አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
684 subscribers
1.56K photos
28 videos
17 files
1.15K links
አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE

ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!
Download Telegram
👉ጤና ይስጥልን👈

👇👇👇
ስብስባችንን ለመቀላቀልና ለሀሳብ አስተያየትዎ።
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇👇
👉@ATRACOSE👈
👉@BATRACOSE👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉መልካም ቀን!👈

👇👇👇
ስብስባችንን ለመቀላቀልና ለሀሳብ አስተያየትዎ።
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇👇
👉@ATRACOSE👈
👉@BATRACOSE👈
👆👆👆👆👆👆👆
መልካም እለተ ሰንበት

👇👇👇
ስብስባችንን ለመቀላቀልና ለሀሳብ አስተያየትዎ።
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇👇
👉@ATRACOSE👈
👉@BATRACOSE👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉እናስታውስዎ👈

👇👇👇
ነገ ማግሰኞ ቀትር ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት በአዋሽ 90.7 ላይ ፈትላችን ይደመጣል። የድምጸ መልካሞች ውድድርም አሸናፊው ይታወቃል። ጥበባዊ ጉዳይና ታሪካዊ ንግር መቅረቡ እንደተጠበቀ ነው!
አብራችሁን ሁኑ!!!

👇👇👇👇👇👇
@ATRACOSE👈
@BATRACOSE👈
👆👆👆👆👆👆
👏👏
.
የመጀመርያው የድምጸ መልካማሞች ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ ጌታቸው ዮኒ!
.
እንኳን ደስ አለህ!

👇👇👇
ስብስባችንን ለመቀላቀልና ለሀሳብ አስተያየትዎ።
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇👇
👉@ATRACOSE👈
👉@Birukmifta👈
👆👆👆👆👆👆👆
👇👇👇
ቻናላችንን በመቀላቀል
👇👇👇
👉 https://t.me/ATRACOSE👈

ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት ወደ ስብስባችን በመቀላቀል
👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A
አብራችሁን ሁኑ!

"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!
👉እንዳይዘነጋ👈

👇👇👇
ነገ ኃሙስ ቀትር ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት በአዋሽ 90.7 ላይ ፈትላችን ይደመጣል። የድምጸ መልካሞች ውድድርም በሁለተኛ ዙር ሁለት ድምጸኞችን ይዞ አዲስ ይቀርባል። ጥበባዊ ጉዳይና ታሪካዊ ንግር መቅረቡም እንደተጠበቀ ነው!
አብራችሁን ሁኑ!!!

👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👆👆👆👆👆👆
👇👇👇
ቻናላችንን በመቀላቀል
👇👇👇
👉 @ATRACOSE 👈

ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት ወደ ስብስባችን በመቀላቀል
👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A
አብራችሁን ሁኑ!

"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!

.
👉ፈትል👈

እንዝርቱን ልዋስሽ አውሺኝ በሞቴ፤
ሳዞረው ሳሾረው ባልሆን እንደ እህቴ ባልሆን እንደናቴ፤
የሴት ወግ ነውና...
ያንቺ የሆነውን ጥበብ አላነክትም፤
ባህሉን ገድፌ በሰጠሽኝ እንዝርት ክር አልሰራበትም።
ባይሆን መስዬበት ሆኜልሽ ባላገር፤
ልፍተልበት ጥበብ ልፍተልበት ነገር!!!
.
ዛሬ ማግሰኞ ከስድስት እስከ ሰባት ሰዓት በአዋሽ 90.7 ላይ አብራችሁን ሁኑ!!!

👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A

👇👇👇👇👇👇
@ATRACOSE👈
👆👆👆👆👆👆
Audio
🎤🎤🎤
ጸደይ ገ/ጻድቅ
👍
ኃሙስ ፳፪/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
🎤🎤🎤
ጸደይ ገ/ጻድቅ
👍
ኃሙስ ፳፪/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
@ATRACOSE🎧
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
Audio
🎤🎤🎤
ሜሮን መከተ
👍
ኃሙስ ፳፪/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
👏👏👏

🎧🎧🎧🎧🎧🎧
https://t.me/ATRACOSE
🎧🎧🎧🎧🎧🎧
ለምስሉ መሳሳት ይቅርታ እንጠይቃለን!
👇👇👇
ቻናላችንን በመቀላቀል
👇👇👇
👉https://t.me/ATRACOSE 👈

ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት ወደ ስብስባችን በመቀላቀል
👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A
አብራችሁን ሁኑ!

"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!

እንደምን አደራችሁ። ውሏችሁ ያማረና መልካም ይሁን፤ እናንተም ለሌሎች መልካሞች ሁኑ፤ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና!

