቷል።

ህወሀት የአፋርን ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በወረራ በመያዝ በከባድ መሳሪያ በፈጸመው ጥቃት ንፁሀን አርብቶ አደሮችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ከቤት ንብረታቸው በማፈናቀል እንዲሁም የመንግስትና የግለሰብ ንብረቶችን በመዝረፍ ቀሪውን ደግሞ ማውደሙ ይታወሳል፡፡

የአፋር ህዝብ በበኩሉ ከክልሉ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ህዝባዊ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት ታላቅ ድልን ማስመዝገብ መቻላቸውን ነው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያስታወሰው፡፡

በመሆኑም ለዚህ ብርቱ ጀግንነት የሀገር መከላከያ ሰራዊት እውቅና መስጠቱ ነው የተመላከተው፡፡

@Abbay_Media
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቲዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡

ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ በመጣስ ወደ ከተማ እንዳይገቡ የተደረጉ 2 ተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በመውረስ የጫኑት ነዳጅ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ በዛሬው እለት 2 ተጨማሪ ነዳጅ የጫኑ ተደብቀው በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር ተይዘው የጫኑት ከ80 ሺህ ሊትር በላይ የሚገመት ነዳጅም በማደያዎች በኩል መከፋፈሉን ገልፀዋል።

እስከ አሁን ድረስ ቢሮው በወሰደው እርምጃ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን ወርሶ የጫኑት ነዳጅ በማደያዎች በኩል ለተጠቃሚዎች እንዲከፋፈል መደረጉን አብራርተው፤ ሕግ አክብረው በማይሰሩና ሆን ብለው እጥረቱ እንዲባባስ በሚያደርጉ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል።


@Abbay_Media
ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር መፍጠሩ ተገለጸ፡፡

ክልሎች ያዘዙትን የተሽከርካሪ ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው የአሰራር ችግር ፈጥሮብኛል ሲል የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ገልጿል።

የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሞን አምባቸው ን ጠቅሶ ፋና እንደዘገበው ክልሎች እንዲመረት ያዘዙትን የተሽከርካሪ ስሌዳ ተገቢውን ክፍያ ከፍለው እንዲውስዱ እና ለተጠቃሚው እንዲያደርሱ አሳስበዋል።

በሀገሪቱ ውስጥ ያሉትን የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች የማተምና የማሰራጨት ስራን የሚያከናውነው የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በጊዜያዊነት ተፈጥሮ የነበረው የምርት እጥረት ቀርፎ ወደ ስራ መግባቱን አስረድተዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም ለክልልና ለአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮዎች በፈለጉት አይነትና መጠን የተሽከርካሪ ሰሌዳዎችን አምርቶ በማከፋፈል ላይ መሆኑን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

በተቃራኒውም በተለይ ክልሎች አዘው ያስመረቱትን ሰሌዳ በጊዜው ባለመውሰዳቸው ለአሰራር ችግር እየፈጠረባቸው እንደሆነ አመላክተዋል፡፡

ክልሎች ያስመረቱትን ሰሌዳ አስፈላጊውን ክፍያ ከፍለው እንዲወስዱና ለተጠቃሚው እንዲያደርሱ ያሳሰቡት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ በቀጣይ መሠል ችግሮች እንዳያጋጥሙ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በጋራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

@Abbay_Media