አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE
684 subscribers
1.56K photos
28 videos
17 files
1.15K links
አትራኮሰ-ጥበብ/ATRACOSE-TEBEBE

ስለ ጥበብ በጥበብ እናወራለን ከኛ ጋራ ሁኑ!
ግጥም፣ ወግና መጣጥፍ፤
ታሪክና ታሪካዊ ንግሮች፤
ምርጥ ምርጥ እባባልና ምስሎች፤
ሰበርና ወሳኝ መረጃዎች፤
የድምጸ መልካሞች ሙዚቃ፤
.
.
በሥነ-ኪን አቅም የተሻለ ነገን እንፈጥራለን!
.
.
.
.
አትራኮሰ-ጥበብ!!!
Download Telegram
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!
ሙሾ አውራጇ ልከኛና ሚዛናዊ አገላለጽ ከገለጸችው የተሻለ የተገለጸ አይመስለኝም። ምን አለች፦

""ከመልአክ ከሰይጣን ቀምሞ ሰርትዎ፤
ማን ብዬ ልበልሁ ምን ብዬ ልጥራዎ?
የመልአኩ ለታ...፣
አልብሱት አጉርሱት ሲያሰኝዎ ዋለ፤
የሰይጣኑም ለታ...፣
ስቀሉት ቁረጡት ሲያሰኝዎ ዋለ፤
ቆንጥረው ቆንጥረው ሁሉን ያካበቱ፤
በመጨረሻው ቀን...፣
ግስላ ሆኑና መቅደላ ከተቱ።"

ወሩ ፀሐይ አናት የምትበጠርቅበት ወር ቢሆንም፤ ስለሱ የጻፉ ታሪክ ጸሐፍት የተወለደበትን ቀን አንዴ በአምስት አንዴ በስድስት እያሉ ባይስማሙበትም ሰውየው ግን ተረት አይደለም ተወልዷል።

ያውም እናት ኢትዮጵያ ከአንድ ትልቅ ወደ ብዙ ትናንሽ ወደተቀየረችበት፣ ወደ ተነጣጠለችበት የመሳፍንት ዘመን እርሱ አንዳች ክስተት ሆኖ ከወ/ሮ አትጠገብ የወንደሰንና ከአቶ ኃይሉ ወልደ ጊዮርጊስ አብራክ በጥንቷ በጌ ምድር በአሁኗ ጎንዱር፣ ቋራ ተወልዷል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ ባይሳካለትም፣ እሱ በቀደደው ጎህ፣ እሱ ባነደደው ብርሃን አልፈው እየተመሩ ነው አጼ ዮሐንስ አራተኛ ጅምሩን ቁጥለውት ተአምረኛው ዳግማዊ አጼ ምኒልክ የዚህችን ሀገር አንድነት ያረጋገጡት።

ዘፋኙ በአንዲት ቃል ተዋከበና እንዳለው፣ ዘመኑን ሁሉ ሲውከበከብ፣ ሲወራከብ፣ ሲዋትት፣ ሲንከራተት፤  በገዛ ወገኖቹ ሲጠላና ተቀባይነትን ሲነፈግ ቢኖርም ታሪክ ግን ሊረሳው የማይችል ክቡር፣ በጣም ክቡድ ሰው ነው።

እንዴት የሚል ካለ እንደ ምሑራን ገለጻ የኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ቁጥሩን የሚጀምረው፣ ከሱ አንድ ብሎ ነውና ነው።

ታሪክ አይዘነጌው ክስተት፣ በፈረስ ስሙ አባ ታጠቅ፣ በሽፍትነት ጊዜው ደጃዝማች ካሳ፣ በደረስጌ ማርያም ንጉሠ ነገሥት ተብሎ ሲሾም ደግሞ ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ ይባላል።

ዛሬ ልደቱ ነው!

መልካም ልደት ለኛ!!!

                        ጥር ፮/፪፼፲፰ ዓ.ም.