መልካም ቀን!!!
.
👇👇👇
ቻናላችንን ለመቀላቀል
👇👇👇
👉https://t.me/ATRACOSE 👈

ሀሳብ አስተያየት ለመስጠት
👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A
አብራችሁን ሁኑ!

"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!!

የዝምታ ጥቅም...(ተፈጥሮ ይገርማል)
.
(እዮብ ዘ ማርያም)
.
የባጡን የቆጡን፣
ስንት አመት አውርተን ስንት አመት ለፍልፈን፤
ግና ምን አመጣን ግና ምን ተረፈን?

እንደውም እንደውም፣
ማያገባው ገብቶ እየቀበጣጠረ፤
የራሳችን ምላስ፣
ከሰው አነካክቶ አጥፍቶን ነበረ።

በህይወታችን መሀል፣
ከሰው በታች ሆኖ ምን በሰው ቢናቅም፤
አሳ ነው ያስተማረን የዝምታን ጥቅም።

አሳ አስጋሪው ሰውዬ...

መንጠቆውን ጥሎ፣
አሳውን ለመያዝ ነበረ ምኞቱ፤
አሳው ግን ተረፈ፣
አፉን እንኳ ሳይከፍት ዝም በማለቱ!!!

.
መልካም ቀን!!!
"በኪነ-ጥበብ አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!"
አትራኮሰ-ጥበቦች ነን!!
.
👇👇👇
👉https://t.me/ATRACOSE 👈
👇👇👇
https://t.me/joinchat/GqC8pRKrtscPwq706Wht4A
📝📝📝📝📝
ሳይሻል አይቀርም
.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
.
ዙርያ መለስሽን በወስፌ የወጋሽ የናቴ እጄታ፤
መሶብ ሊያበጅ ነው የሚያሰባስበን የፍቅር ገበታ።
ታድያ ምን ያረጋል ለመሶብ ታስቦ የተያዘው ስራ፤
ሰፌድ ሆኖ ቀረ በስምሽ ሊጠራ።
.
ሳይሻል አይቀርም!

መብላቱ ይቅርና እስቲ ቆሻሻውን ለዪ አበጥረሽ፤
ግሳንግሶች ወድቀው ከንጹሐን ፍሬ አምላክ ከደመረሽ።
እንጂስ አልቻልነውም የዘንድሮን ነገር፤
ትውልድ እየጠራን ሞት እየሰረግን፤
ያልተጻፍንበትን ማንበብ ጀምረናል፤
ስለዚህ...
መሶቡ ይቅርና አበጣሪ ሰፌድ ቢኖር ይሻለናል!!!
.
ቀን፦ ፳፫/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.

📚📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚📚
📝📝📝📝📝
እንደምን አድረሻል
.
ብሩክ ሚፍታ (ገጣሚ)
.
እንደምን አድረሻል አንቺ ምስኪን ሀገር፤
ዳንኪራ ሲረገጥ መሬቱ ሲወገር።
በፖለቲካ አዚም ልጆችሽ ሲዘሉ፤
እየወዘወዙ አላስተኛሽ አሉ?
ወይንስ አድረሻል በብዙ ጫጫታ፤
ለምደሻል መሰለኝ ጩኸት እየሰሙ ዝም ብሎ መኝታ።

እንግዲህ ምን ይሁን ሁሉም ያብራክሽ ነው፤
ከምድርሽ የወጣ ውልደት ያገነነው።
ምንታደርጊዋለሽ የናት ሆድ ዥንጉርጉር አይደለ ተረቱ፤
ባንዱ መወራጨት ሌሎቹ ይቻሉት ሌሎቹ ይበርቱ!

አንቺ ግን አይክፋሽ በልጆች ጨዋታ፤
ግን አሁን ተነሺ ቀኑ ስለነጋ ይበቃል መኝታ፤
መምጣቱ አይቀርም ያኔ ትተኛለሽ በሌላኛው ማታ፤
እሺ...?!

ቀን፦ ፳፬/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.

📚📚📚📚📚
https://t.me/ATRACOSE
📚📚📚📚📚
አንዴ ስሙኝማ
.
👇👇👇👇👇
"ኢሬቻ ከመቶ ሃምሳ ዓመት በኋላ???"
.

