AYA Media II አያ ሚዲያ
156 subscribers
53 photos
4 videos
2 files
72 links
AYA Media II አያ ሚዲያ

ትላንትን ማያ – ነገን ማደሽያ

ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን!

★ አነቃቂ መልዕክቶች
★ ማህበራዊ ጉዳዮች
★ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ቻናል!

#አያ_ሚዲያ

https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv
Download Telegram
ንግግርና ተግባር እንዳይቃረን!

ልጆቻችንን አንድ ነገር አዘን እኛ በተቃራኒው አንሥራ። እውነት እንዲናገሩ አየመከርን እኛ አንዋሽ። ሰላት እንዲሰግዱ እያስተማርን እኛ አንተው፤ ዝንጉ አንሁን። የንግግርና የተግባር መጣጣም ለልጆች አስተዳደግ ቁልፍ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ምስጢር መጠበቅን ማስተማር!

ልጆቻችን የቤታቸውን ምስጢር መጠበቅ እንዳለባቸው እናስተምራቸው። በቤት ውስጥ የሚነገረውንና የሚደረገውን ነገር ሁሉ ለውጭ ሰው ማውራት እንደሌለባቸው እናስረዳቸው። ይህ ቤትን ከብዙ ችግር ይጠብቃል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
አታስንፏቸው!

ልጆችን በስንፍና ማሳደግ ተገቢ አይደለም። የድካምና የልፋት ውጤት በዱንያም በአኺራም መልካም ነው። በዱንያ ላይ የበላይነትና በአኺራ ላይ ደስታ የሚገኘው በድካም ድልድይ ላይ ካለፉ በኋላ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ሂዳያ ከአላህ ነው!

ወላጆች ሆይ! ልጆቻችንን ለማቅናት የቱንም ያህል ብንጥር፤ ሂዳያ የሚሰጠው (ቅን መንገድን የሚለግሰው) አላህ ብቻ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ የግድ ይላል። የእኛ ድርሻ ተገቢውን ጥረት ማድረግና ልጆቻችንን እንዲያቀናልን አላህን መለመን ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
💰 ሐላል ገንዘብ እና የልጆች መልካምነት

ውድ ወላጅ ሆይ! ምግብህን፤ መጠጥህንና ልብስህን ሐላል አድርግ። ወደ ቤት የሚገባው ገንዘብ ሐላል ሲሆን በልጆች ላይ በረካ ያሰፍናል፤ ለነሱም የምናደርገው ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል። ሐራም የተቀላቀለበት ገቢ ግን በረከትን ያነሳል፣ ዱዓንም ይከለክላል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
በልጆች ፊት ከጠብ ራቁ!

ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጨቃጨቅና መጣላት በልጆች ሥነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። ከነዚህም መካከል:
የደህንነት ስሜት ማጣት፦ ቤት ለልጆች ዋነኛ የደህንነትና የመረጋጊያ ቦታቸው ነው። ወላጆች ሲጣሉ ይህ የደህንነት ስሜት ይናጋል። ልጆች ፍርሃት፣ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይሰማቸዋል።

ይቀጥላል…

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውድቀት ለስኬት

እያንዳንዱ ወላጅ ልጁን ከህመም፣ ከችግርና ከውድቀት ጠብቆ ማሳደግ ይፈልጋል። ይህ ተግባር ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ነገር ግን ልጆቻችንን በምቾት ብቻ አጥረን ስናሳድግ የህይወትን ወሳኝ ትምህርት እየነፈግናቸው ነው፦ እርሱም የመቋቋም ችሎታ ነው።

ህይወት ሁልጊዜ ምቹና ለስላሳ መንገድ አይደለችም። ልጆች ሲወድቁ፤ ሲሳሳቱ ወይም ሲያጡ እንዴት መነሳት እንዳለባቸው፤ ከስህተታቸው እንዴት መማር እንዳለባቸውና እንደገና እንዴት መሞከር እንዳለባቸው ይማራሉ። የእኛ ሥራ መንገዳቸውን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን ከወደቁ በኋላ እጃቸውን ይዘን "ተነስ! እንደገና ሞክር!" ማለትም ነው።