ቴሌግራም፦ https://t.me/BirukMiftaAtracose

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/share/1A6AoJodXA/
Forwarded from Event Addis Media
📌አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም እንደተለየ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን አስታውቋል።

ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር።

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1

ለተጨማሪው: https://t.me/EventAddis1
📌 ነጻነት ወርቅነህ ዛሬ ጠዋት

ነጻነት ዛሬ ጠዋት ወደ ስራ ሊሄድ እየለባበሰ ነበረ። ህመም ሲሰማው ጓደኛውን ጠርቶት ወደ ICMC ሆስፒታል ሄዱ። መንገድ ላይ እያለም ህመሙ እየባሰበት ነበረ። ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ምሳ ሰዓት ገደማ አረፈ። ፖሊሶች በሆስፒታሉ ተገኝተው ሙያዊ የምርመራ ስራቸውን አከናውነዋል።

አሌልቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅበሩኝ

አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በሕይወት እያለ ሲሞት አሌልቱ ጊዮርጊስ ከአያቱ አጠገብ ቀብሩ እንዲፈጸም እንደሚፈልግ ለወዳጆቹ ደጋግሞ ይናገር የነበረ ሲሆን ያለፈው ሳምንትም አሌልቱ ጊዮርጊስ በመሄድ ቤተክርስቲያኒቱን የማሳደስ ስራ ስለማከናወን ከሚመለከታቸው የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎች ጋር ተነጋግሮ መመለሱ ተሰምቷል።

ኑሮዋን በአሜሪካ ያደረገችው ባለቤቱ እና የልጆቹ እናት እሁድ ጠዋት ከአሜሪካ አዲስ አበባ የምትገባ ሲሆን በዚያው ሰዓት ስርዓተ ቀብሩ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

©️ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ዋቢ አድርጎ ኢቪንት አዲስ እንደዘገበው!
ሳቃችን ትዝታ ሆነ - ደስታችንም ታሪክ!

ሞት ፍትሐዊ አይደለም- ገና ገና ያልኖረውን ብዙ ያለመውን ወሰደው። ማን ያስመልሰዋል?

አልጽፍም ብዬ ነበር ግን ታነበው ይመስል፤ ዝም ስል ትታዘበኝ ይመስል ይህን ልልህ ፈልጌ ነው መጻፌ።

ነጺ ምን ያህል እንደምንወድህ፣ ምን ያህል እንደምናከብርህ፣ በአንተ ሥራ ስንት የሀዘን ድባብ የወረሳቸው ፊቶች እንደፈኩ፣ የተከደኑ ጥርሶች በፈገግታ እንደተከፈቱ አልነገርንህም።
አንተም ዋጋህን ያወቅኸው አይመስለኝም።

አንተ ስትኖርበት  የምንጠላውን እንወድዋለን አንተ ስትኖርበት የሰለቸችን ዓለም ሌላ ገጿን ታሳየንና ልንወዳት እንዳዳለን።

ፍሬሽ ማን ትያትር ሲመረቅ የትያትሩ መሪ ተዋናይ ሁነህ ሳለ የተሰለፈውን ሕዝብ ሁሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ስትል ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁህ። ለሰዎች ያለህን ክብርም የተረዳሁት።

ነጺ በዘር ወይ በሃይማኖት የማይከፈሉብህ የሁሉም ነበርህ።
ጥቂቶች ብቻ የሚያገኙት መታደል ነው- ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ጸጋም ነው።

ግን አንተን በመሰሉ ሕይወት የሚያቀሉ ጥበበኞች አብረን የምናልፋቸው ብዙ ቀናት ነበሩ።

እንግዲህ ምን እንላለን እንባችን አይመልስህ ለቤተሰብ ለወዳጅ ለአድናቂ ሁሉ መጽናናት ይሁን።

ሳትሰስት ስለሰጠኸን እያመመህ እንኳ ከቤታችን ስላልጠፋህ እናመሰግናለን።

ነጺ እስካለንና በማይቀረው ማረፊያችን እስክንገናኝ  እናስብሃለን!

አንድ የቤተሰብ አባል ወይ አብሮ አደግ የተለየን ያህል ነው የደነገጥነው ያዘነው… ያለቀስነው… እንጃ ብቻ!

የራስህ ቀለም ያለህ የዘመናችን መልክ፣ ቆንጆ  ትዝታችን፣ በታሪክ ሰምተን ሳይሆን  እድሜህን ስለተጋራን ደስ ይለናል።

እግዚአብሔር ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን!

