እስቲ ይህን ግጥም እንድገመው!
.
📝📝📝📝📝
ሳይሻል አይቀርም
.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
.
ዙርያ መለስሽን በወስፌ የወጋሽ የናቴ እጄታ፤
መሶብ ሊያበጅ ነው የሚያሰባስበን የፍቅር ገበታ።
ታድያ ምን ያረጋል ለመሶብ ታስቦ የተያዘው ስራ፤
ሰፌድ ሆኖ ቀረ በስምሽ ሊጠራ።
.
ሳይሻል አይቀርም!
መብላቱ ይቅርና እስቲ ቆሻሻውን ለዪ አበጥረሽ፤
ግሳንግሶች ወድቀው ከንጹሐን ፍሬ አምላክ ከደመረሽ።
እንጂስ አልቻልነውም የዘንድሮን ነገር፤
ትውልድ እየጠራን ሞት እየሰረግን፤
ያልተጻፍንበትን ማንበብ ጀምረናል፤
ስለዚህ...
መሶቡ ይቅርና አበጣሪ ሰፌድ ቢኖር ይሻለናል!!!
.
ቀን፦ ፳፫/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
.
📝📝📝📝📝
ሳይሻል አይቀርም
.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
.
ዙርያ መለስሽን በወስፌ የወጋሽ የናቴ እጄታ፤
መሶብ ሊያበጅ ነው የሚያሰባስበን የፍቅር ገበታ።
ታድያ ምን ያረጋል ለመሶብ ታስቦ የተያዘው ስራ፤
ሰፌድ ሆኖ ቀረ በስምሽ ሊጠራ።
.
ሳይሻል አይቀርም!
መብላቱ ይቅርና እስቲ ቆሻሻውን ለዪ አበጥረሽ፤
ግሳንግሶች ወድቀው ከንጹሐን ፍሬ አምላክ ከደመረሽ።
እንጂስ አልቻልነውም የዘንድሮን ነገር፤
ትውልድ እየጠራን ሞት እየሰረግን፤
ያልተጻፍንበትን ማንበብ ጀምረናል፤
ስለዚህ...
መሶቡ ይቅርና አበጣሪ ሰፌድ ቢኖር ይሻለናል!!!
.
ቀን፦ ፳፫/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
እናስታውስዎ
✋✋✋
.
የተወደዳችሁ ክቡራትና ክቡራን ነገ ማግሰኞ ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት ላይ በአዋሽ 90.7 ላይ በድምጸ መልካሞቻችን ድምጽ ታጅበን፣ ግጥምና ትረካን ከመጽሐፍ ትንተና ጋር አጅበን በፈትላችን ላይ እንሾራለንና ቀጠሯችሁን ከኛ ጋር ማድረጉን እንዳትዘነጉት!!!
.
👉ፈትል👈
እንዝርቱን ልዋስሽ አውሺኝ በሞቴ፤
ሳዞረው ሳሾረው...
ባልሆን እንደ እህቴ ባልሆን እንደናቴ፤
የሴት ወግ ነውና...
ያንቺ የሆነውን ጥበብ አላነክትም፤
ባህሉን ገድፌ በሰጠሽኝ እንዝርት ክር አልሰራበትም።
ባይሆን መስዬበት ሆኜልሽ ባላገር፤
ልፍተልበት ጥበብ ልፍተልበት ነገር!!!
.
👇👇👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆👆👆
✋✋✋
.
የተወደዳችሁ ክቡራትና ክቡራን ነገ ማግሰኞ ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት ላይ በአዋሽ 90.7 ላይ በድምጸ መልካሞቻችን ድምጽ ታጅበን፣ ግጥምና ትረካን ከመጽሐፍ ትንተና ጋር አጅበን በፈትላችን ላይ እንሾራለንና ቀጠሯችሁን ከኛ ጋር ማድረጉን እንዳትዘነጉት!!!
.
👉ፈትል👈
እንዝርቱን ልዋስሽ አውሺኝ በሞቴ፤
ሳዞረው ሳሾረው...
ባልሆን እንደ እህቴ ባልሆን እንደናቴ፤
የሴት ወግ ነውና...
ያንቺ የሆነውን ጥበብ አላነክትም፤
ባህሉን ገድፌ በሰጠሽኝ እንዝርት ክር አልሰራበትም።
ባይሆን መስዬበት ሆኜልሽ ባላገር፤
ልፍተልበት ጥበብ ልፍተልበት ነገር!!!
.
👇👇👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆👆👆
ክቡራትና ክቡራን እስቲ በድምጸ መልካሞቻችን የቀጥታ ስርጭት የሙዚቃ ቅብብል ዘና እናድርጋችሁ!
የግጥም ስህተትና ሌላም እንከን ካለ ይቅርታ እንጠይቃለን። ቅብብላቸውን ከወደዳችሁት በጭብጨባ ድጋፍ ስጧቸው። እናመሠግናለን!!!