ያለ ውድቀት ስኬት ጣዕም የለውም። ልጅዎ ከብስክሌት ሲወድቅ እግሩ ሊቆስል ይችላል፤ ነገር ግን በራሱ ሲነሳና መንዳት ሲችል የሚያገኘው በራስ መተማመን በምንም ነገር አይተካም። ውድቀትን እንዲፈሩ ሳይሆን እንዲማሩበት አስተምሯቸው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የገቡትን ቃል ያክብሩ!

"ጥሩ ውጤት ካመጣህ መጫወቻ እገዛልሃለሁ!" ብለው ለልጅዎ ቃል ገብተው ቃልዎን ካልፈፀሙ ልጅዎ በተዘዋዋሪ የሚማረው አንድ ነገር ነው፦ "የወላጆቼ ቃል አይታመንም"

ለልጆች፤ የወላጅ ቃል ኪዳን እንደ አለት የጸና መሆን አለበት። ቃልን ማክበር የመተማመን መሰረት ነው። እርስዎ ለገቡት ትንሽ ቃል ሲታመኑ፤ ልጅዎም በትልቁ የህይወት ጉዳይ ላይ እርስዎን ማመን ይማራል።

ቃልዎን መሙላት ካልቻሉ ምክንያቱን በሐቀኝነት ያስረዱና ይቅርታ ይጠይቁ። ይህ "ሁኔታዎች ሊለወጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ታማኝነት ወሳኝ ነው" የሚል ትምህርት ያስተላልፋል። የመተማመን ድልድይ የሚገነባው በእያንዳንዱ በሚከበር ቃል ኪዳን ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውጤታማ የአስተዳደግ ስልት

ውጤታማ አስተዳደግ አንድ ወጥ መንገድ የለውም። ይልቁንም እንደ ሁኔታው የማስተማር፤ የማስጠንቀቅ፤ የሽልማት፤ የቅጣት፤ የማበረታቻና የማነቃቂያ ዘዴዎችን በብልሃት መጠቀምን ይጠይቃል። ወላጅ የልጁን ስብዕና በመልካም ለማነጽ እነዚህን ሁሉ መሳሪያዎች በአግባቡና በሚዛናዊነት ሊጠቀምባቸው ይገባል። አንዱን ብቻ ይዞ ሌላውን መተው አስተዳደጉን ጎዶሎ ያደርገዋል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የጨዋታ ኃይል!

ብዙ ጊዜ ጨዋታን እንደ ባከነ ጊዜ እናስበዋለን። ነገር ግን እውነታው በተለይ ለታዳጊ ህፃናት፤ ጨዋታ ራሱ ትምህርት ነው። ጨዋታ የልጆች ሥራ ነው፤ ዓለማቸውን የሚያገኙበት፤ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትና ስሜታቸውን የሚገልጹበት ዋናው መንገድ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የአያቶች ፍቅር እና የወላጆች ድንበር

የአያቶች ፍቅር ለልጆች እድገት ትልቅ ስጦታ ነው። ነገር ግን ይህ ንጹሕ ፍቅር ድንበሩን አልፎ የወላጆችን የአስተዳደግ ስርዓት ውስጥ ሲገባ፤ በጎ ከመሆን ይልቅ የችግር ምንጭ ሊሆን ይችላል። ስለሆነ ይህን አደጋ ቀደም ብሎ ለመቆጣጠር ጤናማ ድንበርን በጥበብና በአክብሮት ማስቀመጥ ይገባል።

ድንበር ማበጀት የአያቶችን ፍቅር መቃወም ሳይሆን፤ ለልጅዎ ጤናማ እና ወጥ የሆነ የእድገት መስመር ማስቀመጥ ነው። ፍቅርና ሥርዓት ሲጣመሩ፤ ውጤቱ በሥነ ምግባር የታነጸና ለሁሉም ክብር ያለው ትውልድ ይሆናል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የአላህን ውዴታ ማስረፅ!