አይገርምም??? ነጺ አረፈ ብለን እያወራን ነው።

©ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው
ነፃነት ወርቅነህ እምሩ( 1974-2018)

ማስታወሻ፦ሐምሌ ወር ላይ 2017 ነፃነት ለተወዳጅ ሚድያ ደወለ፦

"....እዝራ። ታሪካችን እኮ መሰነድ አለበት።እኔም መረጃ እልካለሁ።" በማለት ነበር ነፃነት የስነዳ ሥራው አዎንታዊ እሳቤውን የገለፀው። እኛም መረጃ ማሰባሰብ ጀምረን ነበር። ነፂ ግን"... ደርሶኛል። አየዋለሁ እዝራችን ነበር የስንብት መልዕክቱ።

ዛሬ ጥር 8 2018 ዓ.ም የሰማነው ክፉ ዜና ግን ለመስማት ይከብዳል። ነፂ ነፍስህ በሰላም ትረፍ። እንደወደድከው ታሪክህን ሰንደናል።

ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።

ከእነዚህ ውስጥ የሚድያ ሰዎችና የቴአትር ባለሙያዎች ይገኙበታል። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ 50 በላይ የፊልምና የቴአትር ባለሙያዎች ፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን አመራሮች እና የሚድያ ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።

በዚህ ፅሑፍ የሙያ ታሪኩ የሚሰነድለት ጠንካራ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ነው። ዕዝራ እጅጉ እና ሣራ አህመድ ታሪኩን አጠናክረውታል።

#ትውልድና ልጅነት

የኪነ ጥበብ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ እምሩ የካቲት 10 1974 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ወርቅነህ እምሩ እና ከእናቱ ከወይዘሮ ምናለሸዋ ይፍሩ በአዲስ አበባ ከተማ በፖሊስ ሆስፒታል ተወለደ።ለቤተሰቡ አራተኛ ልጅ ሲሆን ሶስት ወንድሞች እና አንድ እህት በነበረው ቤተሰብ ውስጥ በኡራኤል ሰፈር እንዳደገ ይነገራል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በአስፋው ወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረ ሲሆን እስከ 7ኛ ክፍል ባለው የልጅነት እና የትምህርት ቤት ቆይታው ለኪነጥበብ የተለየ ፍቅር አልነበረውም። የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለ "የጉሊቷ እናቴ የሚል ቲያትር ላይ የሴት ገፀ-ባህሪይ ይዞ መተወኑ ይነገራል። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ምሥራቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል።

#ወደኪነ-ጥበብ አለም የገባበት አጋጣሚ

የ16 አመት ልጅ ሳለ ከኡራኤል መርካቶ ድረስ በእግሩ እየተመላለሰ ዩኒቲ የቴአትር ክበብን እንደተቀላቀለ ቲያትር መስራት መጀመሩ ይነገራል። የዩኒቲ ክለብ መፍረስ ቀጣዩ የነፃነት መዳረሻ የሩሲያ ባህል ማዕከል ወይም ፑሽኪን አዳራሽ እንዲሆን አደረገው። በፑሽኪን ቆይታውም በግጥሞች በወጎች መሀል የሚተላለፉ የተመልካችን ቀልብ የሚይዙ የ30 ደቂቃ ድራማዎችን ሠርቷል።በፑሽኪን ቆይታው ፍሬሸ ማን የሚለውን ድርሰቱን በ40 ደቂቃ የሚያልቅ ድራማ አድርጎ ሠርቶት ነበር።በኃላም ቲያትሩን አሻሽሎ ከአዳነች ወ/ገብርኤል ጋር መስራቱ አይዘነጋመሰ። ነፃነት በአንድ በኩል ፍሬሽ ማንን ፑሽኪን እያሳየ" የመጨረሻ ሀጢያት" የሚል በቀበሌ አዳራሽ ውስጥ የተሰራ ቲያትርም አሳይቷል።

በፑሽኪን በነበረው ቆይታ ላይ አብረውት ከሰሩት ተዋናዮች መሀከል ኢሳያስ አስራት ስለነፃነት የትወና አቅም ይህን ብሏል።
"እኔ ስለ ነጺ እመሰክራለሁ።የሚሠራውን ገና ሲወጥነው ያውቀዋል።
ፑሽኪን (የሩሲያ ባህል ማዕከል) በነበርንበት ወቅት እኔም እርሱም ተውኔት እንጽፋለን፣እናዘጋጃለን፣እንተውናለን።ፉክክር ነበር በመሀላችን።
ነፂ ግን ይለያል። አድምቶ መሥራት እና በዚያው መጠንከር እና ግቡን መምታት ያውቅበታል" በማለት መስክሯል።