ዝምታን መምረጥ ፈልጌ ነበር። ግን የመምህር ታዬ ቦጋለ ጽሑፍ በህሊናዬ እያቃጨለ ረፍት ነሳኝ።
.
"ዓለም የምትበላሸው በክፉ ሰዎች ሳይሆን በበጎ ሰዎች ዝምታ ነው"
.
እውነት ኢትዮጵያ ታላቅ ሀገር ነች ስትል ታላቅነቷን የፈጠሩት ሁሉም ብሄሮቿ የድርሻቸውን እያዋጡ መሆኑን ከካድክ ታላቅነቷ በትክክል አልገባህም ማለት ነው። እርግጥ መዋጯቸው እንደ ብዛታቸውና ሌሎቹ ጋር እንደደረሰበት መንገድ ይወሰናል እንጂ ያለ ሁሉም አስተዋጽኦ ታላቅ የሆነችም፣ ጸንታ የቆመችም ኢትዮጵያ አልተመሠረተችም!!!
.
ማህበረሰብ የራሱ የሆነ ልማድ አለው። እንደኔ ሀሳብ ያ ልማድ አስተሳሰብ ሲሆን እምነትን ይፈጥራል፡፡ እምነቱ ደግሞ ባህልም በዓልም ይሆናል። ታድያ በዚህ ውስጥ ስህተት ነው ብለህ የምታንጓጥጠው የማህበረሰብ ስርዓት የለም። ምክንያቱም ሁሉም በራሱ እንደራሱ መንገድ ልክ ነው! ከነዚህ ልክ ነገሮች መካከል የኢሬቻ በዓል አንዱና ዋናው ነው።

ኢሬቻ ለዋቄፈና እምነት ተከታዮች ሀይማኖታዊ ስርአት ሲሆን ለኦሮሞ ብሎም ለኢትዮጵያውያን ደግሞ በየኔነት ስሜት የሚያከብሩት ባህል ነው።

ይህ ኢሬቻ እኛ ኢትዮጵያውያን የዓመተ ዓለም ጊዜ ታሪክ ያለን መሆኑና "የዲሞክራሲ" ስርዓትን ማሳያ የሆነው የገዳ ስርዓታችን ውስጥ ያለ በዓልም ባህልም ነው። በዓሉ ዋቃን (ፈጣሪን) ከክረምቱ ወደ በጋው፤ ከጨለማ ወደብርሃን በሠላም በጤና አሸጋገርከን ተብሎ የሚመሠገንበት የምስጋና በዓል ነው።

ታድያ አንድ ታዋቂ ሰው "ኦሮሞ የሚያሳፍር ታሪክ የለውም የሚያሳፍሩ ፖለቲከኞች እንጂ" እንዳሉት ይህንን ከሺ ዓመታቶች በላይ የተሻገረን ክቡር በዓል ዘንድሮ ፖለቲከኞች ለፖለቲካ ፍጆታ ተጠቅመው እናውቅልሃለን ለሚሉት ህዝብ ውርደትና ሀፍረት ሆነዋል። የዚህም ማሳያው "ከመቶ ሃምሳ ዓመት በኋላ" ተብሎ በአዲስ አበባ የተከበረው ኢሬቻ ነው።

ማስረጃዎችን ልጥቀስ፦

ሲጀመት በስርዓቱ መሠረት ኢሬቻ በሆራ (በሀይቅ) ዳር የሚከበር በዓል ሆኖ ሳለ በታቆረ ትንሽ ምንጭ እንዲከበር አድርገው ትንሽ ሲያደርጉት ማየቴ ነው።

ለነገሩ ፖለቲከኞቹ እንደሆን ዋቃን አይፈሩ እግዚአብሔርን፣ አላህን አያፍሩ ተረት እያወሩ ሌላ ቁማር ይጫወታሉ። ተረቱ ምንድን ነው "ከመቶ ሀምሳ ዓመት በኋላ" የሚል የቀሽም ተራች ተረት ነው። ከሁሉ የሚያሳዝኑኝ ይህንን ተቀብለው እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡ አንዳንዶች ናቸው።

በዚህ ላይ የፈረደባቸውን እምዬ ምኒልክን ጠቅሰው "እሳቸው ከልክለው ያስቆሙት ነው" በማለት ያለ ሀፍረት የሚናገሩም አልታጡም።

እስኪ እንጠይቅ፦

ቆይ ከመሰረቱ ኢሬቻ አዲስ አበባ ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊት ይከበር ነበር ለማለት አዲስ አበባ ራሷ መመስረት አለባትኮ። ይህቺ ከተማ በርካታ ሰዎችን በምታኖርበት ልክ የተመሰረተችው ደግሞ በአስራ ስምንት ሰባ ዘጠኝ ዓ.ም. ነው። ያ ማለት መቶ ሠላሳ ሁለት ዓመቷ ነው ማለት ነው። እና ምን ሆነው ነው ከመቶ ሃምሳ ዓመት በኋላ የሚሉን? ፖለቲከኞቹ እኛን መቁጠር አይችሉም ብለው ከሆነ ይንገሩንና እንደምንችል እንንገራቸው።

