አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
684 subscribers
1.56K photos
28 videos
17 files
1.15K links
አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE

ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!
Download Telegram
እስቲ እዚህ ላይ የድምጸ መልካሞቻችንን ቅብብል እንጨምር!
🎤🎤🎤
ፀደይ ገ/ጻዲቅ
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ዳግም ተፈራ
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ዮሐንስ አበበ
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ዳግም ተፈራ
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ዮሐንስ አበበ
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ዮሐንስ ጌታቸው (ዮኒ)
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ማህሌት
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
እንደምን አደራችሁ! ኢትዮጵያችንስ እንደምን አደርሽ???
🎤🎤🎤
ሙሴ አበበ መለሰ (ቤቢ) የኤፍሬም ታምሩን ሙዚቃ "እንዴት ነሽ ሀገሬ" ን እንዳቀነቀነው።
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
አሳዛኝ ዜና

አርቲስት ጫንያለሁ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

😢😢😢😢
https://t.me/ATRACOSE
😢😢😢😢
📝📝📝
አብረን_ዝም_እንበል

ጸጋዬ ገ/መድህን (ሎሬት)

ከሰው መንጋ እንገንጠል፤
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል፤
በእፎይታ ጥላ እንጠለል፤
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።

ምነው አዋሽ ማዶ፣ ቆቃ ሸለቆው ግርጌ ሸሽተን፤
የቆቃን ሰቆቃ ሰምተን፤
ሲቃውን ሲሰብቀው አይተን፤
ሰቀቀኑን ተወያይተን፤
የምሽት ጀምበር ቢውጠን።

ውኃ እንደ ዱታ ሲተም፣ በድን ሸለቆ ሲናገር፤
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ ከአጽናፍ አጽናፍ ሲንደረደር፤
ሲያጉተመትም ሲያስገመግም ባይነ ህሊና ለመመስከር፤
ሳንጨነቅ ሳንገደር...፣
ለምንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር፤
ከዓይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር።

አዋሽ ማዶ አብረን እንውረድ፤
አጉል ነው ብለን ሳንፈርድ፤
ድንቅም ነው ሳንል ሳንወድ፤
ዝም ብለን አብረን ብንወርድ፤
ከሰው መንጋ ተለይተን፤
ከጠረኑ ተነጥለን፤
ከጉምጉምታው ተገንጥለን፤
ከኳኳታው ብንከለል፤
ከላንቃው ከድምፁ ሸሽተን በእፎይታ ጥላ እንጠለል፤
በቆይታ በጸጥታ ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።

መቼስ አይሆንም ካልሽ ቅሪ፤
ግዴለም አትገደሪ፤
ልቦናሽ በመተረልሽ ባሳደረብሽ እደሪ።
ተስፋ መቁነን ነው መቼም፤
የሰው ልብ አይችለው የለም።

ብቻ ዳግመኛ ሞት ሳንሞት አዲስ ቀን ሳይጨልምብን፤
ድፍን ደመና ሳይቋጥር ክረምት ውርጅት ሳይወርድብን፤
ኮከባችንን ሳንጠራ፣ ሳንቆጥርባት ሳትቆጥርብን፤
ሞራችንን ሳናስነብብ ሳናሳያት ሳታይብን፤
ጨረቃን መስክሪ ሳንል ሳናውቅባት ሳታውቅብን፤
አዋሽ ማዶ ቆቃ በረን እባክሽ ጀምበር ትጥለቅብን።

ውሃ እንደ ዱታ ሲተምም በድን ሸለቆ ሲናገር፤
በሰማይ ፈረስ ተጭኖ ከአጽናፍ አጽናፍ ሲንደረደር፤
ሲያጉተምትም ሲያስገመግም ባይነ ህሊና ለመመስከር፤
ሳንጨነቅ ሳንገደር ለማንም ምንም ሳናዋይ ሳንናገር ሳንጋገር፤
ከዓይንሽ ከልብሽ ከልቤ አዋሽ ማዶ አብረን እንብረር።

ከሰው ኳኳታ እንነጠል፤
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል፤
በእፎይታ ጥላ እንጠለል፤
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።
📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚
እስቲ ይህን ግጥም እንድገመው!
.
📝📝📝📝📝
ሳይሻል አይቀርም
.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
.
ዙርያ መለስሽን በወስፌ የወጋሽ የናቴ እጄታ፤
መሶብ ሊያበጅ ነው የሚያሰባስበን የፍቅር ገበታ።
ታድያ ምን ያረጋል ለመሶብ ታስቦ የተያዘው ስራ፤
ሰፌድ ሆኖ ቀረ በስምሽ ሊጠራ።
.
ሳይሻል አይቀርም!

መብላቱ ይቅርና እስቲ ቆሻሻውን ለዪ አበጥረሽ፤
ግሳንግሶች ወድቀው ከንጹሐን ፍሬ አምላክ ከደመረሽ።
እንጂስ አልቻልነውም የዘንድሮን ነገር፤
ትውልድ እየጠራን ሞት እየሰረግን፤
ያልተጻፍንበትን ማንበብ ጀምረናል፤
ስለዚህ...
መሶቡ ይቅርና አበጣሪ ሰፌድ ቢኖር ይሻለናል!!!
.
ቀን፦ ፳፫/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.

📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚

ሠላማዊ ቀን ይሁንላችሁ!!!
.
መልካም ውሎ!!!


📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
ቅድስት የቴዎድሮስ ታደሰን "ማለዳ" ሙዚቃ ደግማ እንዳቀነቀነችው!
🎤🎤🎤

👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
ያሬድ ጥበቡ
🎤🎤🎤

👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
እናስታውስዎ

.
የተወደዳችሁ ክቡራትና ክቡራን ነገ ማግሰኞ ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት ላይ በአዋሽ 90.7 ላይ በድምጸ መልካሞቻችን ድምጽ ታጅበን፣ ግጥምና ትረካን ከመጽሐፍ ትንተና ጋር አጅበን በፈትላችን ላይ እንሾራለንና ቀጠሯችሁን ከኛ ጋር ማድረጉን እንዳትዘነጉት!!!
.
👉ፈትል👈

እንዝርቱን ልዋስሽ አውሺኝ በሞቴ፤
ሳዞረው ሳሾረው...
ባልሆን እንደ እህቴ ባልሆን እንደናቴ፤
የሴት ወግ ነውና...
ያንቺ የሆነውን ጥበብ አላነክትም፤
ባህሉን ገድፌ በሰጠሽኝ እንዝርት ክር አልሰራበትም።
ባይሆን መስዬበት ሆኜልሽ ባላገር፤
ልፍተልበት ጥበብ ልፍተልበት ነገር!!!
.


👇👇👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆👆👆
Audio
🎤🎤🎤
ዳግም ተፈራ
👍
ማግሰኞ ፲፰/፪/፪፼፲፪ ዓ.ም.
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