ነዋሪነቱን በካናዳ ያደረገው ገዛኸኝ መኮንን ሲናገር ፦ "...ለመጀመሪያ ጊዜ በፑሽኪን ማዕከል መድረክ በግጥም መሀል በሚያቀርባቸው አጫጭር ተውኔቶች ላይ ነበር extraordinary የሆነ ችሎታ እንዳለው ያስመሰከረው።
እኔ እና ወዳጄ ሚሊዮን አየለ በጋራ ጽፈን ባዘጋጀነው ፌስታል የተሰኘች የ 5 ደቂቃ ድራማ ላይ ካስት ስናደረገው ከሙናዬ መንበሩ ጋር እንዴት በልዩ ሁኔታ እንደተጫወተው አሁንም አይረሳኝም።
ከዚያ በኋላ በጣም በርካታ ፊልሞች ላይ በመተወን አቅሙን አሳይቷል " በማለት ምስክርነት ሰጥቷል።

#የነፃነት ኪነ ጥበባዊ አበርክቶዎች

በቲያትር ዘርፍ

ነፃነት ወርቅነህ "በይቅርታ ምሽት በማዘጋጃ ቲያትር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ በቲያትር ቤት ደረጃ የሰራው ሥራ ሲሆን በመቀጠልም በብሔራዊ ቲያትር "ካብ ለካብ" የሚባል ቲያትር ላይ "የትወና ብቃቱን አሳይቷል። የዳዊት እንዚራ፤ፍሬሽ ማን፤የጓሮ ጌታ ፤የብሩክታዊት ስጦታ የተባሉ ቲያትሮች የሰራ ሲሆን ፍሬሽ ማን የራሱ ድርሰት እና በህዝብ ዘንድም ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘበት ስራው ነው።

#በቴሌቪዥን ድራማ እና በሬዲዮ ድራማ

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው ስንቅ ፕሮግራም ላይ ባለቤትነቱ የአለልኝ መኳንንት እና የጥላሁን ዘውገ ፕሮግራም ላይ በድርሰት ፤ በአዘጋጅነት ፤ በዳይሬክተርነት እንዲሁም በተዋናይነት ሠርቷል። ጥላሁን ዘውገ ስለ ነፃነት ሲመሰክር ነፃነት ከትወና ባሻገር የማዘጋጀት ችሎታም ስለነበረው ድራማዎችን እንዲያዘጋጅ ዕድል እንሰጠው ነበር ብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "መስኮት በተሰኘ የአምስት ደቂቃ ድራማዎች ላይ በበርካታ ድርሰቶች ላይ የነፃነትን አሻራ ማግኘት ይቻላል።

በሬዲዮ ድራማዎች ላይ በድርሰት በኢትዮጵያ ሬዲዮ እንዲሁም በfm 97.1 ተሳትፏል።

#የፊልሙ አለም

የመጀመሪያ ፊልሙ "የማይደረስበት" የሚለው ሲሆን ኪሳራ ላይ የጣለው ፊልም ሲሆን ከዛ በኃላ FBI1,2,3፤ የአንቺው ሌባ 1,2፤ Mr x ፤ባለቀለም ህልሞች፤ስለማይዘነጋ ውለታ፤ዕድል 20 የተሰኙ ፊልሞችን የሠራ ሲሆን የFBI 1,2,3 ፊልም ደራሲ እሱ ሲሆን፤በባለቀለም ህልሞች ላይ በዳይሬክቲንግ እንዲሁም በMr X ፊልም ላይ በድርሰት ተሳትፏል።በህዝብ ዘንድ በባለቀለም ህልሞች ፤ በአንቺው ሌባ እንዲሁም በFBI ፊልሞችየተለየ አድናቆት እና ተወዳጅነት ሊያገኝ ችሏል።

#ሌሎች ሥራዎች

ነፃነት ደራሲ ፤ተዋናይ ፤ዳይሬክተር ብቻ አልነበረም። ጎበዝ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢም ጭምር እንጂ በተለይ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ በየፕሮግራሙ አዳዲስ ቃና እየጨመረ ለዓመታት ፕሮግራሙ በህዝብ ልብ ውስጥ እንደተወደደ እንዲሁም ሳይሰለች እንዲታይ አስችሎታል።

ከቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነቱ በተጨማሪ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እንዲሁም መድረኮች መልዕክታቸውን ሳያጡ በሳቅ እንዲታጀቡ አድርጎ ማቅረብም ላይም የሚደርስበት የለም። በአጠቃላይ ነፃነት የዘርፈ ብዙ ሙያ ባለቤት ነበር ማለት ያስችላል።

