AYA Media II አያ ሚዲያ
156 subscribers
53 photos
4 videos
2 files
72 links
AYA Media II አያ ሚዲያ

ትላንትን ማያ – ነገን ማደሽያ

ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን!

★ አነቃቂ መልዕክቶች
★ ማህበራዊ ጉዳዮች
★ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ቻናል!

#አያ_ሚዲያ

https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv
Download Telegram
💰 የአስተዳደግ ኢንቨስትመንት 💰

ለልጅዎ ጠቃሚ መጽሐፍትን መግዛት ኢንቨስትመንት እንጂ ወጪ አይደለም! ልጅዎ አዕምሮ ላይ የሚዘሩት እያንዳንዱ መልካም ዘር ነገ ትልቅ ዛፍ ሆኖ ፍሬ ያፈራል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya #HidayaBook

💫 @HidayaTerbiya 💫
🕌 ውዱእ እና ሶላት 💧

ልጅዎን የምግብ ስርአት በማእድ ላይ እንደሚያስተምሩት፤ የሶላትን ስርዓትም በተግባር ውዱእ አብረውት እያደረጉ፤ አብረውት እየሰገዱ ያስተምሩት። ተግባራዊ ትምህርት አይረሳም።


#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጆቻችንን መልካምና ታላቅ በሆነ ሥነምግባር አንፀን ስናሳድግ፤ ለዚህ የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈል መታገስ አለብን። ምክንያቱም ከፍታ መውጣት ሁልጊዜ ዋጋ ያስከፍላልና ነው፤ ብዙ ጊዜ መውደቅ ወይም ዝቅታ ነው ቀላል የሚሆነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
ለልጅዎ ወላጅ ብቻ ሳይሆን የልብ ወዳጅም ይሁኑ። ከልጅዎ ጋር ያለዎትን ግንኙነት በፅኑ ፍቅርና ወዳጅነት ይገንቡት። ይህንንም በፈገግታና በጨዋታ አጅበው ያቅርቡላቸው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
"አስተምሯቸው፤ አደብ አስይዟቸው"

ለልጅዎ እምነትን፣ ንጽህናንና ሰላትን ያስተምሩት፤ ዘጠኝ ዓመት ሲሞላው ከተዋት በቀስታ ይገስጹት፤ ቁርኣንን በልቡ እንዲይዝ ያደርጉ፤ የነብዩን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሐዲሥ ያስተምሩት፤ የሚችለውን ያህል ዕውቀት ያስጨብጡት፤ መጥፎን እንዲጠላ፤ በመልካም ሥነ-ምግባር እንዲዋብ ያደርጉት። ይህ የመዝሪያ ወቅት ነውና ከማስተማር ፈጽሞ ወደ ኋላ አትበሉ፤ አትሰልቹ።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
የልጆች አስተዳደግ በወላጆች ላይ የተጣለ አደራ ነው! ይህንን ኃላፊነት ለቤት ሠራተኞች አሳልፎ መስጠት የልጆች ከትክክለኛው መንገድ ማፈንገጥና የሥነ ምግባርን መበላሸት ሊያስከትል ይችላል!

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ  #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጆችዎን ከልጅነታቸው ጀምሮ በውይይት የመግባባትን ባህል አስተምሩዋቸው፤ ይህም በጉርምስናና በወጣትነት ዘመናቸው ከቤተሰብ ጋር በግልጽ ለመነጋገር ክፍት እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጆችዎን የንግግር ሥርዓት አስተምሯቸው፤ ማመስገንን፤ ፈቃድ መጠየቅን፤ ይቅርታ ማለትን፤ ማዳመጥን፤ ቃል አለመቀማትን፤ እንዲሁም ለተደረገላቸው ውለታ ምስጋናን መግለጽን አስተምሯቸው። ይህም እነዚህ ሥርዓቶች አድገውም ለነገ ሕይወታቸው አብሯቸው የሚዘልቅ ልማድ እንዲሆንላቸው ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya

💫 @HidayaTerbiya 💫
ልጆቼን ለመልካም ሥነምግባራቸው እንዴት ላበረታታቸው?

