ድምጸ መልካሞቻችን አሁን በቀጥታ ስርጭት ከተቀባበሉት ከሃምሳ በላይ ከሆኑ ሙዚቃዎች መሀከል የመጀመርያዎቹን ነው ጀባ ያልናችሁ። ሌሎቹን ሌላ ጊዜ እናሰማችኋለን። ከወደዳችሁት በጭብጨባ አበርቷቸው!!!
✋✋✋
እንደምን አደራችሁ! ውሏችሁ ያማረና መልካም ይሁን፤ እናንተም ለሌሎች መልካሞች ሁኑ፤ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና!
"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!
ዛሬም ጠዋታችሁን በድምጸ መልካሞቹ ጥዑም የሙዚቃ ቅብብል እንጀምራለን። መልካም ቆይታ!
እንደምን አደራችሁ! ውሏችሁ ያማረና መልካም ይሁን፤ እናንተም ለሌሎች መልካሞች ሁኑ፤ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና!
"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!
ዛሬም ጠዋታችሁን በድምጸ መልካሞቹ ጥዑም የሙዚቃ ቅብብል እንጀምራለን። መልካም ቆይታ!
እንደተለመደው በውብ ድምጻቸው ጠዋታችንን ያቆነጁልንን የሙዚቃ ድምቀቶች በጭብጨባ አክብሩልን!!!
እንደምን አረፈዳችሁ። መልካም ቀን ሠላማዊ ውሎ ይሁንላችሁ። በግጥምና በድምጸ መልካሞቹ ሙዚቃ ዘና እናድርጋችሁ እስቲ!
📝📝📝
አንቺማ...
እዮብ ዘ ማርያም (ገጣሚ)
ልቧን ለመማረክ
በማራኪ ቃላት ሆዷን ልብላው ብዬ፤
አጭር ግጥም ፃፍኩኝ
በጧፍና ሻማ ለማርያም ተስዬ።
የልቧን ግድግዳ
በመዶሻ ቃላት መትቼ ለመስበር፤
አምጬ አምጬ
የተገላገልኩት ግጥም ይሄ ነበር፦
ይገርመኛል ውዴ
እራሴን ስጠይቅ ስለ ራሴ ሳስብ፤
ይሄን ግን ታውቂያለሽ
አየር ነው እያልኩኝ አንቺን እንደ ምስብ?
አዬ መከራዬ
"ለምን ነው ምትወደው ጥያቄዎች ማከል"
ብላ ጠየቀችኝ
"ምንድነው ምትስበው አየሩ ሲበከል?"
እንደውም ቅሪብኝ
በቃ አፍርሼዋለሁ የፍቅሬን ከተማ፤
አየሬ አይደለሽም...
አየሩን በክለሽ የምታስነጥሺኝ ጉንፋን ነሽ አንቺማ!
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
አንቺማ...
እዮብ ዘ ማርያም (ገጣሚ)
ልቧን ለመማረክ
በማራኪ ቃላት ሆዷን ልብላው ብዬ፤
አጭር ግጥም ፃፍኩኝ
በጧፍና ሻማ ለማርያም ተስዬ።
የልቧን ግድግዳ
በመዶሻ ቃላት መትቼ ለመስበር፤
አምጬ አምጬ
የተገላገልኩት ግጥም ይሄ ነበር፦
ይገርመኛል ውዴ
እራሴን ስጠይቅ ስለ ራሴ ሳስብ፤
ይሄን ግን ታውቂያለሽ
አየር ነው እያልኩኝ አንቺን እንደ ምስብ?
አዬ መከራዬ
"ለምን ነው ምትወደው ጥያቄዎች ማከል"
ብላ ጠየቀችኝ
"ምንድነው ምትስበው አየሩ ሲበከል?"
እንደውም ቅሪብኝ
በቃ አፍርሼዋለሁ የፍቅሬን ከተማ፤
አየሬ አይደለሽም...
አየሩን በክለሽ የምታስነጥሺኝ ጉንፋን ነሽ አንቺማ!
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
Telegram
አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!
ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!
እንደተለመደው በውብ ድምጻቸው እየተቀባበሉ ረፋዳችንን ያቆነጁልንን የሙዚቃ ድምቀቶችን በጭብጨባ አክብሩልን!!!
ለጠቅላላ እውቀት የሚሆን መረጃ!