#ልዩ ሰብዕና
1
ነፃነት ወርቅነህ ሌሎች ሲደሰቱ ከማንም በላይ ይደሰታል። በበርካታ ችግሮች ቢያልፍም ሳቅ ከምንም በላይ መድኃኒት ነው በሚለው አስተሳሰቡ ለዓመታት ዘልቋል። አብረውት ለሚሠሩ የኪነ -ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ ክብር ያለው ነፃነት ለሰዎች በመድረስ የሚያምን በሰዎች የደስታና የሀዘን ጊዜም ቀድሞ የሚገኝ መሆኑን የቅርቦቹ ይመሰክራሉ።

#የትዳር ህይወት

ነፃነት ወርቅነህ፣ ከንፁህ ዘር በላይ ጋር ትዳር የመሠረተ ሲሆን የሦስት ልጆች አባት ነው። ልጆቹም የ18፤15 እና የ9 አመት ዕድሜ ሲኖራቸው የመጀመሪያ ልጁ ኦራገን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝቶ እየተማረ እንደሆነ፤ሁለተኛ ልጁ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መከታተል እንደጀመረች እንዲሁም የመጨረሻዋ ለፒያኖ ፍቅር እንዳለት ከወራት በፊት ገልፆ ነበር።

ነፃነት ወርቅነህ አርብ ጥር 8 2018 44 አመቱን ሊይዝ 30 ቀናት ሲቀረው ከዚህ አለም ድካም አርፏል።

©ተወዳጅ ሚድያ
የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርአተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን በመፈጸም ላይ ይገኛል። ይህንን ኢቢኤስ ቴሌቭዥን በቀጥታ ስርጭት እያሳየው ይገኛል።
ተፈጸመ!

ጥር ፲/፪፼፲፰ ዓ.ም.
ከቀኑ ፭:፵፮ እለተ እሑድ
የሂሩት በቀለን "ጣራና ግርግዳ" ሙዚቃ ማህሌት ሙሉብርሃን ደግማ እንደሞዘቀችው።
😢😢😢

https://t.me/BirukMiftaAtracose
1😢1
ለጥንቃቄ!

ነገ ጀምሮ ፌስታል ይዞ የተገኘ 5ሺ ብር ይቀጣል

የፕላስቲክ ከረጢት ስስ ፌስታልን ይዞ መገኘት የሚከለክለው አዋጅ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።

ኖር ሬድዮ ባሰባሰው መረጃ መሠረት ከነገ ጥር 23 ጀምሮ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚጠቀሙ፣ የሚያመርቱና ወደሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላት ላይ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ተገልጿል።

ጥቁር፣ ነጭ፣ ትናንሽ እና ትልልቅ በእጅ የሚያዙ ፌስታሎች በእጅ ይዞ የተገኘ ግለሰብ፡- ከ2,000 እስከ 5,000 ብር፤ በሌላ በኩል አምራቾች፣ አከማች እና አከፋፋዮች፡- ከ50,000 እስከ 200,000 ብር ቅጣት እና እስከ አምስት አመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ይጠብቃችኋል።

ምንጭ፦ ኢቨንት አዲስ
እንኳን ለ ፩፻፴ ኛው (130) ዓመት የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
ዋ! .... ያቺ ዓድዋ

ዋ! ....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....
ባንቺ ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና ....

ዋ!
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰዉብሽ ለት፤

ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያነት ምስክርዋ

ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሣኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዊ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው-እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው - በለው - በለው - በለው!

ዋ! .... ዓድዋ....
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በጻኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጐራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ' በለው-በለው!

ዋ!.... ዓድዋ ....
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሡ እንደገና።

.... ዋ! .... ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ ....

የካቲት - ፲፱፻፰፬ - ዓድዋ
እሳት ወይ አበባ ከጸጋዬ ገብረ መድኅን

👇👇👇
https://t.me/ATRACOSE
👇👇👇
"አዝማሪሽ እኔ ነኝ"
ከነ ሙሉ ቅንብሩ!

ድምጻውያን
ትንቢተ ኢሳያስ (ባቢ)
ዮሴፍ በቀለ
ያሬድ ጥበቡ
ዳዊት በቀለ

ግጥም
ብሩክ ሚፍታ (አትራኮስ)

ዜማ
ዳዊት በቀለ

መሰንቆ ተጫዋች
ደግሰው አበበ

ድምጽ ቀረጻ፣ ቅንብር፣ ማስተሪንግ
ዳኜ ደጀኔ (ከበሮ ስቱድዮ)

📻📻📻
https://t.me/ATRACOSE
📻📻📻