ሲቀጥል እምዬ ምኒልክ ከለከሉ የሚሉን ያኔ እሳቸው የነበሩት አንኮበር ነው። ታድያ ምን ቆርጧቸው ነው የሚከለክሉት? አረ ለመሆኑ ማንንስ ነው የከለከሉት??? እንዴ ከመቶ ሃምሳ ዓመት በፊትኮ አዲስ አበባ እንደሆን ከስንት አንድ ካልሆነ በቀር ብዙ ሰው የሌለበት ጫካና ደን ነበረች። እንደውም ሰርጸ ፍሬ ስብሃት በአንድ መድረክ ሲናገር "ቀጨኔ የተባለው ስፍራ ለምን እንደተባለ ሲጠይቅ 'ድሮ ቀጭኔዎች ይኖርሩበት ነበር' " ብለውታል። ታድያ ይህንን ያህል አዲስ አበባ ጫካ ከመሆኑ የተነሳ የዱር አራዊት ይኖሩበት ከነበር ማንን ነው ምኒልክ የከለከሉት??? አያነቡም ብለው ከሆነ ይንገሩንና እንደምናነብ እንንገራቸው።

ይህን ያህል እንዴት ግን በዚህ ህዝብ ክቡር በዓል ይቆምራሉ?! ቢያንስ ባያከብሩን እንኳን ለምን ይንቁናል።

እኔ ኢሬቻ አዲስ አበባ አይደለም ባህር ዳር ጣና ላይ፣ ስትፈልግ ሰቆጣ አሸንጌ ላይ፣ ካሻህም ሀዋሳ ሐይቅ ላይ ወይም በፈለከው የኢትዮጵያ ሐይቅ ላይ ብታከብረው ችግር የለብኝም። ችግሬ ግን አከባበርህ ላይ ነው። ዛሬ ለምታራምደው ቆሻሻ ፖለቲካ የተከበረውን ስርዓት የምታውለው ከሆነ ምን ያህል እንደናቅከን ነው የማስበውና ተው!

"ከመቶ ሃምሳ ዓመት በኋላ" የሚሉትን ቀሽም ተረተረት የምታስተጋቡ ወዳጆቼ ደግሞ ከዚህ ነገር ብትከለከሉ ጥሩ ነው።

እውነት ይህንን በሚያደርጉትና በሚሰሩት ሰዎች በጣም አዝናለሁ። የነገን ትውልድም ሳስብ ጋሽ ጸጋዬ የገጠማት ግጥም ትዝ እያለችኝ ሆዴን ባር ባር ይለኛል።

"እኔስ ኖሬያለሁኝ ሲከፋኝ ሲደላኝ፤
ከእንግዲህ ተወልዶ ሰው ለሚሆን ይብላኝ!"

መልካም በዓል!
አሻም!!!

ቀን፦ ፳፬/፩/፪፼፲፪ ዓ.ም.
ብሩክ ሚፍታ!


https://t.me/ATRACOSE
አሳዛኝ ዜና
😢😢😢😢😢
ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የሙዚቃው ሰው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረ አርቲስት ነው።

ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል። እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ ኤልያስ መልካ በፋና ላምሮት የድምፀውያን ተስጥኦ ውድድር ላይ #በዳኝነት ሲያገለግል ቆይቶ ነበር። ለሊቱንም በመኖሪያ ቤቱ ህይወቱ እንዳለፈ ተሰምቷል።

ኤልያስ መልካ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታሪስት፣ ፒያኒስት ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለሀገራችን በማስተዋወቅና ችሎታቸውን ለይቶ በዚያ እንዲያልፉ በማድረግ ይታወቃል።

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተና ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ከዚያ በኃላ ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋር የሰራበት ጊዜ ነበር ። ከ30 በላይ ሙሉ አልበሞችን ልዩ አድርጎም አቀናብሯል።

ከመሃሙድ አህመድ፣ ከኩኩ ሰብስቤ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ ጋር የሰራ ሲሆን፥ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱ ጥቂቶቹ ናቸው። “ሙዚቃ በኤልያስ መልካ ከነሙሉ ክብሯ ታልፋለች”ይላሉ ብዙ ድምፃውያን።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ

አትራኮሰ-ጥበብ በታላቁ የሙዚቃ ቀማሪ ሰው ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል!

😢😢😢😢😢
https://t.me/ATRACOSE
😢😢😢😢😢