ልጅዎ ሲታዘዝዎ ሳሙትና አቅፉት፤ ወይም ላሳየው መልካም ባህሪ አወድሱት። ለምሳሌ፦ "ጎበዝ!" "ጀዛከላሁ ኸይራ" (አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ!) "ድንቅ ሥራ ነው!" በማለት አበረታቱት።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
💡 የልጅዎን ተሰጥዖ ይወቁና ያሳድጉ! 💡

እያንዳንዱ ልጅ አላህ የሰጠው ልዩ ተሰጥዖና ችሎታ አለው። የወላጅ ድርሻ ይህንን ተሰጥዖ ማወቅና ከሸሪዓ ጋር በማይጋጭ መልኩ እንዲያሳድገው መርዳትና ማበረታታት ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ንግግርና ተግባር እንዳይቃረን!

ልጆቻችንን አንድ ነገር አዘን እኛ በተቃራኒው አንሥራ። እውነት እንዲናገሩ አየመከርን እኛ አንዋሽ። ሰላት እንዲሰግዱ እያስተማርን እኛ አንተው፤ ዝንጉ አንሁን። የንግግርና የተግባር መጣጣም ለልጆች አስተዳደግ ቁልፍ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ምስጢር መጠበቅን ማስተማር!

ልጆቻችን የቤታቸውን ምስጢር መጠበቅ እንዳለባቸው እናስተምራቸው። በቤት ውስጥ የሚነገረውንና የሚደረገውን ነገር ሁሉ ለውጭ ሰው ማውራት እንደሌለባቸው እናስረዳቸው። ይህ ቤትን ከብዙ ችግር ይጠብቃል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
አታስንፏቸው!

ልጆችን በስንፍና ማሳደግ ተገቢ አይደለም። የድካምና የልፋት ውጤት በዱንያም በአኺራም መልካም ነው። በዱንያ ላይ የበላይነትና በአኺራ ላይ ደስታ የሚገኘው በድካም ድልድይ ላይ ካለፉ በኋላ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ሂዳያ ከአላህ ነው!

ወላጆች ሆይ! ልጆቻችንን ለማቅናት የቱንም ያህል ብንጥር፤ ሂዳያ የሚሰጠው (ቅን መንገድን የሚለግሰው) አላህ ብቻ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ የግድ ይላል። የእኛ ድርሻ ተገቢውን ጥረት ማድረግና ልጆቻችንን እንዲያቀናልን አላህን መለመን ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
💰 ሐላል ገንዘብ እና የልጆች መልካምነት

ውድ ወላጅ ሆይ! ምግብህን፤ መጠጥህንና ልብስህን ሐላል አድርግ። ወደ ቤት የሚገባው ገንዘብ ሐላል ሲሆን በልጆች ላይ በረካ ያሰፍናል፤ ለነሱም የምናደርገው ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል። ሐራም የተቀላቀለበት ገቢ ግን በረከትን ያነሳል፣ ዱዓንም ይከለክላል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
በልጆች ፊት ከጠብ ራቁ!

ወላጆች በልጆቻቸው ፊት መጨቃጨቅና መጣላት በልጆች ሥነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። ከነዚህም መካከል:
የደህንነት ስሜት ማጣት፦ ቤት ለልጆች ዋነኛ የደህንነትና የመረጋጊያ ቦታቸው ነው። ወላጆች ሲጣሉ ይህ የደህንነት ስሜት ይናጋል። ልጆች ፍርሃት፣ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይሰማቸዋል።

ይቀጥላል…

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውድቀት ለስኬት

እያንዳንዱ ወላጅ ልጁን ከህመም፣ ከችግርና ከውድቀት ጠብቆ ማሳደግ ይፈልጋል። ይህ ተግባር ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ነገር ግን ልጆቻችንን በምቾት ብቻ አጥረን ስናሳድግ የህይወትን ወሳኝ ትምህርት እየነፈግናቸው ነው፦ እርሱም የመቋቋም ችሎታ ነው።

ህይወት ሁልጊዜ ምቹና ለስላሳ መንገድ አይደለችም። ልጆች ሲወድቁ፤ ሲሳሳቱ ወይም ሲያጡ እንዴት መነሳት እንዳለባቸው፤ ከስህተታቸው እንዴት መማር እንዳለባቸውና እንደገና እንዴት መሞከር እንዳለባቸው ይማራሉ። የእኛ ሥራ መንገዳቸውን ማፅዳት ብቻ ሳይሆን ከወደቁ በኋላ እጃቸውን ይዘን "ተነስ! እንደገና ሞክር!" ማለትም ነው።