የአስተዳደግ ጉዞ የሚጀምረው የአላህን ውዴታ በልጆች ልብ ውስጥ በማስረፅ ሲሆን ተርቢያው ስኬታማ ያደርጋል። ስለ አላህ ውብ ስሞችና ምሉዕ ባህሪያት፤ ድንቅ ሥራዎቹ፤ ስለ ልቅናውና ግርማው በመልካም ቃላት እያዋዛን ስናስረዳቸው፤ በልባቸው ውስጥ የአላህ ክብርና ውዴታ ይሰርጻል። ይህ መሰረት ከተጣለ በኋላ፤ ስለ አላህ መብቶችና ስለ ሥነ-ምግባር ማስተማር ቀላል ይሆናል። ውዴታ የቀደመው ትምህርት ልብ ውስጥ ይቀራል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጅዎን ለራሱ ብቻ ሲያስብ ወይም ትኩረት ሲሰጥ "ራስ ወዳድ" በማለት አይፈርጁት። ይልቁንም፤ እንዴት ማሰብና የሌሎችን ስሜት ግምት ውስጥ ማስገባት እንዳለበት ያስተምሩት። እንዲሁም ሰዎችን በንግግራቸው ብቻ ሳይሆን ከሁኔታቸው በመነሳት እንዲረዳቸው ያድርጉት።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጅዎን በፍቅርና በደግነት ይያዙ!

ምክንያቱም እናንተ ለልጃችሁት የምትሰጡት ፍቅር እዝነትና እንክብካቤ፤ እሱም ለሌሎች ርህራሄ እንዲያሳይ ያስተምረዋል፤ እንዲሁም የሚያጋጥሙትን መከራዎችና እንቅፋቶች እንዲሻገር ይረዳዋል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውድ ወላጅ ሆይ!

ልጅዎን በኢስላማዊ ተርቢያ ለማሳደግ ጊዜ ከሌለዎ፤ ልጅዎን ለማበላሸት ጊዜ ያለው አካል እንዳለ ይወቁ። እንዲያውም ልጅዎን ለማበላሸትና መጥፎ ሥነምግባርን ለማስተማር ሙሉ በሙሉ ጊዜውን የሰጠ አካል አለ።

ከኢስላምና የሰው ልጅ ጠላቶች ዋነኛ እቅዶቻቸው አንዱ የሙስሊም ልጆችን ማበላሸት ነው። ምክንያቱም የልጆች መበላሸት ማለት የቀጣይ ትውልዶች መበላሸት ማለት ነውና። ስለዚህ ለዚህ ነገር ንቁ ይሁኑ፤ ለልጅዎ ከጊዜዎ፣ ከትኩረትዎና ከጉልበትዎ የተወሰነውን ይስጡ።

አደራ ለኢስላም ጠላቶች ቀላል ሲሳይ እንዲሆኑ አድርጋችሁ እንዳትተዋቸው።

በአላህ ፈቃድ መጪውን ትውልድ ለማዳንና የተርቢያ ጉዞዎ ለማገዝ የተቋቋመውን ሂዳያ ተርቢያ ለወዳጅ ዘመድዎ በማስተዋወቅ የበኩልዎን አሻራ ያሳርፉ!

ቻናላችንን በማስተዋወቅ እያንዳንዱ ሙስሊም ቤት እንድንገባ ያግዙን!

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውድ እናት ሆይ!

አንቺ የልጆችሽ የመጀመሪያ አስተማሪ፣ ሙረቢያቸው፣ አርዓያቸው እና ምርጥ ጓደኛቸው ብትሆኚስ?!!

