ክቡራትና ክቡራን እስቲ በድምጸ መልካሞቻችን የቀጥታ ስርጭት የሙዚቃ ቅብብል ዘና እናድርጋችሁ!
የግጥም ስህተትና ሌላም እንከን ካለ ይቅርታ እንጠይቃለን። ቅብብላቸውን ከወደዳችሁት በጭብጨባ ድጋፍ ስጧቸው። እናመሠግናለን!!!
📝📝📝
ደህና እደሪ በቃ!
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
አልነገርኩሽም ወይ አልሰማ አልሺኝ እንጂ፤
ከሰው ይልቅ ላንቺ ምስኪኑ አፈር ነው የልብሽ ወዳጂ።
አርሶ ከሚኖረው ባይተዋር ገበሬ፤
ከሱ ውጪ ያለን ተይው የሰዎቹን ልፍለፋና ወሬ፤
አምላክሽን አምነሽ ለጥ በይ ሀገሬ።
ያውም ከአፈሩ ከተደለደለው፤
ይመችሽ ዘና በይ እኔን ተመልከቺ ተዘርግቼ አለው።
ብቻዬን ነኝ ብለሽ እንዳትሳቀቂ፤
ነዪ ከመሬቱ በፍቅር ውደቂ።
ታድያ ግን ልብ በይ...፣
ልክ እንደዛሬዎች ድንጋይና አፈር ከላይ ካለበሱሽ፤
ሞተሻል ሊሉ ነው ቀስ ብለሽ ተነሽ።
እንዳትሰሚያቸው የሙሾ እዬዬ ግጥም ካወረዱ፤
ህያው መሆንሽን አይተው እስኪረዱ፤
ከአፈርሽ በላይ እግሮችሽን ሰቅለሽ፤
እስኪነጋ ድረስ ጋደም በይና ተኚ ዘና ብለሽ።
.
ቀን ፲፰/፪/፪፼፲፪ ዓ.ም.
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
ደህና እደሪ በቃ!
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
አልነገርኩሽም ወይ አልሰማ አልሺኝ እንጂ፤
ከሰው ይልቅ ላንቺ ምስኪኑ አፈር ነው የልብሽ ወዳጂ።
አርሶ ከሚኖረው ባይተዋር ገበሬ፤
ከሱ ውጪ ያለን ተይው የሰዎቹን ልፍለፋና ወሬ፤
አምላክሽን አምነሽ ለጥ በይ ሀገሬ።
ያውም ከአፈሩ ከተደለደለው፤
ይመችሽ ዘና በይ እኔን ተመልከቺ ተዘርግቼ አለው።
ብቻዬን ነኝ ብለሽ እንዳትሳቀቂ፤
ነዪ ከመሬቱ በፍቅር ውደቂ።
ታድያ ግን ልብ በይ...፣
ልክ እንደዛሬዎች ድንጋይና አፈር ከላይ ካለበሱሽ፤
ሞተሻል ሊሉ ነው ቀስ ብለሽ ተነሽ።
እንዳትሰሚያቸው የሙሾ እዬዬ ግጥም ካወረዱ፤
ህያው መሆንሽን አይተው እስኪረዱ፤
ከአፈርሽ በላይ እግሮችሽን ሰቅለሽ፤
እስኪነጋ ድረስ ጋደም በይና ተኚ ዘና ብለሽ።
.
ቀን ፲፰/፪/፪፼፲፪ ዓ.ም.
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
እንደተለመደው ጥዑም የድምጸ መልካሞቻችንን የቀጥታ ስርጭት የዘፈን ቅብብል አሁን እናሰማችኋለን! አብራችሁን ቆዩ! የግጥም ስህተትና የሚረብሽ ድምጽ ከሰማችሁ ሳይዘጋጁ ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ያቀነቀኑት በቅድሚያ ይቅርታ እንጠይቃለን።