ያለ ውድቀት ስኬት ጣዕም የለውም። ልጅዎ ከብስክሌት ሲወድቅ እግሩ ሊቆስል ይችላል፤ ነገር ግን በራሱ ሲነሳና መንዳት ሲችል የሚያገኘው በራስ መተማመን በምንም ነገር አይተካም። ውድቀትን እንዲፈሩ ሳይሆን እንዲማሩበት አስተምሯቸው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የገቡትን ቃል ያክብሩ!

"ጥሩ ውጤት ካመጣህ መጫወቻ እገዛልሃለሁ!" ብለው ለልጅዎ ቃል ገብተው ቃልዎን ካልፈፀሙ ልጅዎ በተዘዋዋሪ የሚማረው አንድ ነገር ነው፦ "የወላጆቼ ቃል አይታመንም"

ለልጆች፤ የወላጅ ቃል ኪዳን እንደ አለት የጸና መሆን አለበት። ቃልን ማክበር የመተማመን መሰረት ነው። እርስዎ ለገቡት ትንሽ ቃል ሲታመኑ፤ ልጅዎም በትልቁ የህይወት ጉዳይ ላይ እርስዎን ማመን ይማራል።

ቃልዎን መሙላት ካልቻሉ ምክንያቱን በሐቀኝነት ያስረዱና ይቅርታ ይጠይቁ። ይህ "ሁኔታዎች ሊለወጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ታማኝነት ወሳኝ ነው" የሚል ትምህርት ያስተላልፋል። የመተማመን ድልድይ የሚገነባው በእያንዳንዱ በሚከበር ቃል ኪዳን ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
ውጤታማ የአስተዳደግ ስልት

ውጤታማ አስተዳደግ አንድ ወጥ መንገድ የለውም። ይልቁንም እንደ ሁኔታው የማስተማር፤ የማስጠንቀቅ፤ የሽልማት፤ የቅጣት፤ የማበረታቻና የማነቃቂያ ዘዴዎችን በብልሃት መጠቀምን ይጠይቃል። ወላጅ የልጁን ስብዕና በመልካም ለማነጽ እነዚህን ሁሉ መሳሪያዎች በአግባቡና በሚዛናዊነት ሊጠቀምባቸው ይገባል። አንዱን ብቻ ይዞ ሌላውን መተው አስተዳደጉን ጎዶሎ ያደርገዋል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የጨዋታ ኃይል!

ብዙ ጊዜ ጨዋታን እንደ ባከነ ጊዜ እናስበዋለን። ነገር ግን እውነታው በተለይ ለታዳጊ ህፃናት፤ ጨዋታ ራሱ ትምህርት ነው። ጨዋታ የልጆች ሥራ ነው፤ ዓለማቸውን የሚያገኙበት፤ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትና ስሜታቸውን የሚገልጹበት ዋናው መንገድ ነው።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫
የአያቶች ፍቅር እና የወላጆች ድንበር

የአያቶች ፍቅር ለልጆች እድገት ትልቅ ስጦታ ነው። ነገር ግን ይህ ንጹሕ ፍቅር ድንበሩን አልፎ የወላጆችን የአስተዳደግ ስርዓት ውስጥ ሲገባ፤ በጎ ከመሆን ይልቅ የችግር ምንጭ ሊሆን ይችላል። ስለሆነ ይህን አደጋ ቀደም ብሎ ለመቆጣጠር ጤናማ ድንበርን በጥበብና በአክብሮት ማስቀመጥ ይገባል።

ድንበር ማበጀት የአያቶችን ፍቅር መቃወም ሳይሆን፤ ለልጅዎ ጤናማ እና ወጥ የሆነ የእድገት መስመር ማስቀመጥ ነው። ፍቅርና ሥርዓት ሲጣመሩ፤ ውጤቱ በሥነ ምግባር የታነጸና ለሁሉም ክብር ያለው ትውልድ ይሆናል።

#ተርቢያ #የሂዳያ_ትውልድ #Terbiya #HidayaTerbiya #ምክር

💫 @HidayaTerbiya 💫