ለዚህ እንዲረዳሽ ዲንሽን በአግባቡ ተገንዘቢ፤ ተማሪ፤ አንብቢ፤ ዕውቀትሽን አስፊ፤ ቁርኣንንና ሐዲሦችን በቃልሽ ያዢ፤ ራስሽንም እነርሱን በዲን፤ በእምነት፤ በሥነ-ልቦና እና በፊቅህ (የእስልምና ህግጋት) ለመቅረፅ የሚረዳሽን ዕውቀት አዳብሪ።

ኡማው አንቺን እና አንቺ የምታፈሪውን መልካም ትውልድ በብርቱ ይፈልጋል!

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የስብዕና ግንባታ!

የወላጆቻቸውን ቅርበትና ልዩ እንክብካቤ የሚያገኙ ልጆች ወደፊት በህይወታቸው የበለጠ ስኬታማ የመሆን እድላቸው ሰፊና ስብዕናቸውም ጠንካራ ይሆናል።

ከልጆችዎ ጋር መልካምና ጠንካራ ግንኙነት መፍጠር፤ ትዕዛዞችዎን በቀላሉ እንዲቀበሉ ያደርጋቸዋል። እንዲሁም ስህተት ሲሰሩ የሚሰጣቸውን ቅጣት አስፈላጊነቱን ተረድተውና አምነው እንዲቀበሉት ያደርጋቸዋል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ሚዛንዎን ይጠብቁ!

ሚዛናዊ እና ደስተኛ ልጆችን ማፍራት ይፈልጋሉ? መልሱ በአስተዳደጋችሁ ሚዛን ላይ ነው!

⚖️ ይህን አመዛዝኑ፡

ውዳሴ  ከ ገንቢ ነቀፌታ
ሳቅ  ከ ቁጣ (ድንበር ለማሳየት)
ስጦታ  ከ መከልከል (ለጥፋት)

ሁልጊዜ መሸለምም ሆነ ሁልጊዜ መቅጣት ሚዛናዊ አይደለም። ሚዛኑን የጠበቀ አስተዳደግ በሥነ ምግባሩ የታነጸና በራሱ የሚተማመን ደስተኛ ልጅ ይፈጥራል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ሂዳያ

💫 @HidayaTerbiya 💫
👨‍👩‍👧‍👦 ከአንድ በላይ ልጆች ላሏችሁ ወላጆች ወርቃማ ምክሮች

የቀጠለ …

6. 👨‍👩‍👧‍👦 እንደ አንድ ቡድን ቁሙ

በተለይ በችግር ጊዜ ቤተሰቡ እንደ አንድ ቡድን እንዲቆም አስተምሯቸው። የችግር ጊዜያት የቤተሰብን አንድነት ለማጠንከር ከሁሉ የተሻሉ ወቅቶች ናቸው።

7. 📜 ለእያንዳንዱ ልጅ የተለየ መመሪያ

የልጆች ግንዛቤና ብስለት ይለያያል። ስለዚህ ከእያንዳንዱ ልጅ የሚጠብቁት ነገር እንደ ዕድሜውና እንደ አቅሙ ሊወሰን ይገባል።

8. ማዳላትን አስወግዱ

በምንም አይነት ሁኔታ ለአንዱ ልጅ እንዳታዳሉ። ሁሉም ልጆች እኩል ፍቅርና ትኩረት እንደሚያገኙ እንዲሰማቸው አድርጉ።

9. 🎲 ግንኙነታችሁን አሳምሩ

አንዳንድ ጊዜ ከሁሉም ልጆች ጋር በጋራ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከእያንዳንዱ ልጅ ጋር አንድ ለአንድ በመሆን ልዩ ጊዜ ያሳልፉ። ይህ ከእያንዳንዳቸው ጋር ያላችሁን ትስስር ያጠነክራል።

10. 🌟 ጠንካራ ጎናቸውን እወቁ

የእያንዳንዱን ልጅ ልዩ ተሰጥኦና ጠንካራ ጎን ለይታችሁ እወቁ፤ እንዲሁም አበረታቱት። ይህ ልጁ በራሱ እንዲተማመንና ጠንካራ ስብዕና እንዲኖረው ያደርገዋል።

መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ!

ይህን ጠቃሚ መልዕክት ለሌሎች ወላጆች ያጋሩ!

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