ስለ ትዕይንተ ምስል (ፊልም)
🎬💿 💿 💿 🎬
የዓለም የመጀመሪያው የምዕራባዊያን ፊልም በሆሊውድ ሳይሆን በእንግሊዝ ብላክበርን መሰራቱ ይፋ ሆነ፡፡
ዘመናዊ ፊልሞች እንደ አሸን የሚመረቱባት ሆሊውድ አልነበረችም የመጀመሪያው የምዕራባዊያን ፊልም የተሰራባት፡፡ እንደ ቢቢሲ ዘገባ የብሪታኒያዋ የብላክበርን ከተማ ነች ተብሏል፡፡
አንድ በዘርፉ የተካሄደ አዲስ ጥናት እንዳመለከተው ምዕራባዊያን የሰሩት የመጀመሪያው ፊልም በላንክሻየር ገጠራማ ሥፍራ በእንግሊዝ መሆኑ ተነግሯል፡፡
“ኪድናፒንግ ባይ ኢንዲያንስ” የተሰኘው ፊልም በ1899 የተሰራ ሲሆን “ዘ ግሬት ትሬን ሮክሪ” ከተባለው ፊልም አራት ዓመት ቀድሞ መሰራቱ ታውቋል፡፡
🎬 🎬 🎬 🎬
https://t.me/ATRACOSE
🎬 🎬 🎬 🎬
ስለ ትዕይንተ ምስል (ፊልም)
🎬💿 💿 💿 🎬
የዓለም የመጀመሪያው የምዕራባዊያን ፊልም በሆሊውድ ሳይሆን በእንግሊዝ ብላክበርን መሰራቱ ይፋ ሆነ፡፡
ዘመናዊ ፊልሞች እንደ አሸን የሚመረቱባት ሆሊውድ አልነበረችም የመጀመሪያው የምዕራባዊያን ፊልም የተሰራባት፡፡ እንደ ቢቢሲ ዘገባ የብሪታኒያዋ የብላክበርን ከተማ ነች ተብሏል፡፡
አንድ በዘርፉ የተካሄደ አዲስ ጥናት እንዳመለከተው ምዕራባዊያን የሰሩት የመጀመሪያው ፊልም በላንክሻየር ገጠራማ ሥፍራ በእንግሊዝ መሆኑ ተነግሯል፡፡
“ኪድናፒንግ ባይ ኢንዲያንስ” የተሰኘው ፊልም በ1899 የተሰራ ሲሆን “ዘ ግሬት ትሬን ሮክሪ” ከተባለው ፊልም አራት ዓመት ቀድሞ መሰራቱ ታውቋል፡፡
🎬 🎬 🎬 🎬
https://t.me/ATRACOSE
🎬 🎬 🎬 🎬
ፈገግ በይልኝ
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
ጦብያ ሆይ ውዲቷ ዘመንሽ ይባረክ፤
ካንቺ የሚታገል፣
እቅም እየከዳው ጉልበቱ ይብረክረክ!
ልርገምልሽ እንጂ፣
ይህን ፈገግታሽን ደብዝዞ እንዳላይ፤
ሊጥልሽ የሚሻ ይውረድ ከራስሽ ላይ፤
የመከራ ፍዳ ይውደቅበት ሰማይ።
ምን መሰለሽማ፣
ከጨምዳዳው ቆዳሽ ከተሸበሸበው፤
ትክ ብዬ ሳይሽ አለኝ የማነበው፣
አለኝ የማስበው።
ምን መሰለሽማ፣
የዘመናት ክታብ የአብሮነት ምስል፤
ከውቡ ፊትሽ ገጽ እርጅና ሲመስል፤
የወላዶች መካን እንክርንዳድ አብቃይ፤
ገበሬ የሌለው አራሚና ነቃይ፤
ወና ባዶ መሬት የታረሰ እርሻ፤
የተፈጥሮ ምስጢር ምርምር መድረሻ፤
ይመስለኛል ፊትሽ፣
የነገር ጅማሮ እስከ መጨረሻ።
ምን መሰለሽማ፣
ስቆ ያልጨረሰው የፈገግታሽ ወሰን፤
ጥረትሽ ነውንዴ ፣
ላሊበላን ሰርቶ ፋሲል የቀለሰን፤
የእጆችሽ መዳፍ፣
መስሎኝ ያስተዋልኩት አክሱምን ያቆመ፤
ሐረርን ተሻግሮ ጥያን የጠቆመ፤
መፍጨርጨር ከሆነ መዳከር ለመሳቅ፤
እንዲህ አልነበረም፣
በልጅነት ዓይኔ ድሮ መልክሽን ሳቅ።
ደስታሽስ ነበረ ከአሁኑ እጥፍ፤
ጀምሮ የማይቆም ምንጩ የማይነጥፍ።
ታድያ ምን ያደርጋል፤
ሻሽሽ እንኳን ጠቁሮ ደስታን ያጨፍጋል።
ሀጫ መሆን ትቶ ሌላ ነው ነጠላሽ፤
ያደፈ እጄታ ንጣቱን ሲያበላሽ፤
ተው የሚለው ያጣ ከልካይም የሌለው፤
እንዳላስቆምልሽ እኔ አንቺን አይደለው።
የልጅ ጨዋታውን የምችል ለመግታት፤
አይደለሁምና ጸባይ የሚቀናኝ እናቴን ሲመታት፤
የገዛ ወንድሜን የማልፍ ዝም ብዬ፤
ባለኝ አቅም ሁሉ አዳፋ እጆቹን በዱላ ከልክዬ፤
መዳፉን ስልልሽ፤
በኔና እሱ ጸብ ሌላ ማዘንን ነው የምጨምርልሽ።
ዓይንሽ ላይ የማየው እኛን የሚያባብል፤
የፍቅር አዝመራ የናትነት ሰብል፤
የሳቅሽ መጀምር ከሚጨልምብኝ፤
ከወንድሜ ጋራ መጣላት ይቅርብኝ፤
ልክ እንደጀመርሽው አሁን በእጅጉ ፈገግ በይልኝ።
ቀን፦ ፳፪/፪/፪፼፲፪ ዓ.ም.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
ጦብያ ሆይ ውዲቷ ዘመንሽ ይባረክ፤
ካንቺ የሚታገል፣
እቅም እየከዳው ጉልበቱ ይብረክረክ!
ልርገምልሽ እንጂ፣
ይህን ፈገግታሽን ደብዝዞ እንዳላይ፤
ሊጥልሽ የሚሻ ይውረድ ከራስሽ ላይ፤
የመከራ ፍዳ ይውደቅበት ሰማይ።
ምን መሰለሽማ፣
ከጨምዳዳው ቆዳሽ ከተሸበሸበው፤
ትክ ብዬ ሳይሽ አለኝ የማነበው፣
አለኝ የማስበው።
ምን መሰለሽማ፣
የዘመናት ክታብ የአብሮነት ምስል፤
ከውቡ ፊትሽ ገጽ እርጅና ሲመስል፤
የወላዶች መካን እንክርንዳድ አብቃይ፤
ገበሬ የሌለው አራሚና ነቃይ፤
ወና ባዶ መሬት የታረሰ እርሻ፤
የተፈጥሮ ምስጢር ምርምር መድረሻ፤
ይመስለኛል ፊትሽ፣
የነገር ጅማሮ እስከ መጨረሻ።
ምን መሰለሽማ፣
ስቆ ያልጨረሰው የፈገግታሽ ወሰን፤
ጥረትሽ ነውንዴ ፣
ላሊበላን ሰርቶ ፋሲል የቀለሰን፤
የእጆችሽ መዳፍ፣
መስሎኝ ያስተዋልኩት አክሱምን ያቆመ፤
ሐረርን ተሻግሮ ጥያን የጠቆመ፤
መፍጨርጨር ከሆነ መዳከር ለመሳቅ፤
እንዲህ አልነበረም፣
በልጅነት ዓይኔ ድሮ መልክሽን ሳቅ።
ደስታሽስ ነበረ ከአሁኑ እጥፍ፤
ጀምሮ የማይቆም ምንጩ የማይነጥፍ።
ታድያ ምን ያደርጋል፤
ሻሽሽ እንኳን ጠቁሮ ደስታን ያጨፍጋል።
ሀጫ መሆን ትቶ ሌላ ነው ነጠላሽ፤
ያደፈ እጄታ ንጣቱን ሲያበላሽ፤
ተው የሚለው ያጣ ከልካይም የሌለው፤
እንዳላስቆምልሽ እኔ አንቺን አይደለው።
የልጅ ጨዋታውን የምችል ለመግታት፤
አይደለሁምና ጸባይ የሚቀናኝ እናቴን ሲመታት፤
የገዛ ወንድሜን የማልፍ ዝም ብዬ፤
ባለኝ አቅም ሁሉ አዳፋ እጆቹን በዱላ ከልክዬ፤
መዳፉን ስልልሽ፤
በኔና እሱ ጸብ ሌላ ማዘንን ነው የምጨምርልሽ።
ዓይንሽ ላይ የማየው እኛን የሚያባብል፤
የፍቅር አዝመራ የናትነት ሰብል፤
የሳቅሽ መጀምር ከሚጨልምብኝ፤
ከወንድሜ ጋራ መጣላት ይቅርብኝ፤
ልክ እንደጀመርሽው አሁን በእጅጉ ፈገግ በይልኝ።
ቀን፦ ፳፪/፪/፪፼፲፪ ዓ.ም.